• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው

September 1, 2021 01:39 am by Editor 1 Comment

የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ (ትህነግ) ይመራው የነበረው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከትህነጉ አሸባሪ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ የካድሬ ቃል” ኤርሚያስ ሲጠቀም መቆየቱን የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል። መረጃውን ይፋ ያደረገው ኢትዮ 12 ነው።

በ360 “ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሰሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ July 2, 2020 ያስነበበው ዜና እዚህ ላይ ይገኛል።

የኢትዮ 12 መረጃ አቀባዩን ጠቅሶ እንዳለው ቀደም ሲል ከተለመደው አግባብ በተለየ ኤርሚያስ ተደብቆ ለብቻው ከጌታቸው ረዳ ጋር በስልክ እንደሚገናኝ ሃብታሙ አያሌው አውቋል። ሰሞኑንን ሁለቱ “ተንታኞች” እየተካረሩ የመጡትም በዚሁ ምክንያት ነው። ሃብታሙ ብዙ ጊዜ ሲል ባይሰማም “ለትንታኔ“ በሚወጡበት ጊዜ ኤርሚያስ አሸባሪውን ጌታቸው “አቶ ጌታቸው“ እያለ “እርሳቸው“ በማለት ያለምንም መሸማቀቅ እንደሚጠራው ፕሮግራሙን የሚከታተሉ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን ሃብታሙም የታዘበው ነው::

ዘወትር አንዱ ሌላኛውን እየደገፉ መንግሥትን፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ከሕዝብ ለመነጠል ዘመቻ ሲያካሂዱ የሚታወቁት ሃብታሙና ኤርሚያስ፣ ባለፈው ዓርብ ዱላ ቀረሽ ዘለፋ ውስጥ የገቡበት ዋና ምክንያት ኤርሚያስ ሃብታሙን ተደብቆ ከጌታቸው ረዳ ጋር በምሥጢር መግጠሙ እንደሆነ ተባባሪያችን አመልክቷል።

አርብ ዕለት በተላለፈው የ“ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ሃብታሙ “ስለወያኔ ሲነሳ ያንቀጠቅጥሃል” በሚል ኤርሚያስን ክፉኛ ሲዘልፈው ተሰምቷል። ይህን ከማለቱ በፊትም “እኔም ሆንኩ አንተ ኢህአዴግ በነበርንበት ወቅት ለፈጸምነው እንደ ድርሻችን እንጠየቃለን” ካለ በኋላ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ዜጎችን ለመምታት በተደነገገው የጸረ ሽብር ህግ የኤርሚያስ ሚና ጉልህ እንደነበር በይፋ አስታውቋል። ከዚህም የዘለለ ተናግሮት ነበር። “እኔ እዛው ሆኜ ታግያለሁ” ሲልም ኤርሚያስ “ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲቀዘቅዝ በጄ” እንዲሉ አይነት መሆኑንን አመልክቷል።

የአርብ ዕለቱ መስመር የለቀቀ ሁኔታ ያወራጨው ኤርሚያስ፤ ሃብታሙ ተናግሮ ሲያበቃ “እኔም ያልኩት ይህንኑ ነው” በማለት ከሃብታሙ ጋር ሃሳቡ ተመሳሳይ እንደነበር ለመናገር የሞከረ ቢሆንም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በመቀጠለም “ወደ ኋላ በመሄድ ይህ ተደርጓል ያ ተደርጓል ማለቱ ብዙም አስፈላጊ አይደለም” በማለት የሃብታሙን ክስ ለማጣጣል ሞክሯል። በዕለቱ ሁለቱን ያጣላቸው ዋና ሃሳብ ኤርሚያስ በአማራ ክልል ትህነግ እያደረሰ ላለው ጉዳት ዐቢይም ተጠያቂ ነው፤ ምክንያቱም ዐቢይ ጄኖሳይደር (ጅምላ ጨፍጫፊ) ነው በማለቱ ነበር። በአንጻሩ ሃብታሙ አማራን እየጨፈጨፈ እና ፈንጂ እየተኮሰ ንፁሃንን እየገደለ ያለው ዐቢይ ሳይሆን ትህነግ ነው ብሏል። ሁኔታው እየከረረ ሲሄድ ሃብታሙ በግልጽ ኤርሚያስን በመዝለፍ “ስለህወሃት ሲነሳ ያንቀጠቅጥሃል” ብሎታል። የዚህ የሃብታሙ ንግግር የኤርሚያስን የበፊት ሁኔታ የሚገልጽ ብቻ ሳይሆን አሁን የተደረሰበትና ከእነ ጌታቸው ጋር የሚያደርገውን ምሥጢራዊ ግንኑነት ያካተተ እንደሆነ ተነግሯል።     

ሰኞና ማክሰኞ ከኢየሩሳሌምና ከብሩክ ጋር 360 ላይ “ለትንታኔ” የቀረበው ኤርሚያስ ለገሰ ብቻ ሲሆን፣ ሃብታሙ ያልቀረበበት ምክንያት ለጊዜው አልታወቀም። ሃብታሙ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ “አሁን አማራን እየጨረሰ ያለው ትህነግ ነው” በሚል አቋሙን አጥርቶ የመጣ ሲሆን፣ ኤርሚያስ “አዎ፣ ግን …” እያለ የትህነግን በደለና ወንጀል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሲያጋራ ተስተውሏል። ይህ አካሄድ አዲስ ባይሆንም ኤርሚያስ አሁንም ሆን ብሎ የሚያደርገው እንደሆነ ከ360 አካባቢ ተሰምቷል።

ቀደም ሲል በስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለይቶ በማሳጣትና የትህነግን ሃጢያት ተካፋይ በማድረግ ተግባር ላይ ተሳትፎው የጎላ እንደሆነ የሚጠቀስለት 360፣ ከጀርባ ሆነው ከሚረዱት አጋሮቹ በተጨማሪ 360ን በገሃድ የሚደግፈው የመረጃ ቴሌቪዥን ባለቤት በቅርቡ ሚናቸውን ይለያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናግረዋል። “ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ከሆነ እንገባለን” ከሚል ድርጅትና የድርጅት አመራር ጋር ግንኙነት ካለው ሚዲያና አዘጋጆቹ ጋር የመረጃ ቲቪ ባለቤት ሚናቸውን ሳይለዩ የት ድረስ እንደሚዘልቁ ግራ የገባቸውም አሉ።


ጌታቸው ረዳ፤ አንሙት አብርሃምን በቅርቡ “ሰላም ስበክ ወንድም ዓለም” እንዳለው በማህበራዊ ገጹ ማንሸራሸሩን ያስታወሱ “ኤርሚያስ ከጌታቸው ጋር የስልክ ግንኙነት አለው መባሉ አያስገርምም” ባይ ናቸው።

አንሙት አብርሃም ቀደም ሲል ENN (ኢኤንኤን) በሚባለውና ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቦርድ እየመራው በነበረው የቴሌቪዥን ላይ ይሰራ የነበረ፣ አሁን የአማራ አክቲቪስት መሆኑን በይፋ ያስታወቀ ነው።


ሲያስረዱም “360 ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ይቀርቡ የነበሩት ፕሮግራሞች በሙሉ የትህነግ ሃሳብና ዓላማ ላይ የተቸከሉ ነበሩ። በተለይ ኤርሚያስ ሌላው ‘በረከት ስምዖን’ ነው ሲባል በጅምላ ሲጮሁ የነበሩ ይህ መረጃ አዲስ ይሆንባቸው ካልሆነ በቀር ለሌሎች ከድሮም ግልጽ ነበር” ብለዋል።

ኤርሚያስ “ከኦሮሚያ ዘርፋለች” ብሎ ለሰደባት ከተማ፣ በባለ አደራ ምክትል ሊቀመንበር የሆነላት እንደሆነ ያስታወሱ፣ ሃብታሙ በደረጃ ዝቅ ቢልም ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንደነበረው አይጠራጠሩም። ሆኖም ግን ትህነግ “ከአማራ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ወረራ ካካሄደ በኋላ ምክር ሰምቶ ወደ ቀልቡ መመለሱን በበጎ ተመክተዋል።

ሰኞና ማክሰኞ ብቻውን የቀረበው ኤርሚያስ ለገሰ ቃሊቲ አቃቂ መምህር እያለ ካድሬነትን ሲጀመር በመድረክ የትህነግ ታጋዮችን “ጀብድና ማንነት” እያነሳ ያለቅስ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት መምህራን ባለደረቦቹ ምስክርነት መስጠታቸው አይዘነጋም። በ1997 ምርጫ አፈ ቀላጤ ሆኖ ህዝብ ሲፈጅ ትህነግን ይከላከል እንደነበር በውል የሚታወስ ነው። ጀግና ብርቁ የሆነው ዲያስፖራ ሁሉን ረስቶ ያጨበጨበለት ኤርሚያስና የ360 ቀጣይ ግንኙነት ምን ሊሆን እንደሚችል ለጊዜው መረጃ የለም።

ጎልጉል የሰበሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው በሁለቱ የቀድሞ የትህነግ አገልጋዮች ላይ የሚሰጠው ሃሳብ የተለያየ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ እንዲህ ይላሉ፤ “የኤርሚያስ ለገሰና የሀብታሙ አያሌው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያላቸው አስተሳሰብ፤ ኤርሚያስ በእውቀትና በአርቆ አስተዋይነት አስተያየት የሚሰጥ ሲሆን ሀብታሙ ደግሞ የጥላቻና የእልህ ነው። ሀብታሙ ግራ ተጋብተዋል ህክምናና እረፍት ያስፈልገዋል”። እንዲህ ዓይነቶቹን የሚዲያ አስተያየቶችን በ360 ውስጥ ያሉት ሠራተኞች “ኤርሚያስ ቀድሞም ካድሬ ስለነበር የቀድሞውን ድርጅታዊ አሠራር ሥልት በመጠቀም የራሱን ሰዎች እያሰማራ እኛን ለማንኳሰስ የሚበትነው መረጃ” በማለት ለማጣጣል ሲሞክሩ ይደመጣሉ። ሆኖም ኤርሚያስ በሚያራምደው አቋም በርካታ ትህነጎች እንደሚደግፉት ከሚሰጡት አስተያየቶች ለመመልከት ይቻላል። በዚህ አፍራሽ አቋሙ ኤርሚያስ ከ360 እና ከሃብታሙ ጋር አንዴት እንደሚቀጥል በቀናት ውስጥ የሚታይ ይሆናል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics, Slider Tagged With: 360, ermias legesse, Ethio 360, habtmu ayalew

Reader Interactions

Comments

  1. አብርሃ says

    September 3, 2021 09:57 am at 9:57 am

    ልጉል
    በእውነቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማስተዋል ነገሮችን ግራ ቀኙን አይቶ የመረዳት የማገባዘብ ችሎታውን ምን ያክል ዝቅ አድርጋችሁ ብትገምቱ ነው እንደዚህ የምትዘላብዱት? ወይስ እንደ “ንጉሳችሁ” የኢትዮጵያ ሕዝብ short memory ነው ብላችሁ አምናችሁ ነው። ሁለቱም ስህተት ነው። አንድ እውነት ግን አለ እሱም “Stupid knowing the truth, seeing the truth, but still believing the lies” እንደዚህ አይነት የማስተዋል ችሎታቸው እጅግ የወረደ ሰዎች አሉ በውድ አገራችን ኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ግፍና በደል እያዩ እንዳላዩ ግፍ ፈጻሚውንና አስፈፃሚውን ሲሞካሹ የሚውሉ። ሕዝባችን ላይ ከቁስሉ ላይ ጨው የሚጨምሩ። እረ በሕግ አምላክ የሕዝብ ሰቆቃ ይሰማችሁ። ሰባዊነት የት ገባ በእውንቱ በወለጋ፣ በመተከል፣ በሀረር፣ ባአርሲ፣ ሻሸመኔ በአጣዬ በሌላውም በብሄራቸውና ሀይማኖታቸው ብቻ የሚስጨፈጭፋቸው የመለስ “ልጅ” የወያኔ/ኦነግ ሰላይና ካድሬ ወይስ የኢትዮጵያዊነት፣ የእውነትና የመርህ አርበኞች የግፉን ድምፅ የሆነው ሚዲያ ኢትዮ 360??? ወያኔን ጠፍታለች ዱቄት ሆናለች ሲል ሕዝባችን በአደባባይ አይኑን በጨው አጥቦ ዋሽቶና አዘናግቶ ያንድ ወገን ተኩስ አቁም በሚል ሰንካላ ምክንያት ወያኔ ተጠናክራ በአፋርና አማራ ወገኖቻችን ላይ ይህን ሁሉ ጭፍጨፋና ማፈናቀል እንደትፈጸም እያደረገ ያለው ያላቅሙና ያለ ችሎታው ኢትዮጵያ ታክል ታላቅ ሀገር እመራለሁ ብሎ እምዬ ምኒልክ ቤተመንግስት ገብቶ የውሸት ኢትዮጳዬ እያለ ግብሩና የእለት ተእለት ስራው ግን በተረኝነት ከወያኔ በከፋ ያንድን ጎሳ የበላይነት ለማንገስ ኢትዮጵያዊነት እየገደለ ያለው ማነው ኢትዮ 360 ኤርሚስ ነው ወስ ማን?? ንገሩና አንድ ነገር በእርግጠኝነት ልንገራችሁ ራሳችሁን እንጅ ማንንም አታታልሉም። ሕዝብ “Fool me once shame on you. Fool me twice shame on me.” ብሏል አይበገሬው እስክንድርና የትግል ጓዶቹ አዲስ አበባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባት እንድትሆን ባልደራስ ብለው ሰላምዊና ሕጋዊ ትግል ሲደርጉ ስሩ እየተገታተረ ግልጽ ጦርነት እንገባለን ብሎ ዝቶ አሁን በውሸት የሽብርተኝነት ክስ የሚሰቃቸው በማነው??? መለስ “ልጅ” ወይስ በእናንተ አባባል የበረከት “ልጅ” ኤርሚ የበረከት ወያኔ መንግስት እንክትክት ብሎ እንዲወድቅ የታገለ አሁንም የመለስ ዜናዊን ወራሽ ጠበቃ ሆኖ ያስቀጠለውን ኋላቀር የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ እንዲወገድና በምትኩም ሕዝብን ያማከለ ኢትዮፕይቂነት ያነገሰ እኩልነት ነጻነት የሚያጎናጽፍ ፍትዊ ስርአት እንዲመጣ ኢትዮ 360 ሚዲያን መስርተው ከባልደረቦቻቸው ጋር እየታገለ ያለ አርበኛ ነው ። አረጋዊውን የእውነት አርበኛ ጋሽ ታዲዎስ በእርጅና እውነት ስለተናገሩ ብቻ ታስረው እንዲንገታቱ እያደረገ ያለው ማነው?? ሌችም የሕዝብ ወገኖች እውነት ስለተናገሩ ስለፃፉ በእየስርቤቱ አበሳ የሚያዩትን ቤት ይቁጠራቸው። ሕዝብ ይህን ሁሉ ግፍና በደል የማያይና የማይሰማ የእናንተንና የመሰሎቻችሁን ቱልቱላ ብቻ የሚሰማ ይመስላችኋል? አብይ ከወያኔ/ኦነግ ጋር ሆኖ የሰራውን እልቆ መሳፍርት ወንጀል ሕዝብ ይቅር ብሎት ሳይመረጥ “መርጦት” በሚናገረው ብቻ ሕዝብ ወዶትና አምኖት አክብሮት አንግሶት ዳር እስከ ዳር ደግፎት ያን ሁሉ በካልቾ ብሎ የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ብሎ ካደገበት ከተፈጠረበት ጎሰኝነቱ ዘረኝነቱ ወርዶ ተወሸቀ። አሁን እናነተ ምን አድርጉ ብላችሁ ነው ሕዝብን ከግፍና መከራ ኢትዮጵያዊነትን ከጨርሶ መጥፋት ለመታደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን እየተጉ ያሉ ጀግኖቻችንና አረበኞቻችን ሰላምና እረፍት የምትነሱ?? ሕሊና ካላችሁ ለነፃነት ለፍትህና ለእኩልነት የሚደረውን ትግል አግዙ አለዚያ እባካችሁ ገለል በሉ። ነገ ሁሉም በሰራው በሕዝብና በአምላክ ፊት ለፍርድ ይቀርባል። ብቻ አምላከ ኢትዮጵያ ለሁላችንም እድሜ ይስጠን። የችግራችን ምንጭ የሆነውን “ሕገመንግስት aka ህገአራዊት” ሌላውን ሁሉ የጠቀመ ይመስል “ለአንድ ክልል ብለን አንቀይርም እያለ የሚያላግጠውስ እኮ ማነው??? ደግነቱ አሁን የጊዜ ጉዳይ እንጅ ሕዝባችን ማን እየገደለውና እያስገደለው እንዳለ የውሸት ኢትዮጵያዬ እያለ እያታለለው እንዳለ ማን ለነፃነትና ለሕልውናው በሚያደርገው ትግል አጋሩ እንደሆነ ጠንቅቆ አውቋል።
    ኢትዮፕያ በልጆቿ ትግል ወደ ጥንት ክብሯ ትመለሳለች!!!
    ጎሰኝነት ጎጠኝነት ከምድራችን ይወገዳል ኢትዮጵያዊነት ያብባል!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule