ከ698,000 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Mereja TV’ የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ ከነገ ጀምሮ “በአማራ ክልል ለ10 ቀናት የሚቆይ ዘመቻ የኮቪድ ክትባት በሚል ምንነቱ ያልታወቀ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል” የሚል መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል። ገጹ በተጨማሪም ህብረተሰቡ ክትባቱን እንዳይወስድ የሚያሳስብ መልዕክት ማከሉን አስተውለናል። መረጃ ቲቪ የተባለው ይህ የፌስቡክ ገጽ ይህን ይበል እንጅ በአማራ ክልል እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ለ10 ቀናት ሊሰጥ ስለታቀደው ክትባት የአማራ ክልል ጤና ቢሮና የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባለፉት ቀናት በተናጠል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ መስጠታቸውን ተመልክተናል። በመግለጫዎቹም የክትባቶቹ ምንነት የተገልጸ ሲሆን ዘመቻ አገር አቀፍ ስለመሆኑን ተብራርቷል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በትናትናው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ … [Read more...] about መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ
Mereja TV
ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች
የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባ ምክንያት ሕይወታቸውን ከሚያጡት በተጓዳኝ አገራቸውንም እያጡ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም። የዛሬ ስድስት ዓመት በቱርክ የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሤራ የማክሸፍ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። አገር ወዳድ ቱርካውያን የወሬ ሰለባ አንሆንም ብለው አገራቸውን … [Read more...] about ገቢ የማያስገኙ የዜና ርዕሶች