• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች

July 17, 2022 05:36 pm by Editor 2 Comments

የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው።

በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን ሲያድኑ ሤራው የተካሄደባቸው ፕሬዚዳንት ረሲፕ ኤርዶጋን ሤራውን ለማክሸፍ ስልካቸውንና ማኅበራዊ ሚዲያን መጠቀማቸው በዋናነት የሚጠቀስ ነው።

ከላይ እንደተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ሕይወታቸውን እስከማጣት የደረሱ ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሉ ዓይናቸው እስኪያብጥ፣ ጆሮአቸው እስኪደማ የወሬ ሱስ ሰለባ የሆኑ። ጠዋት ሲነሱ (ተኝተው ካደሩ) “ዛሬ ምን አለ?” ብለው እንደ ነገረኛ ሰው በወሬ ቀናቸውን የሚጀምሩ። እነዚሀ ሰዎች ከጠዋቱ የመጸዳዳት ተግባራቸው በፊት በዜና ስም የሚለጠፍ ተራ ወሬና የመንደር አሉባልታ እንዲጸዳዳባቸው ራሳቸውን በፈቃዳቸው አሳልፈው የሰጡ ከንቱዎች ናቸው።

ከዚህ ዓይነት የቀን ጅማሮ በኋላ እንዲህ ዓይነቱ ሰው በልቡ ማኅደር ያለውም ሆነ ቀኑን ሙሉ ከአፉ የሚወጣው ጽድቅ ሳይሆን ርኩሰት፣ ነውር፣ ብልግና እና ውርደት ነው። ልቡን ለክፋትና ርኩሰት ባዘጋጀበት መጠን ቀኑን ሙሉ እያነፈነፈ አእምሮውን የሚሞላው ይህንን እየቀመሙ በሚግቱት ግጭት ጠማቂዎች፤ ክፋት ጠንሳሾችና አእምሮአቸው የላሸቀ የጭንቅላት ጉዳተኞች የወሬ መርዝ ነው። ከንጋት ጀምሮ ወደ ውስጡ ባስገባው መርዝ መጠን እርሱም በየፊናው መርዙን ሲተፋ ይውላል። ይህንን በማስፈጸም ማኅበራዊ ሚዲያ የተዋጣለት መሣሪያ ነው።

ባለፉት ሁለት ሦስት ቀናት በአገራችን መልካም የሚባሉ ሥራዎች ተከስተዋል። በወለጋ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችን ልባችንን እያደማ ሌቦችን ወደሚገባቸው ቦታ ማስገባት ወሳኝ ሥራ ሆኖ ተስተውሏል። መከላከያም ከሸኔ ጋር ሲፋለም፣ ሠልጣኞችን ሲያስመርቅና ሌሎች ለአገር ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን ሲፈጽም ነው የሰነበተው።

በተለይ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦች በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ያለፉት ሁለት/ሦስት ቀናት የሁሉም ትኩረት ተመሳሳይ ተግባራት በሁሉም የሥልጣን ተዋረድ ይቀጥል የሚል ነበር። በኮንዶሚኒየምም ሆነ በዕርዳታ ጉዳይ ሕዝብን ከመዝረፍ አልፈው የትህነግን የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት የተቀናጀ ሤራ ሲፈጽሙ የነበሩ በተያዙ ቀን እየተናበቡ የሚሠሩት አጀንዳ ሰጪዎቻችን የወሬአቸው ቀዳሚ ዜና ያደረጉትን ጉዳይ ምን እንደነበር መመልከቱ ከማኅበራዊ ሚዲያ ሱስ ለመላቀቅ ዓይን ከፋች ነው።

የትህነግና የግብጽ ልሳን የሆነው 360 ዋና ርዕስ ያደረገው ይህንን ነው፤

የአማራ ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው የቀድሞው እስክስታ ወራጅና የዳዊት ወልደጊዮርጊስ አጋፋሪ አበበ በለው ደግሞ ይህንን ነው ቀዳሚ መረጃ አድርጎ ያቀረበው፤

በአስከፊው የትህነግ የግፍ ዘመን የመዝናኛ ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረው ማየት የተሳነው ቴዎድሮስ ጸጋዬ በማኅበራዊ ሚዲያው ጠጅ ለሚያሰክራቸው ተከታታዮቹ ይህንን ነው ርዕሰ ጉዳዩ ያደረገው፤

ሲሻው ቀዳሽ ዲያቆን፣ ሲሻው አራጅ ወያኔ፣ ሲሻው ወታደር፣ ሲሻው ደግሞ የሚዲያና ፖለቲካ ተንታኝ የሆነው ለ360ውም የዩትዩብ ጡረተኞች የዕለቱን አጀንዳ የሚሰጣቸው ስታሊን ደግሞ ዋና አጀንዳው ይህ ነበር፤

እነዚህ እየተናበቡ አገር በማፍረስ አጀንዳ ላይ የተሰማሩ፤ የየዋሆችን ልብ ለመስለብ ኢትዮጵያዊ ስምና ሠንደቅ ከፊት ለፊታቸው የሚያደርጉ፤ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” እያሉ የሚምሉ የኮንዶሚኒየም ሌቦች ሤራ በተጋለጠበትና፤ ከረሃብተኛ የዕርዳታ እህልና ገንዘብ እየነጠቀ ራሱን ሲያበለጽግ የነበረው ምትኩ በተያዘበት ዕለት ለእነርሱ ይህ ለዐቅመ አጀንዳ የደረሰ፤ ለትንታኔ የበቃ ጉዳይ አልነበረም። እንደ እውነቱ ከሆነ ብቁ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም። ያልተጠበቀው ኩነት በተከታታይ ያቀዱትን አጀንዳ የእንቧይ ካብ ስላደረገባቸው ነው። ከእነዚህ ግን የተለየ ሌላ በወገኖቹ ደም የሚሸቅጥ አለ …   

በአምላክ ስም አማትቦ ጀምሮ የጥላቻ ቃላትን በመትፋት ሰይጣንን የሚያስንቀው፤ አእምሮው የተቃወሰ መሆኑን በራሱ አንደበት የመሰከረው ዘመድኩን በቀለ ደግሞ ሰሞኑን ሁሉ “አጀንዳዬን አልቀይርም”፤ “ኑ ለቅሶ እንድረስ” እያለ በወለጋ ወገኖቻችን ጭፍጨፋ ላይ ሲነግድ ነበር የከረመው። በዚህ የደም ንግድ ብዙዎችን አንዴ ጥቁር ሲያስለብስ፤ አንዴ ሲያስለቅስ ከከረመ በኋላ እንደለመደው “(የስድብ) አገልግሎቴን በዚህ ደግፉ” ብሎ ለአንድ ሳምንት እንደማይኖር መረጃ ሰጥጦ ተሰናብቷል። ቆፈናሙ የጀርመን ብርድ ሳይገባ ፈታ፣ ላላ፣ ዘና ልበል፤ ከቤተሰቦቼ ጋር ልዝናናበት ተውኝ ብሎ አጀንዳውን ቀይሯል። አስለቅሶ፣ “ለአገልግሎቱ” መደጎሚያ ብሩን ሰብስቦ፣ አልቀይርም ያለውን አጀንዳ ቀይሮ ለሳምንት ተሰናብቷል።

ዘመድኩን እንደምክንያት የሰጠው የጀርመን መንግሥት በ9 ዩሮ ተዝናኑ ብሎናል የሚል ነው። ምነው ያ ሁሉ አማራ ተጨፍጭፎ ገና ደሙ ሳይደርቅ አንተ እንዴት አጀንዳ ለመቀየር አንጀትህ አስቻለህ? ብሎ የሚጠይቅ የለም። እንዴት በቀን 90 ጊዜ ትህነግና እነ ጃል መሮ የሚልኩልህን ፎቶ “የአማራ ደም” እያልህ እየለጠፍህ በአስከሬን ሳንቲም ስትሰበስብ እንዳልቆየህ አሁን ለመዝናናት ልብህ እሺ አለ? ብሎ የሚሞግት የለም። እኛን በየቀኑ “አጀንዳዬን አልቀይርም” ስትለን ቆይተህ ለምን እና እንዴት አጀንዳህን ለመቀየር ደፈርህ? የጀርመን መንግሥት በግድ ተዝናኑ፤ ካልተዝናናችሁ ትቀጣላችሁ አላለም፤ ምነው አንተ መዝናናቱን ግዴታ አደረግኸው? በተለይ እንዳንተ ዓይነቱ “አጀንዳዬን አልቀይርም” ባይ ምነው ለጀርመን መንግሥት “አይ እኔ ለቅሶ ላይ ነኝ፤ ሐዘን ላይ ተቀምጫለሁ፤ አልዝናናም፤ ተውኝ ላልቅስበት” ማለት አቃተው? በማለት ከተከታዮቹ የሚሞግት የለም። ምክንያቱም የአእምሮ መላሸቅ ሰለባ ስለሆኑ እውነቱ ውሸት፤ ውሸቱ እውነት ሆኖባቸዋል። በአደንዛዥ ዕፅ እንደሚደነዝዝ ሰው በወሬ ድግምግሞሽ ማሰብ እስከሚሳናቸው ደንዝዘዋል።   

በአሁኑ ሰዓት ከድምጺ ወያኔ፣ 360፣ TMH፣ ርዕዮት፣ ኢትዮ ፎረም ወዘተ እኩል ትግራይ ከሚሰሙ መካከል አንዱ ዘመድኩን በቀለ ሆኗል። ትህነግ ደጋፊህ ሆኖ ለሕዝቡ እንድትሰማ ሲፈቅድልህ በመናገር ነጻነት ስላመነ ሳይሆን ከድምጺ ወያኔ እኩል ካድሬውና አጀንዳውን ፈጻሚ ምርጥ ወያኔ ስለሆንህለት ነው። ትህነግ ማለት አማራ ጠላታችን ነው፤ አማራን ማዋረድ፣ መግደል፣ መጨፍጨፍ፣ ማፈናቀል፣ መቅኖቢስ ማድረግ አለብን የሚለው ማለት ነው። የወልቃይትን ሕዝብ ከምድረገጽ ለማጥፋት ለ30 ዓመት የሞከረውና አሁን በቅርቡ ደግሞ አማራ ክልል መጥቶ ሒሳብ አወራርዳለሁ ባለው መሠረት የክልሉን መሠረተ ልማት አውድሞና ሊጥ ጠጥቶ የተባረረው ትህነግ ዘመድኩን በቀለ በሮማኖት አደባባይ መቀሌ ላይ እንዲሰማ ፈቅዷል። መረጃው እነሆ! (ምንጭ፤ Melke Ethio Habesha)

ትህነግ ሲያበሰብስ እንዲህ ነው። በአንድ በኩል ወዳጅ መስሎ ግፋ በለው፤ አብሬህ ነኝ ይላል። በሌላው ደግሞ የትህነግ ደጋፊ መሆንህን ለዓለም ያሳውቅብሃል። ዘመድኩን መቀሌ ላይ ሲደመጥ ቀድተው የላኩት ማንም ሳይሆኑ የትህነግ ካድሬዎች ናቸው። ዘመድኩን ተጠቁሯል፤ አጀንዳው የትህነግ አጀንዳ ነው። የፈለገ ቢያማትብ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ቢያውቅና ቢመረምር ቢያገላብጥ ዘመድኩን በቀለ የሚያራምደው አጀንዳ ከትህነግ አጀንዳ ጋር የሚመሳሰል ነው።

ከመግቢያው ላይ የተጠቀሱት የኮንዶሚኒየም ሌቦች እና የዕርዳታ ማስተባበሪያ አመራር መያዝ ገቢ የሚያስገኙ የዜና ርዕሶች አይደሉም። ሥርዓት ለማፍረስ የሚጠቅሙ የዜና ርዕሶችም አይደሉም። የዩትዩብ ተመልካች የሚስቡ አይደሉም። መንጋውን ለመመገብ የሚጠቅሙ የወሬ ምግቦች አይደሉም። ተጨፈጨፈ፣ ተገደለ፣ ተሰደደ፣ … የሚሉት ናቸው ገቢ የሚያስገኙ የዜና ዘገባዎች። ይህንን የሚያውቁት ሸቃጮች ደግሞ መዘገብ ያለበትን ሳይሆን ኪሳቸውን የሚያደልብላቸውን እና መንጋውን እንደፈለጉ የሚነዱበትን ነው ቀን ተሌት የሚያወሩት። ታላቁ መጽሐፍ እንደሚለው “በድን ወዳለበት በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ”።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: Abebe Belew, ermias legesse, Ethio 360, habtamu ayalew, Mereja TV, operation dismantle tplf, Stalin, Tewodros Tsegaye, Zemedie, zemedkun bekele

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    July 18, 2022 10:44 am at 10:44 am

    ዓለሙ ሁሉ ገምቷል የምለው ለዚህ ነው። በፈጠራ ወሬ ሰውን ማበራየት የተለመደ የንግድ ዓርማ ሆኖአል። ሲጀመር ያለምንም መረጃ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ አደረገ፤ ከንቲባዋ ይህን ሰራች፤ ዶ/ር አብይ ኦነግ ነው አይኑና ጆሮው እያየ እየሰማ ነው ሰውን የሚያስጨርሰው ኸረ ስንቱ ወዘተ የሚለፉ አክራሪ ብሄርተኞችና የወያኔ ተከፋዪች ቅንጣት ያህል መረጃ በሚያላዝኑት ጉዳይ ማቅረብ አይችሉም። አንድ አንድ ደግሞ ለይቶለት አብዶ የባለስልጣን ወላጆችን እስከ መሳደብና ተራ ዘለፋ ስድፍ እስከ መለጠፍ ደርሰዋል።
    በቅድሚያ የእኔ እይታ አቶ ሽመልስ አብዲሳም ሆነ ሌሎች ባለስልጣኖች ሆን ብለው ሰው በጅምላ ያስገድላሉ ብዬ አላምንም። ዶ/ር አብይም ሃገሩን የሚወድ በወስላታና በተመሰቃቀለ ህዝብ መካከል የቆመ ቅሚያና ዝርፊያን የሚጠላ ሰው ነው። ይህ ሲባል ባለስልጣን የሆኑ ሁሉ ለበጎ ተሰልፈዋል ማለት አይደለም። ብሄር ያሰከራቸው ቀን ተደምረው ማታ በመቀነስ ሃገር የሚያፈርሱ እንዳሉም መገመት ይቻላል። ይህ ደግሞ ፓለቲካ ነው። ስንዴን ከንክርዳድ ማበጠር የስለላ መረቡ ሥራ ነው። ይህን በፌስቡክ ጽፈሃል፤ ያን ተናግረሃል፤ ይህን አቁመህ ያን ንደሃል እያሉ ሰውን በየሰበቡ ማፈንና ገርፎና ያላቸውን ዘርፎ መልቀቅም የመንግስትን ባህሪ አያሳይም። ሊቆም ይገባዋል። መሆን ያለበት ለጻፉት፤ ለሚናገሩት ሁሉ መረጃ እንዲያቀርቡ መጠየቅ እንጂ “ወታደራዊ ሚስጢር ” አውጥተሃል በማለት እንደ ተመስገን ደሳለኝ ያሉ እውቅ ጋዜጠኞችን ማሰር ራስን ወንጀለኛ ማድረግ ነው። ገጣሚው ይግጠም። ጸሃፊው ይጻፍ፤ ለፍላፊው ይለፍልፍ። ህዝብ ይመዝነው። እውነት ያለውን ነገር እንማርበታለን፤ ሌላው ደግሞ መጣያ ሥፍራ ከተገኘ ቆሼ ወስዶ ማራገፍ ነው። ካልሆነ ስንቱ ታስሮ፤ ስንቱን አስፈራርቶ ይዘለቃል? ስንት የሚሰራ ጉዳይ እያለ በሃገራቸው አንድነት በምንም ሂሳብ የማይደራደሩትን ወገኖቻችን ስናሳድድ እንኖራለን?
    ማህበራዊ ሚዲያ ማለት መርካቶ ገቢያ ማለት ነው። ሌባው፤ ጤነኛውም የሚጋፋበት የእኔ አውራ ጣት ካንተ ይበልጣል የሚባባልበት የገቢያ መሃከል ነው። እዚያ ውስጥ ስለ ፓለቲካ የተለጠፈ ነገር አንብቦ ደሙ የሚፈላ ወይም በትካዜ ልቡ የሚሰበር ሰው ሁሉ ብኩን ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት 99% በውሸትና ለሰው ልጆች ጥቅም በሌለው ነገር የተሞላ ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ሲባል ራሱ ስሙ ቁጭ ብሎ ሰው ሰንበቴ እየጠጣ የሚጫወት ያስመስሉታል። አይደለም። የወሮበሎች ጉድጓድ ነው። እልፍ ተከታይ አለኝ ይላል አንድ ተነስቶ። እኔ የማንም ተከታይ መሆን አልፈልግም። ተከትለህ የት ነው የምትደርሰው የሰው ገቢያ ከማድመቅ በስተቀር። የአሜሪካ ሜጋ ቸርቾችና ማህበራዊ ሚዲያ ተመሳሳይነት አላቸው። ገቢያቸውን እንጂ ተከታዪቻቸውን አያውቁም። ከላይ በድህረ ገጽ ላይ ለናሙና የተለጠፉት ሁሉ አሰልቺዎችና አጋናኝ ወረኛ ሰዎች ናቸው። ከመሰረቱ (Default position) የወሰድ ግለሰቦችና የሚዲያ አናፋሾች በመሆናቸው ምንም አይነት መረጃ ቢቀርብላቸው ሃሳባቸውን የመለወጥ ተስፋ የላቸውም። የሚገርመው ግን ሁሉም ባይሆኑ ጥቂት የማይባሉት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ሰላም ቆመናል ይሉናል። ተግባራቸው ግን ሰው ከሰው ጋር የሚያጋጭ፤ የመንግስትን አመራር ያለ ምንም ተጨባጭ መረጃ የሚወነጅል ለሃገርና ለወገን ሲፋለሙ የቆሰሉ ሰዎችን የሚያጥላላ ወይም የሚያለያይ ብቻ በስማ በለው ሰምተው በስማ በለው ነገር የሚነዙ ቱልቱላዎች ናቸው። መንግስት ሥራውን እንዲሰራና በሰራው በጎ ነገር እንዲመሰገን ባልሰራው እንዲጠይቅ ለማድረግ የጅምላና የነሲብ ኩነናን ማቆም ያስፈልጋል። እንዴት ጠ/ሚሩ ሰው እያለቀ የስንዴ ማሳ ይጎበኛል? እንዴት ችግኝ ተከላ ይውላል? የሚሉን በውጭና በውስጥ ያሉ የሙታን ስብስቦች ውጊያው ከድህነት፤ ከአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ከወያኔና ወያኔ እየከፈለም ሆነ እያስፈራራ ካሰለፋቸው የዘርና የውጭ ጉዳይ አስፈጻሚ ተላላኪዎች ጋር ነው። በአንድ እጅ ጠበንጃ በሌላው አካፋን ዶማ ይዘን ካልሰራን ችግራችን ይሰፋል እንጂ አይከስምም። እንዴት በፓርላማ የህሊና ጸሎት ሳይደረግ ቀረ ብለው ቡራ ከረዪ ላሉ ተደረገ አልተደረገ ለሟችና ለተፈናቃይ የሚያመጣው ምን ጥቅም አለ? ህሊና በጎደለው ህብረተሰብ መካከል የህሊና ጸሎት ለራስ ነው ወይስ ለሞቱት? ግን ጉዳዪ ቁርሾ መወጫና ነገር መፈለጊያ ስለሆነ ሰው ይንጫጫበታል።
    በማጠቃለያው ፓለቲካ ጥልፍልፍ ነው። በኢትዮጵያ ላይ የተጫነው የውጭና የሃገር ውስጥ ጫና የምናውቀው ቅንጣት ያህሉን ብቻ ነው። መንግስቱን በሴራ ያባረሩትና ወያኔን በአዲስ አበባ ሻቢያን በአስመራ ያስቀመጡት እነዚያ ሃይሎች ዛሬም ሊያተራምሱን እየሰሩ ነው። በቅርቡ ወደ ጀዳ ተጉዘው የሳውዲዊን ገዳይ ሰው በጭብጥ እጅ ሰላምታ የተገናኙት የአሜሪካው መሪ እንዴት እንዲህ ያደርጋሉ ተብሎ በብዙ እየተዘለፉ ነው። የእኔ እይታ ግን የሳውዲው ሰው ቆራጭ ለአሜሪካ ያለውን (Disdain) ያሳያል እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም። አሜሪካ በሳውዲ በፊት እንደነበራት ፓለቲካዊ ጫና የማድረግ ሃይል የላትም። እንዲህ ነው እንግዲህ የዓለም ፓለቲካ። የእኛው የጭቃና የጥላሽት መቀባባት ፓለቲካም ትርፍ አልባ ሰውን ከሰው የሚያላትም (Devoid of the truth) መኖሪያ ፍለጋ ለፍጆታ የሚቀርብ የእንክርዳድ ክምር ነው። ልብ ያለው ያስተውል። ጀሮ ያለው ይስማ። በቃኝ!

    Reply
  2. fasil says

    August 8, 2022 06:13 am at 6:13 am

    ewunetu siwetta taleqaqsalachu

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule