• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር

March 10, 2026 09:24 am by Editor Leave a Comment

ጎንደር ወዴየት እየሄደች ነው? ጎንደር እስከመቼ በውሸት ሪፖርት ትደበቃለች? መቼ ነው በጎንደር የጃኖ ስጦታ እና የዶሮ ፖለቲካ የተሸፈነችበት ጭምብል የሚገለጠው? ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ ያሻዋል።

የጎንደር የፖለቲካ አመራር ራሳቸውን ለሥራ ያተጉ፣ ተግባራቸውን በወቅቱ የሚከወኑ ለመምሰል የሚያሳዩትን ድራማ እስከመቼ ነው የሚገፉበት? እስከመቼ ነው ዝምስ የሚባሉት?

ጎንደር ለሚመጡ ባለሥልጣናት የባሕል አልባሳትን በማልበስና የጎንደርን ዶሮ በመጋብዝ ታታሪ መምሰል፣ ከዚያም በላይ “ወደ ቤት የምትወሰዱት” በማለት በአገልግል ዶሮ፣ በጀሪካ ቅቤና ማር እየሞሉ ውለታ ማስቀመጥ ፖለቲካ ሳይሆን፣ አድሮ መንግሥትን ዋጋ የማስከፈል ጉዳይ እንደሆነ እንዴት ይዘነጋል?

መቼ ነው የጎንደር ባለሥልጣናት ከጃኖ ስጦታና አገልግል ቋጠራ የውለታ ፖለቲካ በመውጣት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ በቅጡ የሚመሩት? የሚጠብቁት? ያለ ስጋት እንዲኖር የሚያደርጉት?

ሙስሊም ክርስቲያን ሳይል ከመንግሥት ጎን የቆመ ሕዝብ በአስተዳደር ድክመት ለምን መከራ ያያል? ከውስጥ ሆነው በጥቅም ትሥሥርና ሚሊሻ ጨምሮ በስሙ ከሸፈቱ ጋር ውስጥ ሆነው ሽፋን በመስጠት ንጹሐን እንዲገደሉ የሚደረገው እስከመቼ ነው።

ከትላንት በስቲያ በጎንደር ኡስታዝ መሐመድ ዘይኑ ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ የአንድ የሙስሊም ሞት ተደርጎ የሚታይ አይደለም። ይልቁኑም አብሮ በሚበላ፣ በሚጠጣና በማኅበራዊ ሕይወቱ ከቶውንም የማይነጣጠለውን የሙስሊምና የክርስቲያን ማኅበረሰብ ለማጋደል የተደረገ ሤራ ነው።

ከዛሬ አምስት 5 ዓመት በፊት በሁለቱ ዕምነት ተከታዮች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል ከፈቱት መካከል እኚሁ አሁን የተገደሉት ኡስታዝ ቀዳሚው ናቸው። ቁርሾ እንዳይኖር፣ ትክክለኛ ዕርቅ እንዲወርድ ትልቁን ሥራ የፈጸሙት መልካም ሰው ኡስታዝ ግድያን ከተራ ዝርፊያ ጋር ማገናኘት እናንተ በጃኖና በዶሮ ወጥ ስጦታ የምትታወቁትን አመራሮች ነጻ አያደርጋችሁም።

ደግነቱ በሁሉ ሕዝብ እገሌ ከእገሌ ሳይባል፣ ቀብራቸው ላይ በመገኘት የዶሮ ፖለቲካ ለሚጫወቱት ሁሉ፣ በጨዋ ደንብ ትምህርት ሰጥቷቸዋል። ለኡስታዝ ነፍስ ይማር እያልኩ መንግሥት ከሰማ የሚከተለውን ለማለት እወዳለሁ።

አድማጭ፣ የሚሰማ መሪ ከተገኘ፣ ብልጽግና ሆይ እባክህ ሁሉንም ነገር በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉና በዝረፊያ የካበቱትን የዶሮ ፖለቲካ ዥዋዠዌ ተጫዋቾችን አጥራ። በርካታ የሚነሱ ጉዳዮች አሉና ጥልቅ ማጣራት ተደርጎ ጎንደርን የማጽዳት ሥራ እንዲሠራ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

የከተማዋን ፖለቲካዊና ኤኮኖሚዊ ተግዳሮቶች አቻችለውና አሳልጠው ይመራሉ የተባሉ አመራሮች ሕልማቸው ወሳኝ የገቢያ ማዕከሎች በኮሪደር ስም በማስተከል ወንድምና እህቶቻቸውን አደራጅቶ ማስገባት ሆኗል። ይህ ነው ሕዝብን ተጠቃሚ አድርገናል እየተባለ በጃኖና ዶሮ ፖለቲካ ታጅቦ የቅጥፈት ሪፖርት የሚቀርበበት ሐቅ።

አንዳንድ ባለሃብቶችን ጽንፈኛ ነህ ብሎ በማሰር ገንዘብ መቀበል፣ ገንዘብ ተቀብሎ መልቀቅ፣ በመንግሥት ድጋፍና መዋጮ ሰበብ ራሰን ማበልጸግ የተለመደ ባሕል ሆኗል።

ግድያን ማጥፋት፣ ሰላምን ማስፈንና ሕዝብ በእርጋታ እንዲኖር ማድረግ ጉዳያቸው ስላልሆነ ነገም ከነገ ወዲያም በተመሳሳይ መልኩ ግድያው ላለመቀጠሉ ዋስትና የለም። እኛም “እገሌ መልካም ሰው ነበር” ብለን ከንፈር ከመምጠጥ ውጪ አማራጭ አይኖረንም።

ዛሬ ላይ የተገደሉት የሃይማኖት መሪ ቀደም ሲል ተለኩሶ የጠፋው እሳት ዳግም ማቀጠጠያ ክብሪት ናቸው። ትላንት የነበረውን ቁርሾ እንደያጠፋ ታቅዷል። ድርጊቱ በዕቅድ የተከነወነ ተግባር ነው። ዓላማው በሁለቱ ሃይማኖቶች ምዕመን መካከል ግጭት በመፈጠር  ከተማውን ለዝርፊያ ማዘጋጀት ነው።

አሥራ አንድ ምዕመን ሞባይል ብቻ በመዘረፉ መምህሩን ነጥሎ መግደል ዓላማው ግልፅና የማያሻማ ነው። የዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂዎች በአገልግል ዶሮ ፖለቲካ ሚኒስትር ለመሆን የሚሽቀዳደሙት የመዋቅሩ አካላት እንጂ ሌላ ማንም አይደለም።

መንግሥት ሆይ! ይህ የመጨረሻ የማንቂያ ደወል ይሁን። ይህን ጉዳይ ከሥሩ ማጽዳት ለነገ ሊባል አይገባም። ይህ ጉዳይ ከሥሩ ካልተበረበረና ተመሳስሎ የተሰገሰገው የውሰጥ አመራር ካልተፈተሸ ሀገር የጃርት መዋያ መሆኗ አይቀርም።

ጎንደር በብዙ ፈተናዎች ተፈትና አልፋለች። የጎንደር ልባም ሕዝብ ሁሉንም መከራ እንደ አመጣጡ አሳልፏል። ይህ የሚያማቸው እያደር የጥፋት ድግሳቸውን ከዶሮ ፖለቲከኞች ጋር ሆነው ይደግሳሉ። ዛሬ ጎንደር ስስ በሆነችበት ሃይማኖት ጉዳይ ነገር በማቀጣጠል ውድቀትን ማፋጠን እንደ ሀገር አይጠቅምም።

እነዚህ አዝማሪ ደርድረው፣ የባሕል ልብሰ አልብሰው፣ ዶሮ ጋብዘው፣ ዶሮ በአገልግል፣ ማር እና ቅቤ በጀሪካን የሚሸከሙት የመንግሥት ባለሥልጣናት እውነት ለምን ይህ ችግር ተፈጠረ? እስከ አሁንስ ለምን ጊዜ እየጠበቀ ያመረቅዛል? ብለው ይፈትሹ። እውነታው የውሸት ሪፖርት እና በዶሮ ፖለቲካ ሚኒስትር የመሆን ሕልም ውጤት ሆኖ ታገኙታላችሁ!!

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Opinions, Politics Tagged With: Doro Wot, gondar, Jano, ዶሮ, ጃኖ

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule