ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤ “ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”። ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን … [Read more...] about “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
ermias legesse
ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
ኤርሚያስ ቃል በቃል የተናገረው ይህንን ነው፤ “ቲዲኤፍን (ስሙን የቀየረውንና በሃሺሽ ያበደውን የትህነግ ጭፍራ ማለቱ ነው) ምሳሌ ውሰዱ፤ የትግራይ ቲዲኤፍ ሕዝባዊ ኃይል ነው፤ (እነርሱ) ሳይነጋገሩ አይወስኑም፤ እንደ ቤስት ፕራክቲስ ነው የሚወሰደው፤ እደግመዋለሁ ቤስት ፕራክቲስ ነው”። ለአማራ ህዝብ እንዲተገብረው የሰጠው “ምክር” ይህንን ነው። በሌላ አነጋገር ኤርሚያስ እያለ ያለው፤ አገኘሁ ተሻገር ደብረጽዮንን፤ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ፃድቃንን፤ ጄ/ል አዳምነህ መንግሥቴ ታደሰ ወረደን ወይም ምዕግበን፤ ግዛቸው ሙሉነህ ደግሞ ጌታቸው ረዳን መሆን አለባቸው ነው። “የህወሃት አገልጋይ” በሚል ልዩ መለያው የሚታወቅው፣ በበረከት ስምዖን አስተምህሮ ተቀርጾ የተሠራ የሚባለውና ከዚሁ ፈጣሪው ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንደነበረው በርካታ መረጃ የሚቀርብበት ኤርሚያስ ለገሠ፤ በአበበ ገላው … [Read more...] about ለኤርሚያስ ክስ ትህነግ ወጪውን ሊሸፍን ነው
እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
እነ ኤርሚያስ ለገሰ አርብ ምሽት አንድ ፕሮግራም ሰርተዋል። በዚህ ፕሮግራም ዋና ሀሳባቸው አማራ ክልል ላይ አዲስ መንግስት መመስረት የለበትም የሚል ነው። በፕሮግራሙ: 1) አማራ ክልል ላይ ጭካኔና ውድመት እየፈፀመ ያለውን የትግሬ ወራሪ ኃይል TDF እያለ የትግሬ ወራሪ ራሱን የሚጠራበትን ይፋዊ ስሙ አድርጎ፣ ይህ ቡድን ምርጥ ተሞክሮ እንደሆነ ይናገራል። የትግራይ ወራሪ ኃይልን ጥሩ ምሳሌ ሲያደርግ፣ የትግራይን ወራሪ ኃይል እውቅና ሰጥቶ ትክክለኛና ሌላውም ምሳሌ ሊያደርገው የሚገባ ነው ሲል ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። አማራን ለማጥፋት እየሰራ ያለን ኃይል ነው ምርጥ ተሞክሮ እያለ የሚያስተዋውቀው፣ የሚያሞካሸው። አማራው ላይ ይህን ያህል ውድመት እየፈፀመ ያለውን ቡድን ጠቅሶ አማራውም ይህን የሚመስል ቡድን ነው መንግስት ሊይዝ የሚገባው ይላል። ይህ ማለት የትግራይ ወራሪ … [Read more...] about እነ ኤርሚያስ ለገሰን አማራ ምን ቢበድላቸው ነው በዚህ መጠን ሊበቀሉት ፈለጉ?
የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ (ትህነግ) ይመራው የነበረው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከትህነጉ አሸባሪ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ የካድሬ ቃል” ኤርሚያስ ሲጠቀም መቆየቱን የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል። መረጃውን ይፋ ያደረገው ኢትዮ 12 ነው። በ360 “ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሰሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ July 2, … [Read more...] about የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡ ኤርምያስ ሹመት አስቦ የለውጡ ደጋፊ የነበረ ጊዜ የተናገረው የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡ ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”