የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ (ትህነግ) ይመራው የነበረው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከትህነጉ አሸባሪ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ የካድሬ ቃል” ኤርሚያስ ሲጠቀም መቆየቱን የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል። መረጃውን ይፋ ያደረገው ኢትዮ 12 ነው። በ360 “ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሰሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ July 2, … [Read more...] about የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
360
“አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል። ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን … [Read more...] about “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ