የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
ermias
“አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል። ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን … [Read more...] about “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ