አቶ በላይነህ ክንዴንና የተለያዩ የአማራ ባለሃብቶችን ስም በመጥራት መስዋዕትነት እየተከፈለበት ያለውን ትግል ለማኮላሸት የምታደርጉትን እንቅስቃሴ ደርሰንበታል፤ መንግሥትም ሆነ መከላከያ ንብረታችሁን አይጠብቅም፤ ንብረታችሁን የሚጠብቀው ሕዝብ ነው፤ ብታርፉ ይሻላችኋል ሲሉ “በባንዳነት” ፈርጀው እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚጠቁም መረጃ ራሳቸውን ኢትዮ 360 ብለው የሚጠሩት ሰጡ። ይህንን የሰሙ ከዚህ በፊት በዚሁ ሚዲያ አቶ ግርማ የሺጥላ “half caste ሃፍ ካስት” ወይም ዲቃላ ወይም ቅልቅል በማለት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ አስቀድሞ ካሰራጩት መረጃ ጋር አመሳስለውታል። ምናልባትም መረጃው የደረሳቸው ባለሃብቶች ጉዳዩ በሕግ እንዲታይላቸው የሚያደርጉበት ሁኔታ ይኖራል ተብሏል። ሙሉ መረጃውን ቪዲዮው ላይ ይመልከቱ። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በላይነህ ክንዴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ኢትዮ 360ዎች ጠቆሙ
Ethio 360
ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
በኤርሚያስ ለገሰ እና በሃብታሙ አያሌው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ውዝግብ በርካታዎችን ሲነጋግር የቆየ ነበር። በተለይ በመካከላቸው ጥል እንዳለ በግልጽ በሚታይ መልኩ በአደባባይ እየወጡ የሚናገሩት ከበስተጀርባ ምን እየተደረገ ነው የሚል ጥያቄ ብዙዎች እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። አሁን ግን ሁኔታው ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። በኤርሚያስ እና በሃብታሙ መካከል ሰሞኑን የታየው ልዩነት አስመልክቶ ጥቂቶቹን ቪዲዮዎች እንመልከት፤ ከዚህ ሌላ የጌታቸው ሹመት በተሰማበት ቅዳሜ ዕለት እንደተለመደው ከሃብታሙ ጋር ለውይይት መውጣት የነበረበት ኤርሚያስ አልወጣም። ሃብታሙ ከሌላ ግለሰብ ጋር ለወሬ የወጡ ሲሆን በበረከት እና ጌታቸው ሥልታዊ የካድሬ ትንታኔው የበርካታዎችን ቀልብ የሚስው ኤርሚያስ በዚህ ወሳኝ ቀን ለትንታኔ አለመከሰቱ ምናልባት ለጌታቸው “ሹመት ያዳብር” … [Read more...] about ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
ስሙ የክህደት መጠሪያ ሆነ እንጂ የስሙ ትርጉም ግሩም ነው። ይሁዳ የሚለው ቃል በእብራይስጥም “ይሁዳ” ማለት ነው፤ “ያዳ” ነው ሥርወ ቃሉ ይላሉ የሙያው ባለቤቶች። ይህ ደግሞ ትርጉሙ “ማመስገን” ማለት ነው። በግሪክም ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው - “የተመሰገነ”፣ “ምስጉን” ማለት ነው። “የአስቆሮቱ” የሚለው ቃል ደግሞ የክፋት መጠሪያ አይደለም። በተለምዶ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” በማለት ከሃዲዎችን ስንጠራቸው “አስቆሮቱ” የይሁዳ የክፋት ማዕረግ ይመስለናል። ሊቃውንቱ እንደሚሉን ከሆነ ትርጉሙ “የኬሪዮት ሰው” ወይም “የአራዳ ልጅ” እንደ ማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ በከሃዲነቱ ባናውቀው ኖሮ “ተመስገን ያራዳ ልጅ” ብለን እንጠራው ነበር። ስሙ ግን ከግብሩ ፍጹም የራቀ ነው፤ እንዲያውም ተጻራሪ። ይሁዳ ከሃዲ ብቻ አይደለም፤ ማሳካት የሚፈልገው ዓላማ ያለውና የሚያደርገውን … [Read more...] about የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
ትህነግና ኢትዮ 360 በአማራ ክልል ሰብል እንዲወድም በቅንጅት እየሠሩ ነው
ምዕራብ ጎንደርን ጨምሮ ሰፊ እርሻ መሬት ያላቸው አካባቢዎች ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ ማስታወቂያ ሲያወጡ ይህ የመጀመርያቸው አይደለም። ማህበራዊ ሚዲያ በማይታወቅበት ጊዜ በኢቲቪና አማራ ቲቪ ጭምር በሚሊዮን የሚቆጠር ሰራተኛ እንፈልጋለን ብለው ማስታወቂያ ሲያስነግሩ ኖረዋል። ባለፈው አመት በዛ ቃውጢ ጦርነት ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ በማስታወቂያ ጠርተዋል። በሌላ አካባቢ ያለው አርሶ አደር የራሱ ሰብል እስኪደርስ ለአንድና ሁለት ወር ሰርቶ እንደሚመለስ ይታወቃል። በቋሚነት በርሃ ወርዶ የሚሰራ፣ ካምፕ ተሰርቶለት በአካባቢው የሚከርም ሞልቷል። የሰብል ስብሰባን ብቻ ስራቸው አድርገው በቆላማ አካባቢዎቹ የሚኖሩ በርካታ ወጣቶች አሉ። ለረዥም አመታት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚቀበሉት ወጣት በላይ የቋራ፣ የመተማ፣ አርማጭሆ፣ ወልቃይት ጠገዴ አካባቢዎች ሰብል … [Read more...] about ትህነግና ኢትዮ 360 በአማራ ክልል ሰብል እንዲወድም በቅንጅት እየሠሩ ነው
ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን … [Read more...] about ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
ራሱን ኢትዮ 360 ብሎ ስለሚጠራው ቡድን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በመረጃ ማንነቱን እና ለማን እንደሚሠራ አጋልጠናል። የትህነግ ተከፋይ ቡድን መሆኑን ከሁለት ዓመት በፊት በማስረጃ ተናግረናል። ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች ይመልከቱ። “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳየበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረውየ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ በዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ሲሻቸው መንፈሣዊ ሆነው በመቅረብ የሰውን ቀልብ ለመሳብ ይሞክራሉ። ሃብታሙ አያሌው አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ዘመድኩን በቀለ … [Read more...] about ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
ከሽፏል!
የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!
እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
እነ ኤርሚያስ ለገሰ አርብ ምሽት አንድ ፕሮግራም ሰርተዋል። በዚህ ፕሮግራም ዋና ሀሳባቸው አማራ ክልል ላይ አዲስ መንግስት መመስረት የለበትም የሚል ነው። በፕሮግራሙ: 1) አማራ ክልል ላይ ጭካኔና ውድመት እየፈፀመ ያለውን የትግሬ ወራሪ ኃይል TDF እያለ የትግሬ ወራሪ ራሱን የሚጠራበትን ይፋዊ ስሙ አድርጎ፣ ይህ ቡድን ምርጥ ተሞክሮ እንደሆነ ይናገራል። የትግራይ ወራሪ ኃይልን ጥሩ ምሳሌ ሲያደርግ፣ የትግራይን ወራሪ ኃይል እውቅና ሰጥቶ ትክክለኛና ሌላውም ምሳሌ ሊያደርገው የሚገባ ነው ሲል ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። አማራን ለማጥፋት እየሰራ ያለን ኃይል ነው ምርጥ ተሞክሮ እያለ የሚያስተዋውቀው፣ የሚያሞካሸው። አማራው ላይ ይህን ያህል ውድመት እየፈፀመ ያለውን ቡድን ጠቅሶ አማራውም ይህን የሚመስል ቡድን ነው መንግስት ሊይዝ የሚገባው ይላል። ይህ ማለት የትግራይ ወራሪ … [Read more...] about እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ (ትህነግ) ይመራው የነበረው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከትህነጉ አሸባሪ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ የካድሬ ቃል” ኤርሚያስ ሲጠቀም መቆየቱን የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል። መረጃውን ይፋ ያደረገው ኢትዮ 12 ነው። በ360 “ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሰሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ July 2, … [Read more...] about የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ
ከየአቅጣጫው ከተለያዩ ምንጮች ገንዘብ እንደሚለገሰውና የውክልና ፕሮፓጋንዳ እንደሚሠራ ይፋ የተደረገበት ኢትዮ 360 ሚዲያ ይህንኑ ለማስተባበል የገንዘብ ችግር አንቆናል፤ ዋናው ችግሬ ብር ነው እርዱኝ ሲል ባወጣው መግለጫ የልመና ድምጹን አሰማ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በውስጥ በተከሰተ መከፋፈል ምክንያት የተለያዩ ምሥጢሮች እየወጡበት የተቸገረው ኢትዮ 360 አሁን ካለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ራሱን መገምገሙን በመግለጫው ጠቁሟል። ቅዳሜ ዕለት መግለጫው እንደወጣ በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ (በተለምዶ ዲኤምቪ በሚባለው) የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያነጋገረችው የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለችው መግለጫው ሌላ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ስልት ነው በማት አስተያየት ሰጪዎች መናገራቸውን ገልጻለች። “ሁሉንም እኮ እናውቃቸዋለን፤ ኮትና ከረባት አሳምረው ሲታዩ … [Read more...] about ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ