አቶ በላይነህ ክንዴንና የተለያዩ የአማራ ባለሃብቶችን ስም በመጥራት መስዋዕትነት እየተከፈለበት ያለውን ትግል ለማኮላሸት የምታደርጉትን እንቅስቃሴ ደርሰንበታል፤ መንግሥትም ሆነ መከላከያ ንብረታችሁን አይጠብቅም፤ ንብረታችሁን የሚጠብቀው ሕዝብ ነው፤ ብታርፉ ይሻላችኋል ሲሉ “በባንዳነት” ፈርጀው እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚጠቁም መረጃ ራሳቸውን ኢትዮ 360 ብለው የሚጠሩት ሰጡ። ይህንን የሰሙ ከዚህ በፊት በዚሁ ሚዲያ አቶ ግርማ የሺጥላ “half caste ሃፍ ካስት” ወይም ዲቃላ ወይም ቅልቅል በማለት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ አስቀድሞ ካሰራጩት መረጃ ጋር አመሳስለውታል። ምናልባትም መረጃው የደረሳቸው ባለሃብቶች ጉዳዩ በሕግ እንዲታይላቸው የሚያደርጉበት ሁኔታ ይኖራል ተብሏል። ሙሉ መረጃውን ቪዲዮው ላይ ይመልከቱ። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በላይነህ ክንዴ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ኢትዮ 360ዎች ጠቆሙ
habtamu ayalew
ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
በኤርሚያስ ለገሰ እና በሃብታሙ አያሌው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ውዝግብ በርካታዎችን ሲነጋግር የቆየ ነበር። በተለይ በመካከላቸው ጥል እንዳለ በግልጽ በሚታይ መልኩ በአደባባይ እየወጡ የሚናገሩት ከበስተጀርባ ምን እየተደረገ ነው የሚል ጥያቄ ብዙዎች እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። አሁን ግን ሁኔታው ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። በኤርሚያስ እና በሃብታሙ መካከል ሰሞኑን የታየው ልዩነት አስመልክቶ ጥቂቶቹን ቪዲዮዎች እንመልከት፤ ከዚህ ሌላ የጌታቸው ሹመት በተሰማበት ቅዳሜ ዕለት እንደተለመደው ከሃብታሙ ጋር ለውይይት መውጣት የነበረበት ኤርሚያስ አልወጣም። ሃብታሙ ከሌላ ግለሰብ ጋር ለወሬ የወጡ ሲሆን በበረከት እና ጌታቸው ሥልታዊ የካድሬ ትንታኔው የበርካታዎችን ቀልብ የሚስው ኤርሚያስ በዚህ ወሳኝ ቀን ለትንታኔ አለመከሰቱ ምናልባት ለጌታቸው “ሹመት ያዳብር” … [Read more...] about ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን … [Read more...] about ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
“ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ
ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤ “ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”። ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን … [Read more...] about “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ