• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ

November 23, 2021 02:35 am by Editor 3 Comments

ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤

“ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”።

ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን ለመታደግ ወደ ግምባር የዘመተ መሪ በሚል ታሪክ የሚስታውሳቸው ይሆናሉ፤ በጥቅማጥቅም ብለው ለነጭ የሚገዙ የአፍሪካ መሪዎችን ወቃሽ ውሳኔ ነው። ወደድንም ጠላን ጀግና ናቸው።

ይህ ግን የእነ እንትና ሠፈር የሚወደው ዓይነት ውሳኔ አይደለም። ጠቅላዩ ምዕራባውያኑ ከገመቱት አማራጮች የራሳቸውንና ምናልባትም ያልተሄደበትን ሦስተኛውን መንገድ ነው የመረጡት። ለእነ እንትና ግን ይህ በየቀኑ በቱቦ (ዩትዩብ) ለሚለቁት አሉባልታ አፍራሽ ውሳኔ ነው።

እነ እንትና በመረጃ ቲቪ በየቀኑ የሚተፉ የውርደትና የነውር ተምሳሌቶች ናቸው – ኤርሚያስ ለገሠ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዘመድኩን በቀለ፣ …። አጀንዳ ፈጻሚዎች ናቸው። ለአማራ እንደቆሙ አስመስለው በየዕለቱ መርዝ የሚረጩ የወያኔ ሽርፍራፊ ሳንቲም ለቃሚዎች ናቸው። ከዲጂታል ወያኔ ጋር የዓላማ እና የግብ አንድነት አላቸው – ሁለቱም የሚከተሉት መርህ “እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል” የሚል ነው። ዐቢይን በተቻለ ሁኔታ ቀጥቅጥ፣ በሕዝብ አስጠላው፣ የአማራው ጨፍጫፊ አድርገህ ሳለው፣ … ከዚያ መንጋውን መበተን ይቀልላል።

የማክሰኞው የ360 አዳምጡን ባዮች እና የፖለቲካ ጠንቋዩ ዘመድኩን ውሎ በዐቢይ የመዝመት ውሳኔ ላይ ሆኖ የሚከተሉትን እንደሚሉ መገመት አያዳግትም፤

  • ዐቢይ የዘመተው የራሱን ዝና ከፍ ለማድረግ እና ኢጎ ለማርካት ነው
  • ኤርሚያስ፤ “ለዐቢይ ከምንም በላይ የራሱ ማንነት ይበልጥበታል፤ (ኢየሩስ/ብሩክ) ይህ ከዚህ በፊትም ተናግሬዋለሁ መረን የለቀቀ ናርሲሲዝም ነው፤ አሁን እዘምታለሁ ማለቱ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው፤ ራሱ የጻፈውን መመልከት ይበቃል፤ ለዝና፣ ለመደነቅ ብሎ ይህንን ውሳኔ እንደወሰነ ወደ በኋላ ላይ በአራት ከፍዬ እተነትነዋለሁ …”
  • ሃብታሙ፤ “እኔ ስለዚህ ሰውዬ የምለው ነገር ካጣሁ ቆይቻለሁ፤ እንደው ጠበል የሚወስደው ቢኖር ጥሩ ነው ብዬ ስናገር ማንም የሰማኝ የለም፤ በውነት ኢትዮጵያን ያከለ አገር በዚህ ዓይነት የወረደ ሰው መመራቷ መቀበል የማልችለው የውርደት ውርደት ነው” ይላል ሃብታሙ ኢንተርኔቱ ከሚቋጥበት ቤዝመንት ሆኖ፤
  • ዘመድኩን (ሃሳቡን ባጭሩ መጻፍ የማይችል መጻጉ ስለሆነ እኔም እንደሱ ላርዝመው)፤ “ዐቢይ ይምራን፤ ብልጽግና ተስፋችን ነው (ማሸሞሩ ነው)፤ ስነግርህ ስማ፤ እኔ ዘመዴ እንደሆንኩ የምትፈልገውን ሳይሆን የምትጠላውንና መስማት የማትፈልገውን ነው የምግትህ፤ ዐቢይ ሁለቱን ባለማተቦች አማራና ትግሬን አጣልቶ ኦሮሙማን ለማንገሥ ነው ከነሽመልስ ጋር እየጸለየ የሚሠራው፤ ለሱ ምን ጨነቀው ሃይማኖቱ አይደል፤ ኦርቶዶክስ ሲያፈርስ አማራን ያፈርሳል፣ ኢትዮጵያዊነት አብሮ ይፈርሳል፣ …”

በተለይ የዘመድኩን ነገር የሚገርም ነው። የትህነግ ሽፍቶችን “ባለማተቦች” እያለ ሲጠራቸው ቅንጣት ታህል አይሰቀጥጠውም። ይህንን ባለበት አፉ “ለዋልድባ አባቶች ገንዘብ እናሰባስብ” እያለ የኅሊናውን ወቀሳ ዝም ለማሰኘት የሚታትር የአእምሮ ስንኩል ነው። ቤተመቅደስ ገብቶ ካህናትን በግድ ሥጋ እንዲበሉ የሚያደርገውን፣ የካህን ሚስት ካህኑ ፊት የሚደፍረውን፣ ቤተመቅደስ ውስጥ እጅግ አስነዋሪ ተግባር የሚፈጽመውን፣ አማራውን በጾም በሬውን እያረደና ሥጋ እያስጠበሰ በግድ ብላ የሚል አረመኔ ለዘመድኩን “ባለማተብ” ነው። ለነገሩ ዘመድኩን ከስታሊን ገብረሥላሴ የሚለይበት እርሱ አማራ ነኝ ስለሚል እና ስታሊን ደግሞ ትግሬ ስለሆነ ነው። ከዚያ ሲያልፍ ሁለቱም የመርዝ ብልቃጡ መለስ ዜናዊ አምላኪዎች ነበሩ። ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

እነዚህ እንግዴ ልጆች ዓላማውና ግቡ ምን እንደሆነ ግልጽ ባልሆነው የመረጃ ቲቪ እየቀረቡ የከረፋ ትፋታቸውን ይተፋሉ። ይችኑ ጠቅላዩን የማዋረድና የመንቀፍ አባዜያቸውን ልቡ ለታወረው ቴዎድሮስ ጸጋዬ ያቀብሉታል። እየተናበቡ አድማሳቸውን በማስፋት አማራን የሚደግፉና የሚጨነቁለት መስለው የሚቀበርበትን ጉድጓድ በየቀኑ ይምሱለታል። በእነርሱና መሰል ከንቱዎች አማራው ተከፋፍሎ ይኸው ለትህነግ ጥቃት ፍጹም ተጋላጭ ሆነ። አፋርም ተጠቅቷል። ነገርግን እንደ አማራው በነዘመድኩን እና ሃብታሙ ዓይነት ደናቁርት ስላልተከፋፈለ የአፋር ምድር ለትህነግ ረመጥ ሆነበት።

አንዲት ነገር እንደ ማሳሰቢያ ልስጣቸውና ላብቃ፤ በማክሰኞው የዐቢይ ወቀጣ ላይ ሌላ የሚወቀጥ ሰው ላቀብላችሁ – የአብኑ አቶ ክርስቲያን ታደለ! የጠቅላዩን ውሳኔ ተከትለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የአብን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህንን ነው ያሉት፤ “ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት የምንሰስተው ሕይወት የለምና እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዘምታለን። ሕዝቤ ሆይ ተከተል!”

አደራ ክርስቲያንንም አብራችሁ መውቀጡን እንዳትረሱ በተለይ “ባለማተቡ” ዘመድኩን እንዳትረሳ።

ለገሠ በቀለ     

“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Middle Column, Opinions Tagged With: ermias legesse, habtamu ayalew, operation dismantle tplf, zemedkun bekele

Reader Interactions

Comments

  1. Ashebir says

    November 23, 2021 09:01 am at 9:01 am

    ለግሰ በቀለ

    እነ ኤርምያስን የሚየሳስቱዋቸው እነማን መሰሉህ? “መንግሥት ወታደሮቹን አፈግፍጉ እያለ.በጁንታው ለምን ያስፈጀናል? እኛን ማጥፋት ፍልጎ ከሆነ፤ በአውሮፕላን ከላይ ቦንብ ጥሎ በቀላሉ ቢጨርሰን አይሻልም ወይ? እያሉ የሚቀልዱትን ከቁም ነገር እየቆጠሩ ነው። አይመስልም?

    Reply
  2. birru says

    November 23, 2021 02:03 pm at 2:03 pm

    የጠ/ሚ ጉዳይ ግራ እሚያጋባ ነው። ግንባር ሂደው ምን ሊሰሩ ? በዚህ ቀውጢ ጊዜ ባንከር ውስጥ ቁጭ ብለው የጦር መሀንዲሶቻቸዉን ይዘው፣የተበላሸውን ማስተካከል ሲገባ በግንባር መገኘት አደጋ መጋበዝ ይመስለኛል። በእኔ ግምት የጦርነቱ አጀማመር የተዋጣለት ነበር እላለሁ።እየቆየ የተበላሸው ለአፈጻጸሙ ትኩረት ባለመስጠቱና በሚገባ ባለመታቀዱ ይመስለኛል። ፈረንጆቹ “It is not how you start but how you finish” ይላሉ። የዶ/አቢይ አመራር አስቀድሞ ባዘጋጀው የኤርትራ ወዳጅነት ለዚህ ጦርነት ‘ ተስፈንጣሪ ‘ ጉልበት ሲያገኝ፣ ጦርነቱን በድልና በክብር ለመጨርስ ግን በብዙ የሚያሳፍሩ ምክንያቶች ሊጓተት ችሏል። የወያኔ ቅሬት የሆነው የዘር ተውሳክ ተጠራርጎ ከሰራዊቱ ዉስጥ ከጠፋ ዶ/ር አቢይ፣ ሌላ አድዋን የሚፈጥር አርሚ እንደሚገኙ አልጠራጠርም።

    Reply
  3. Ashebir says

    November 29, 2021 11:56 am at 11:56 am

    ከዚህ ጦርነት ጋር በተያያዘ፤ ካደርጓችው አስደናቂ ነገሮች፣- የዶ{ር አቢይ የሰሜን እዝ ሲጠቃ፡ ፓርላማ ቀርበው “እስከሚጨፈጭፉን አልነካናቸውም” ሲሉ፤ እንዴ! እስከምትጨፈጨፍ ምን ታደርግ ነበር? ብሎ የጠየቃቸው የለም። በግሌ እኔን ያሳቀኝ፣ ትግራይን ሲለቁ ተኩስ አቁሜአለሁ አገርም ለቅቄአለሁ አሉ። አገሩን ስትለቁ ተኩሱ እንደሚቆም የታውቀ ነውና ተኩስ አቁሜአለሁ ማለቱ ምን አስፈለገ? ብሎ የጠየቀ የለም። ከሁሉ የሚያስደንቀው ደግሞ “ወያኔ አመድ ሆኖ በኗል” ባሉ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ወደፓርላማ መጥተው ይህንኑ ፓርልማ ቀርበው በሽብርተኝነት ፈርጁልኝ ሲሉ፤ ምነው አመድ ሆኗል ብለው አልነበረም? ምን መጣ? ብሎ የጠየቀ የለም። ሌላም ደግሞ፤ የክተት አዋጅ አውጀው፤ ዋል አደር ብለው አንድ የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ሳለ፤ ታጠቅ፤ ዝመት እትዮጵያ አያስፈልጋትም፤ ትራክተር፤ ማረሻ… ወዘተ ነው የሚያስፈልጋት ብለው ቁጭ አሉ። ማንም ምንም ያለ የለም። በመጨረሻ ቱመትኩ አሉና ቁጭ አሉ። ቀጥሎ ስየሚባለው መተንበይ አይቻልም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule