ከለውጥ ወዲህ መላው የኢትዮጵያ ክፍል ሲታመስ ሰላሙ ተጠብቆ የነበረው በትግራይ ነበር። በአገሪቷ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የሰላም መታጣት ያሳሰባቸው እናቶች ወደ ተለያዩ ክልሎች ሄደው ስለ ሰላም ሲማጸኑ ቆይተው ትግራይ ሲደርሱ የተነገራቸው እነርሱንም ያስደመመ ነበር። በወቅቱ ከታቦት እኩል ለአምልኮ የደረሰው ደብረጽዮን የመለሰላቸው በትግራይ ሰላም ነው፤ ሰው ወጥቶ ይገባል፤ ሰላም የታጣው በሌላ ክልል ነው፤ እዚያ ሄዳችሁ ብታለቅሱ ይሻላል ነበር ያላቸው። ሌላው የአገሪቱ ክልል ቀውስ ውስጥ መግባት ዋናው መሪ እና ግጭት ቀማሚ ህወሓት መሆኑን የካደ ግብዝነት የተሞላበት ምላሽ ነበር። እጅግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ያለችው ትግራይ እስካሁን ድምጽ ሳይሰማባት ቆይቶ ዛሬ በተቃውሞ ስትናወጥ ውላለች። በጦርነቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በመለስ ዜናዊ አነጋገር … [Read more...] about በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ
getachew reda
በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ከአድዋ ወደ ራያ የዞረው የትግራይ አስተዳደር አዲስ መሪና ከመሪው ጀርባ የሚያጦዝ አዲስ ስብሃት ነጋን አግኝቷል። አዲሱ የስብሃት ነጋ ምትክ ንጉሥ ፈጣሪ (kingmaker) ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ሲሆን፣ የትግራይ ቲቪ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ መሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ ነው - ሁለቱም ከአማራ ከተወሰደው ራያ!! በይፋ በሚታዩ መረጃዎች ጌታቸው ረዳ በትግራይ ታጋይ ሳይሆን ትግራይን የመራ ብቸኛ ካድሬ ሆነው ይመዘገባል። ጌታቸው ረዳ ሌላ የሚያስመዘግበው ሪኮርድ ደግሞ በጥላቻና “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የተፈለፈሉ ሚዲያ፣ አክቲቪስቶች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የብሔራቸው ተቆርቋሪ መስለው ሲንቀሳቀሱና ጥላቻን ሲያሰራጩ የነበሩ፣ በየክልሉ የክልልነት ጥያቄ በማስነሳት ግጭት እና አገር ብጥበጣ ውስጥ የገቡ፣ ሁሉ በጌታቸው አመራር ሥር ስለነበሩ ቆጣሪያቸው … [Read more...] about በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
በኤርሚያስ ለገሰ እና በሃብታሙ አያሌው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ውዝግብ በርካታዎችን ሲነጋግር የቆየ ነበር። በተለይ በመካከላቸው ጥል እንዳለ በግልጽ በሚታይ መልኩ በአደባባይ እየወጡ የሚናገሩት ከበስተጀርባ ምን እየተደረገ ነው የሚል ጥያቄ ብዙዎች እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። አሁን ግን ሁኔታው ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። በኤርሚያስ እና በሃብታሙ መካከል ሰሞኑን የታየው ልዩነት አስመልክቶ ጥቂቶቹን ቪዲዮዎች እንመልከት፤ ከዚህ ሌላ የጌታቸው ሹመት በተሰማበት ቅዳሜ ዕለት እንደተለመደው ከሃብታሙ ጋር ለውይይት መውጣት የነበረበት ኤርሚያስ አልወጣም። ሃብታሙ ከሌላ ግለሰብ ጋር ለወሬ የወጡ ሲሆን በበረከት እና ጌታቸው ሥልታዊ የካድሬ ትንታኔው የበርካታዎችን ቀልብ የሚስው ኤርሚያስ በዚህ ወሳኝ ቀን ለትንታኔ አለመከሰቱ ምናልባት ለጌታቸው “ሹመት ያዳብር” … [Read more...] about ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው