በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል።
ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን በእስር ላይ የሚገኘው በረከት ስምዖን መ/ቤት አደረሱት። በሚመለመልበት ጊዜ ምን ሆኖ ያለቅስ እንደነበር ሲጠየቅ የመለሰውም ከላይ የተባለው የታጋዮቹ ማንነት እንደሆነ ተናግሯል። ምናልባት ድብቅ መረጃዎችን የሚያጋልጠው ስዩም ተሸመ ከእኔ የበለጠ መረጃ ካለው ጀባ ሊል ይችላል።
በዚህ ዓይነት ራሱን ከጥቅም ጋር በማቆራኘት የፈለገውን ሲያደርግ የኖረው ኤርሚያስ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ መንግሥት ላይ በኢህአዴግ/ህወሓት ዘመን የተማረውን የሤራ ፖለቲካ በ360 ሚዲያ ላይ በየቀኑ እየተናገረ አገር በማፍረስ ተግባር ላይ ይገኛል።
በነገራችን ላይ 360 በገንዘብ ከደጎሙትና ከሚደጉሙት አገር አፍራሾች መካከል እነማን እንዳሉበት አንዳንድ መረጃዎች አሉ። ለዛሬ በይደር ይቆይ።
ከዚህ ሌላ ግን ኤርሚያስ ከቴዎድሮስ ጋር በዚሁ 360 ላይ ቀርቦ ሳየው አዘንኩ። ያዘንኩት በኤርሚያስ የካድሬነት ባህርይ ሳይሆን ቴዎድሮስ ማን እንደሆነ ጠንቅቆ እያወቀ ከእርሱ ጋር አብሮ በመሰለፉ ነው። ቴዎድሮስ አዲስ አበባ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ከወላዋይና እጅግ መሰሪ ባህርዩ በተጨማሪ ተፈጥሮ የነሳቸው ትልቅ ነገር ስላለ በዚያ ላይ ለመጨመር ብዙም አልፈልግም። ነገር ግን በቴዎድሮስ ባህርይ እጅግ ያዘኑት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በፌስቡክ ገጻቸው የጻፉትን የሐዘንና የምክር መልዕክት አንባቢያን ሄደው እንዲያነቡት እጋብዛለሁ።
ኤርሚያስ በአዲስ አበባ ላይ የነበረው አመለካከት ምን እንደነበር አውቅ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከስዩም ተሾመ ጋር ተናጅሶ ከእኔ በበለጠ የመጻፍና የማቀናበር ብቃት ስዩም ያወጣውን መረጃ እዚህ ላይ ለመድገም ተገድጃለሁ።
ይድረስ ለአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ‼
አቶ ኤርሚያስ ለገሰ (Ermias Legesse Wakjira) ትላንት ከቴድሮስ ፀጋዬ ጋር Ethio 360 Media ላይ ባደረጉት ውይይት እኔን በስም በመጥራት “እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ቡድን አካል እንደሆንኩ ተናግሯል። ከዚህ በተጨማሪ በመረጃና እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የዶ/ር አብይ ጭፍን ደጋፊ እንደሆንኩ በይፋ ተናግሯል። ያው እንደምታውቁት የዚያች ሚጥሚጣ (መኪና) ነገር ብዙ ጣጣ ይዞ መጥቷል።
የመጀመሪያው እንደ ኤርሚያስ ላሉ ሰዎች ወሬ ለመጠረቅ ያመቻቸዋል፣ ሁለተኛው ደግሞ ቀሪውን ሂሳብ መክፈል ተስኖኛል። ይሄው ትላንትና ደሞወዜን ሙጥጥ አድርጌ ከፍዬም ገና 15ሺህ ዕዳ ይቀርብኛል። ይህን ለመክፈል ደግሞ ምን እንዳደረኩ Ben Abera ብትጠይቁት ይነግራችኋል። ስለዚህ አቶ ኤርሚያስ እንደዛሬው ሳይሆን ቀድሞ የነበረንን ወዳጅነት አስበህ ቀሪውን ብትከፍልልኝ መልካም ነው። በዚህ መልኩ የእኔን ስም በማጥፋት የሰራኸው ቪዲዮ ብቻ በትንሹ $500 ዶላር ያስገኛል። እሱን ብትልክልኝ ይበቃኛል።
ወደ ዋናው ነጥብ ልመለስና፤ ኤርሚያስ በዚህ ልክ የወረደ ነገር የተናገረው ተበሳጭቶ ነው። ያበሳጨሁት ደግሞ አንዴ በአሽሙር፣ ሌላ ግዜ ደግሞ ስሙን በመጥቀስ ስለፃፍኩበት ነው። ባለፈው “በማን የሚመራው ቄሮ በሽብርተኝነት ሊፈረጅ ይገባል?” የሚል ነገር ለጥፎ ስመለከት “OMG” ብዬ ኮሜንት አደረኩለት። በውስጥ መስመር መጥቶ “ፅሁፉ ምን ችግር አለው?” አለኝ። እኔም “ቄሮ ማለት ሁሉም ወጣት የኦሮሞ ወጣት ነው። አንድን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ ማሰብ በራሱ እብደት ነው” ብዬው ነበር። ነገር ግን ልንግባባ አልቻልንም።
በመጨረሻ “የፀረ ሽብር” አዋጁ ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ተሳታፊ እንደነበር በመጥቀስ ከላይ ለጠየቀው ጥያቄ መልሱን ታውቃለህ ብዬ ነቆርኩት። ቀጠለና የኤርሚያስ ስም ሳልጠቅስ ታከለ ኡማ ስልክ ደውሎ ስልጣን ለምኖ ሲያጣ ቀንደኛ ተቃዋሚና የባልደራስ ምክትል እንደሆነ በመጠቆም ሾጥ አረኩት። ነገር ግን ስሙ ስላልተጠቀሰ እሱ መሆኑን የሚያውቁት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። ይሁን እንጂ እነ ኤርሚያስ አሁን ባሉበት ሁኔታ ፀብ በደላላ እየፈለጉ ነው። ስሙን ሳልጠቅስ በታናገርኩት ተናድዶ “ስዩም ተሾመ” እያለ በስም ጠቅሶ ሞልጮኛል። እኔ ለራሴ ዛቻና ማስፈራሪያ ይመቸኛል! ስድብና ስም ማጥፋት ይደላኛል።
ኤርሚያስ ስለ እኔ በተናገረው ነገር በጣም እርግጠኛ እንደሆነ ከማንም ጋር ፊት ለፊት ለመከራከር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። አሁን የምጠይቀው፤ 1ኛ) በተናገርከው መሰረት ከእኔ ጋር ክርክር ትገጥማለህ? 2ኛ) አንተ እንደፈለክ ዘርጥጠኝ፣ እኔም እንደፈለኩ ልዘርጥጥህና ተላልጠን ይዋጣልን? ወይስ 3ኛ) በድፍረት ስሜን ስላጠፋህ ይቅርታ ትጠይቀኛለህ? ወዳጄ ልቤ ሆይ፣ ሦስቱም አማራጮች ለእኔ ልዩነት የላቸውም። ስለዚህ የሚበጅህን መርጠህ ታሳውቀኝ ዘንድ እልምንሃለሁ።
ከሠላምታ ጋር፤
ስዩም ተሾመ፤ ስዩመ እግዚያብሔር ዘ-ይምነገደ ኢትዮጵያ
ስም ይህንን ከጻፈ በኋላ ከኤርሚያስ ምላሽ ማግኘቱን ባላውቅም የሚከተለውን መረጃ አተመ፤ ይህ መረጃ በማንበብ ብቻ የኤርሚያስን ማንነት ለመናገር ይቻላል፤ ከላይ እንዳልኩት ይህ የኤርሚያስ አቋም በምንም ዓይነት መስፈርት ከእስክንድር ነጋ ጋር የባልደራስ ምክትል መሆን የሚያስችለው ሳይሆን ከጃዋር ጋር እንዲቆም ወይም መቆም እንዳለበት ግልጽ ማስረጃ የሚሰጥ ነው። እኔ በግሌ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም አላት ምናምን የሚባለውን እንደማልቀበል ራሱ ኤርሚያስ ያውቃል፤ ነገር ግን ኤርሚያስ ይህንን ጉድ ተሸክሞ በምን መስፈርት እነ ታከለ ዑማን፣ እነ ለማ መገርሳን፣ እነ ዐቢይ አሕመድን ተረኛና ኦሮሞ እያለ እንደሚከሳቸው ለራሱም የሚያሳፍረው ይመስለኛል፤ የስዩም ተሸመ ጽሁፍ እንዲህ ይነበባል፤
“ዓሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል ቁ.1” ለኤርሚያስ ለገሰ
ቆይ ቆይ… አቶ ኤርሚያስ ለገሰ (Ermias Legesse Wakjira) የባልደራሱ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ነው። ባለፈው አመት የባልደራስ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢና መስራች ከሆነው አቶ እስክንድር ነጋ ጋር ነፃ ውይይት ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ቀርቦ “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ላይ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለውም፤ ‘ልዩ ጥቅም’ የሚለው እሳቤ በራሱ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ የተጋረጠ የዘር/ብሔር መድልዎ ነው” በሚል ሃሳብ አቅርቧል። በእርግጥ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ዙሪያ ያለኝን አቋም በፅሁፍና ቃለምልልስ በተደጋጋሚ ገልጬያለሁ። በተመሣሣይ አቶ እስክንድር ነጋ “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም አለው” የሚለውን እሳቤ አምርሮ እንደሚቃወም የታወቀ ነው። እኔም ሆንኩ እስክንድር በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን አቋም የዚህ ፅሁፍ ትኩረት አይደለም። ከዚያ ይልቅ የፅሁፉ ዋና ትኩረት “ከቅርብ ግዜ ወዲህ የባልደራስ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ያለው አቋም ምንድነው?” የሚለው ነው።
ንግግሩን ቃል በቃል ባላስታውስም፣ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የባልደራስ ምክትል ከመሆኑ ቀደም ብሎ “እናቴ ስትኖር አዲስ አበቤ፣ ስትሞት ደግሞ ኦሮሞ እንድትሆን አልፈልግም!” ማለቱ አይዘነጋም። ከዚህ አንፃር “የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለው ልዩ ጥቅም ሊከበርለት ይገባል” የሚለውን እሳቤ አምርሮ እንደሚቃወም መገመት ይቻላል። ነገር ግን ወደኋላ ሸርተት ብለን እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም የኦሮሞ ጥናት ማህበር (Oromo Studies Association – OSA) ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተናገረውን ስንመለከት ደግሞ ናላችን ይዞራል። በዚህ መድረክ ላይ ኤርሚያስ ቃል በቃል “ኮተቤ፥ አቃቂ፥ ካራቆሬ፥… የአዲስ አበባ አይደሉም” በማለት ይናገራል። (ይሄን ጉድ ለመስማት የቸኮለ እዚህ ቪዲዮ ላይ ከ8:00 ደቂቃ ጀምሮ ይመልከት)።
በእርግጥ ለእኔ ወያኔ ለዘረፋ ሲል የሰራው ተንኮል እንጂ አዲስ አበባ የኦሮሚያ፣ ኦሮሚያም የአዲስ አበባ እንደሆነ አምናለሁ። ነገር ግን “የአዲስ አበባ ከተማ አሁን ካላት 54ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ የከተማዋ ትክክለኛ ይዞታ የሆነው 21ሺህ ሄክታር ነው” የሚለው ኤርሚያስ እንዴት የባልደራስ ምክትል የሆነው? “ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም!” ከሚለው እስክንድር ነጋ ጋር እንዴትና በምን ቋንቋ ተነጋግረው ነው የተግባቡት? አቶ ኤርሚያስን የባልደራስ ምክትል ሰብሳቢ የሆነው በአዲስ አበባ ስር የተጠቃለሉ የኦሮሚያ መሬቶችን ለማስመለስ ነው ወይስ በውስጡ ያለው የስልጣን ጥማት ህሊናውን ስለጋረደው?
በመጨረሻም ይህን የፃፍኩት የኤርሚያስን ክብርና ዝና ለመንካት አይደለም። ከዚያ ይልቅ “ዝም ብለህ የሰው አናት ላይ ፊጥ አትበል! በቅድሚያ ራስህን መርምርና ከህሊናህ ታረቅ። ይሄን ተምሬያለሁ።፣ ያንን አስተምሬያለሁ ከማለት ይልቅ በሰከነ አዕምሮ ለማሰብ ሞክር፣ በምክንያትና ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ወጥ አቋም፣ ከግል ፍላጎትና እልህ የፀዳ አመለካከት ይኑርህ” ለማለት ያህል ነው!
እኔም ይህንን ብዬ ላብቃ፤ ኤርሚያስ በደንብ አድርገህ ታውቀኛለህ፤ በአጻጻፌም እንድታውቀኝ አድርጌአለሁ፤ እየሄድክበት ያለው መንገድ የጨለማ ነው፤ ታከለ ዑማ ስለዘጋህ ዶ/ር ዐቢይን በጭፍን በመቃወም እየሄድከበት ያለው መንገድ ከእነቴዎድሮስ ጋር እንድታብር እያደረገህ ነውና ንቃ! አልረፈደም ተመለስ! ካልፈለግህ ትራምፕን ለመጣል በወሰድከው የአሜሪካ ዜግነት ተጠቅመህ “የትራምፕ ልቃቂት” የመሳሰሉ ጽሁፎች በእንግሊዝኛ እየጻፍክ የዜግነት ድርሻህን ብትወጣ እመክርሃለሁ።
በጣም ስለምታውቀኝ ስሜን አልጠቅስልህም 🙂
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
ስሜን አልጠቅስልህም says
ጎልጉል?
የዕውነት “ካው ቦይ” ጋዜጠኝነታችሁ እየተገለጠ ነው፤ ኤርሚያስ እንዲህ አለ፤ ስዩም እንዲያ አለው፤ እስክንድር ምን ይላል፤ ቴዎድሮስ ምን መለሰለት – ይሄ ዜና ነው? ተራ ስም ማጥፋት ነው! የወስጥ ልብስና ግልገል ሱሪያቸውን በአደባባይ አጥቦ ማስጣት ተለምዷ ጎልጉልም ይተባበራል – ሕዝብ ተጨባጭ ዕውነተኛ ዜና ነው መስማትና ማንበብ የሚፈልገው እንጂ ይህን ሃሜትና ጉንጭ አልፋ ቀደዳ አደለም
ለመሆኑ ይህ ምን ማለት ይሆን? መረጃ አለኝ ግን ይቆይ፤ ዕንቁልልጭ ነው?
“በነገራችን ላይ 360 በገንዘብ ከደጎሙትና ከሚደጉሙት አገር አፍራሾች መካከል እነማን እንዳሉበት አንዳንድ መረጃዎች አሉ። ለዛሬ በይደር ይቆይ።”
name says
Ewww.. How is this article anything more than gossip? Top to bottom “alu`balta”. I suppose this is what happens when technology is fallen under wrong hands. Sad..
wolde says
betam yasazinal. Endih aynet yetechemaleke hateta.
Hale says
Alubaltegnoch lekas zibazinke new yemtawerut kkk ye Ermin yegir etabi athonum ye Abiy mirkognoch
George says
you are rubbish no. 1 !!!!!!!!!