• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”

September 22, 2020 11:51 pm by Editor 8 Comments

የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል።  

ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር።  

አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ ስለ ዐቢይ አሕመድ የተናገረው እንዲያውም ጠቅላዩ እንዲወደዱ የሚያደርግ እንጂ እንዲጠሉ የሚያደርግ አይደለም። ያም ቢሆን ስዩም ተሾመ በየኔታ ትንታኔ ላይ እንዳቀረበው መረጃው፤

  • በወቅቱ አበበ በኢሣት ውስጥ ለሚገኙ ባልደረቦቹ በኢሜይል ልኮላቸው ነበር
  • በቃለምልልሱ ላይ ግለሰቡ ሲናገር እንደሚሰማው ኢንሳ ደግሞ የኢሣት ባልደረቦችን ኢሜይል እየበረገደ ይመለከት (ሃክ ያደርግ) ነበር
  • ስለዚህ መረጃው ኢንሳ ውስጥ ባሉ ሠራተኞች ዐቢይንም ጨምሮ የተሰማ ነው ለማለት ያስደፍራል
  • ግለሰቡ ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ የዳሽን አቪየሽን ሠራተኞችን ስለ ሮቦቲክስ ለማሰልጠን ተመልሶ ሲመጣ ተይዞ ታሰረ
  • በጌታቸው ሽፈራው የተጻፈው የሰቆቃ ድምጾች የሚለው መጽሐፍ ገጽ 117 ላይ ግለሰቡ በ2009ዓም ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ገልጾዋል፤ በመጽሐፉ ላይ ጌታቸው ሰለ ግለሰቡ ሲናገር፤
    • ስሙ ጸጋዬ ተክሉ እንደሚባል  
    • ለኢሣት የሰጠውን መረጃ በተመለከተ “ጉዳዬ በዝግ ችሎት ይታይ” ብሎ ፍርድቤቱ መጠየቁ
    • የድምጽ መረጃው ለፍርድ ቤት በኤግዚቢትነት መቅረቡን ይናገራል
  • ስለዚህ ኤርምያስ “ስለ ዶ/ር ዐቢይ አበበ የሚውቀው ምሥጢር” አለ ያውጣው እያለ ሲናገር የነበረው መረጃ፤
    • ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በፍርድ ቤት ዳኞች የታየ መሆኑ
    • ጠበቆች የሰሙት መሆኑ
    • ምናልባትም ከእነዚህ ሌላ ሰዎች የሰሙት እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል
  • ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ አበበ ገላው የድምጽ ማስረጃውን ወደ እንግሊዝኛ በመመለስ ለሒውማን ራይትስ ዎች በመላክ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቱ “They Know Everything We Do” በሚል ርዕስ ህወሓት በዜጎች ላይ ስለሚደርገው ስለላ ዳጎስ ያለ ሪፖርት ለማውጣት እንዲረዳው ግብዓት ሆኗል፤ ሪፖርቱም ላይ ለሕዝብ ይፋ ሆኗል

ስለዚህ ግለሰቡ በቃለምልልሱ ወቅት ስለ ዐቢይ አሕመድ የተናገረው በምንም መልኩ “የተደበቀ ምሥጢር” የሚያስብል ሳይሆን በርከት ያሉ ሰዎች የሚውቁት የአደባባይ ምሥጢር ነው። ኤርምያስም ይህንን ያውቃል። እንዲያውም የተቀረጸው ድምፅ እርሱም እጅ ስለሚገኝ እንዲያውጣው ከኢሣት ሰዎ ተነግሮት ነበር።

የኔታ ትዩብ ያወጣውን የድምጽ ቅጂ ከዚህ በታች አትመነዋል። 

ኤርምያስ በርካታ ችግሮች ያሉበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በሙሉ ልቡ በመደገፍ በርካታ ውዳሴ ዐቢይ በኢሣት ላይ ሲያሰማ ነበር። ጠቅላዩ 100 ቀናት ባጠናቀቁ ጊዜ እዚያው ኢሣት ላይ በሰጠው አስተያየት የመቶ ዓመት ሥራ ነው በመቶ ቀን የሠሩት ብሎ ነበር። ከዚህ በኋላ በምን “ሰርፕራይዝ” ያደርጉን ይሆን፤ በመቶ ቀን ከሚገባው በላይ አድርገውናል ብሎም ሲናገር ተደምጧ። ከዚህ ባለፈም ከእንግዲህ ዶ/ር ዐቢይ እንደ ክርስቶስ እግር በማጠብ የአገልጋይ መሪነት ማሳየት ብቻ ነው የቀራቸው ብሎ ከሚገባው በላይ አድንቋቸዋል።

ከዚህ ሁሉ ውዳሴ ዐቢይ በኋላ ኤርምያስ በዐቢይ ላይ ዘመቻ የከፈተበትን ለማወቅ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ከዚህ በፊት ያተምናቸውን ጽሁፎች ማንበቡ በቂ ምላሽ ይሰጣል። ጉዳዩ ሲጠቀለል ግን “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል” የሚለውን ብሒል በተግባር ያሳየ ሆኖ እናገኘዋለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Opinions Tagged With: abiy ahmed, ermias, ermias legesse, leaked audio

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    September 23, 2020 01:02 am at 1:02 am

    የጎልጉል ድህረ-ገፅ አዘጋጆች የአማርኛ ቋንቋ ችግር ያለባችሁ ይመስለኛል ፥ የከሃዲውና የዘረኛው አብይ አህመድ አሊ (በቀድሞው ስሙ አብዮት ካሳየ በላይነህ) በፋሽስቱ ህወሃት ሥር ሆኖ ከዚያ የበለጠ ወንጀል ምን ሊያደርግ ነበር ? ምሁራንን እያሳደደ ከሀገር ያባርር እንደነበርና እርሱ ያልመሰለውን ሁሉ ሲያሰልልና ሲያሳድድ የነበረ ዕኩይ ጉግማንጉግ ወንጀል አልሰራም ብላችሁ ስታስተባብሉ አለማፈራችሁ በጣም ይገርማል ! የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ይባላል ፥ ስዩም ተሾመ የተባለውን የአራጁና ነፍሰ-ገዳዩ አብይ አህመድ አሊ አፈ ቀላጤ ምስክርነት አቀረባችሁ ፥ በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሰ ብቻ ሳይሆን አያሌ ኢትዮጵያውያን አብይ አህመድ አሊን ሆ ! ብሎ ተቀብሎት ነበር ፥ ነገር ግን ሰውየው አፈ ቅቤ ግን ልበ ጩቤ ሆኖ ብቅ አለ ፥ ታዲያ ኤርምያስ ከእውነታው የወጣበት ምክንያቱ የት ላይ ይሆን ? ኤርምያስ ለገሰ የገዳዩንና አራጁን የአብይ አህመድ ገመና ግልጥልጥ አድርጎ በማውጣቱ ለአብይ ሎሌዎች ወይም አጨብጫቢዎች አልተመቻቸውም ፥ እበላ ባይና አፋሽ አጎንባሽ ባለበት ሀገር እውነት የለም ፥ ስዩም ተሾመ የአብይ ደንገጡር ነው ፥ ምክንያት ደመውዝ የሚከፍለው ስለሆነ የፈለገውን ቢል ማንም ሰሚ የለውም ፥ ጎልጉል ድህረ-ገፅ የአራጁና ገዳዩ ብሎም የኦሮቶዶክስና የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነው አብይ አህመድ አሊ ምርኮኞች ትመስላላችሁ ፥ እውነት የራቃችሁና ከዘመኑ ኦሮሙማ ፀረ-ኢትዮጵያ ከሆኑ የ16ኛው ክ/ዘመን ሰዎች ጋር የምትዘፍኑ መሆናችሁን እየተረዳሁ ነው ፥ ሞት ለኦሮሙማ ዘረኞችና ሎሌዎቻቸው ይሁን ።

    Reply
    • Makonnen T says

      September 23, 2020 07:24 am at 7:24 am

      ከላይ የተጠቀስው አስተያየት ትክክልና እውነተኛ ነው:: ግን እናንተ የድረገፁ አዘጋቾች በጣም በሚገርም ሁናቴ የዘረኛው የዓብይ ደጋፊዎች መሆናችሁን በግልፀ ያሳያል::
      ኤርሚያስ እውነተኛ ንጹህ ኢትዩጵያዊ ለእውነት የቆመ ስው ነው!
      ይህንን ዐፍረተ ቢስ ዜና ብላችሁ ማውጣታችሁ እናንተንም ያሳፍራል ወይም የዓብይ መፅዋት ተቀባይ ናችሁ:: ወደፊትም ቢሆን የዓብይን የዘርኝነት ጠባይ ብታጋልጡ እውነት ለኢትዬጲያ ህዝብ በተለይም ለታረደው ለአማራ ህዝብ ጉን መቆማችሁን
      ማሳየት ይኖርባችሆል::

      Reply
  2. ናጋሮ says

    September 23, 2020 07:43 am at 7:43 am

    አማራነት እንደማይጠፋ ሁሉ ኦሮሙማም አይጠፋም:: የማንም ማንነት አይጠፋም:: ዘረኝነት (እኔ እበልጣለሁ) ግን ይጥፋ!

    Reply
  3. Tekola says

    September 23, 2020 08:45 am at 8:45 am

    Ermias is not a politician, and can not be. Not before, not now, and not in the future. He does not have the a, b, c, of politics.

    Reply
  4. kemil says

    September 23, 2020 05:58 pm at 5:58 pm

    enante mesemat yemtifeligut yand behaare yebelayinet newu. yihe demo aktimoale yalefe yareje astesaseb newu. so we dont need old regime(fewdalizem) ok. bezihm bezah ewunetan lehizeb yifa mareg ye abiy degafi ayasegnim. mekeneyatum enante mesemate yemitefeligut yemitodutin bicha silehone. primitive huala kere astesaseb demo rasin, batesebin, bilom, hagerin yigodale. so, ewunetaw ethiopia ye bizu beharoch ena yebizu haymanotoch balebate hona sale yandu behare ena haymanot bicha endinore maseb memegnet tenegna asetesaseb aymeselegnime. degmo abiy ayfokerem bifokerem yaregewal so sereto masayet newu… we love our leader abiy and we support him.

    Reply
  5. ሚኪ says

    September 24, 2020 03:28 pm at 3:28 pm

    ኤርሚያስ ለገሰ አውርቶ አደር መሆኑን አትርሱ!

    Reply
  6. Lema says

    September 27, 2020 04:25 am at 4:25 am

    It is true that Ermias and the likes makes their bread by making happy their pay masters.
    The rate depends on the amount of talks they make every day that occurred to be boring even for themselves like Minalachew. They always go to pick negatives among the heapes of many positives that seems to be against their conscious.

    Reply
  7. Assefa says

    October 3, 2020 07:06 am at 7:06 am

    እንደኔ ጥሩ አቋም ወይም ጥሩ አስታራቂ ሃሳብ የምለው፤ ዛሬ ግለሰቡ ምን እየሰራ ነው? ጠቃሚ ወይስ ጎጂ? ብሎ በመገምገም አስፈላጊውን አስተያየት መስተጥ ነው፡ ከዚያ ባለፈ ከወያኔ ጋር እብሮ የስራ ከነበረ ማንኛውም ሰው ጥፋት ወይም መውቀሻ ጉድይ አላገኝም ብሎ ማሰብ ከንቱ ድካም ነው። ምከንያቱም ወያኔ የጥፋት ሃይል ነው፤ አገልጋዮቹም የግድ የዚሁ ጥፋት ሃይል ሥራ አሥፈጻሚ ወይም ፈጻሚ ሳይሆኑ አብረው ሊሄዱ ስለማይችሉ፤ ግልጽ በሆነ ጉዳይ ላይ መነታረክ አስፈላጊ አይደለም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule