ከአሸባሪው ትህነግ ጋር የሚደረገውን የመጨረሻ ፍልሚያ አስመልክቶ ጠቅላዩ ይህንን ብለው ወደ ግምባር እንደሚዘምቱ አስታውቀዋል፤ “ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ”። ይህ በዘመናዊ አገላለጽ የተጻፈ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከነበረው የአጼ ምኒልክ የክተት ጥሪ ጋር የሚመሳሰል ነው። ጠቅላዩ ቃላቸውን ጠብቀዋል። “አንገቴን እሰጣለሁ እንጂ ተላላኪ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አይኖርም” ብለው ነበር። ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ወደ ሌላ አገር አልሄዱም። ወይም ደንዝዘው አዲስ አበባ በመቀመጥ እንደነ ጋዳፊ ለመሆን አልፈጉም። በዘመናዊ ታሪክ አገሩን … [Read more...] about “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ