• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ”

March 27, 2026 09:14 am by Editor Leave a Comment

መነሻውን አማራ ክልል በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ለሽብር ዓላማ ሊውል የነበረ ሕገ ወጥ ጠመንጃና ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

መነሻውን ከአማራ ክልል ያደረገ ኮድ 3 አ.አ ታርጋ ቁጥር 05299 የሆነ ተሽከርካሪ ሕግ ወጥ 08 ክላሽ፣ 151 የክላሽ ጥይት፣ 17 የብሬን ጥይት እና 07 የክላሽ ካዝና ጭኖ በድብቅ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማሳለፍ ሲሞክር ለገጣፎ ኬላ ላይ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በተመሳሳይ መነሻውን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ያደረገ ኮድ 3 ኢት የታርጋ ቁጥሩ 55426 የሆነ ተሽከርካሪ በእንቁላል ካርቶን ውስጥ 988 የክላሽ ጥይት ደብቆ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማሳለፍ ሲሞክር በሱልልታ ኬላ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጠንካራ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ የተሰጠውን ግዳጅ በታማኝነትና በቁርጣኝነት በመወጣት የሀገርን ሰላምና ደኅንነት እያስከበረ የሕገ-ወጦች እኩይ ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ የበኩሉን ድርሻ በጀግንነት እየተወጣ እንደሆነ ገልጾዋል።

በውጭ ሀገር የሚገኙና ለሻዕቢያ ደፋ ቀና እያሉ የሚሠሩ ባንዳዎች ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ሀገሪቱን መበጥበጥ አለብን በሚል መመሪያ መቀበላቸው በስፋት እየተሰማ ነው። በነአምን ዘለቀ አስተባባሪነት ልደቱ አያሌውና መሰሎቹ የሚሳተፉበት የትርምስ ኮሚቴ ተመሥርቶ አንድ ደረጃ ላይ ለመድረስ እየታተረ ነው። አካሄዱ እንዲህ ነው፤…

በሰላማዊ ትግል ሽፋን ከውጪ በሰልፍና በፕሮፓጋንዳ ለመሥራት፤ ከውስጥ ደግሞ ከፋኖም፣ ከሸኔም ጋር በመሆን ነውጥ መፍጠርና ለምርጫው ምቹና አስቻይ ሁኔታ አልተፈጠረም በሚል ፓርቲዎቹ ከምርጫ ራሳቸውን እንዲያገልሉ፤ በመጨረሻም ምርጫው ያለ ሕዝብ ውክልና የሚካሄድ ነው በሚል ቅቡልነትና ሕጋዊ እንዳይኖረው የማድረግ ዘመቻ ነው። ለዚህም እንዲያግዝ የሸኔው ተወካይ በስብሰባቸው መገኘቱን በጥምረት መሥራት መጀመራቸውን ጎልጉል ዘግቦ ነበር።

ሻዕቢያ የሰጠው መመሪያ ምርጫውን ሕገወጥ አድርጉት የሚል ነው። ይህንንም ዘመቻ ለማስፈጸም በዳያስፖራ ያሉት ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቡድኖች፣ ድርጅቶች፣ ስብስቦች፣ የቤተሰብ ዕድሮችና ዕቁቦች የሚመስሉ ሁሉ እንዲሳተፉ እነ ነዓምን ከጀርባ ሆነው እየተጉ ነው። በሰብዓዊ መብት ስም ድርጅት የሚመራው ያሬድ ኃይለማርያምም ስብሰባዎችን በመምራትና የነዓምንን ትዕዛዝ በማስፈጸም ላይ ይገኛል። ልደቱም ወደኛ ቀረብ በል ተብሎ ከሚኖርበት አትላንታ ወደ ዲሲ አካባቢ እንዲመጣ በነዓምን ተደርጓል።

በሀገር ውስጥ ግድያዎችን ማካሄድ፤ ንጹሐንን በግፍ መረሸን፤ የሃይማኖት የሚመስል ግጭት መፍጠር፤ ወዘተ የዕቅዱ አንዱና ዋነኛ አካል ነው። ለዚህም ሥራ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሰው አሸባሪ (ደረጃ ሦስት) ፋኖ እና አራጁ ሸኔ የገፊና ጎታች ነውጡን ለማፋፋም ተጋብዘዋል። ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ የተላከው መሣሪያና ጥይት የዚሁ ዘመቻ አንዱ አካል ሆኖ ሊታይ የሚገባው ነው።

አንዳንድ ተጣምረናል፤ ምርጫ እንሳተፋለን ያሉ ፓርቲዎች አስቻይ ሁኔታዎች የሉም፤ በዚሁ ከቀጠለ ከምርጫው ለመውጣ እንገደዳለን ሲሉ ሰሞኑን የተደመጡት ከግብፅ በሻዕቢያ አድርጎ ከዳያስፖራ የተላከላቸውን መመሪያ በትዕዛዙ መሠረት ሲያስፈጽሙ ነው። ይህ ሁሉ ከዚህ በፊት ጎልጉል በስፋት እንደዘገበው የገፊና ጎታች ፕሮፓጋንዳ አካሄድ ስልት ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ 

Filed Under: Left Column, Literature, News Tagged With: ethiopian terrorists, lidetu ayalew, Neamin, operation dismantle tplf, Pull and Push Conspiracy

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule