ከበረሃ ውንብድና አገረ መንግሥትን ወደመምራት ሳያስበው የተቀበለው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት በነጻ አውጪ ስም አንዲት ሉዓላዊት አገር ጠርንፎ በአናሳዎች በግፍ ሲገዛ የነበረው የወንበዴዎች ቡድን ጎራ ለይቶ በአደባባይ መካሰስ ከጀመረና ውዝግቡም እየተካረረ መጥቶ ትግራይን እንደ አፍጋኒስታን ወይም ኢራቅ በጦር አበጋዞች ከፋፍሎ ወደለየለት ደረጃ እየወሰዳት መሆኑ በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቡድኑ መሪ የሆነው ደብረጽዮን እነ ጌታቸው የሚከሱኝ በፊትም ጦርነት ውስጥ ያስገባንና ሚሊዮኖችን ያስጨፈጨፈው ትህነግ ነው፤ አሁንም መልሶ ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው፤ ጦርነት ናፋቂ ነው እያሉ ነው፤ ነገር ግን ተጨፈጨፈ የተባለው ሕዝብ ማስረጃ የታለ? ባለተጨበጠና ባልተረጋገጠ፤ ማስረጃ በሌለው እኔን መክሰስ ብቻ ስለፈለጉ ባልሞተ ሕዝብ ይከስሱኛል በማለት … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
tsadkan gebretinsae
በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ከአድዋ ወደ ራያ የዞረው የትግራይ አስተዳደር አዲስ መሪና ከመሪው ጀርባ የሚያጦዝ አዲስ ስብሃት ነጋን አግኝቷል። አዲሱ የስብሃት ነጋ ምትክ ንጉሥ ፈጣሪ (kingmaker) ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ሲሆን፣ የትግራይ ቲቪ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ መሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ ነው - ሁለቱም ከአማራ ከተወሰደው ራያ!! በይፋ በሚታዩ መረጃዎች ጌታቸው ረዳ በትግራይ ታጋይ ሳይሆን ትግራይን የመራ ብቸኛ ካድሬ ሆነው ይመዘገባል። ጌታቸው ረዳ ሌላ የሚያስመዘግበው ሪኮርድ ደግሞ በጥላቻና “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የተፈለፈሉ ሚዲያ፣ አክቲቪስቶች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የብሔራቸው ተቆርቋሪ መስለው ሲንቀሳቀሱና ጥላቻን ሲያሰራጩ የነበሩ፣ በየክልሉ የክልልነት ጥያቄ በማስነሳት ግጭት እና አገር ብጥበጣ ውስጥ የገቡ፣ ሁሉ በጌታቸው አመራር ሥር ስለነበሩ ቆጣሪያቸው … [Read more...] about በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”
ወደ ገደለው ስንሄድ፦ የራያው ልጅ ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ አራት ኪሎ የባዮሎጂ ተማሪ ነበረ። ከዛም ትግል ስታይሌ ነው አለና ደደቢት በረሃ ወረደ።[ውጊያ ተለማመደ]ወያኔ ከደርግ ጋራ ስትዋጋ ከጦር ፊታውራሪዎች አንዱ ሆነ፤ ፃድቃን ገብረትንሳኤ። ከገቡም በኋላ ለአስር አመታት ያህል፣ በሌተና ጀነራል ማዕረግ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ኤታማዦር ሹም (Chief of Staff) ነበረ።ፃድቃን ቀጥተኛ፣ ቅን እና ሆደ ቡቡ ነው ይሉታል የሚያውቁት።[አንዴ]የካህሳይ አብርሃን 'የአሲምባ ፍቅር' መፅሃፍን ካነበብክ፣ ያኔ ኢህአሠ አሲምባ እንደገባ በብሄር ፌድራሊዝም ጉዳይ ኢህአፓና ህወሃት ሲከራከሩ፣ ''የብሄር ፌዴራሊዝም የታክቲክ ጉዳይ ነው። ማታገያ ነው እንጂ End አይደለም'' ብሎ የሞገተ ነው። ''የትግራይ ገባር የመሬት ላራሹ ጥያቄው ስለተመለሰለት፣ አሁን መደብ ምናምን ከምንለው ጨቋኝ … [Read more...] about ነገረ ወዲ ገብረ ትንሳኤ – ”አባዬ ምን በድለን ነው ህወሃት የምትቀጣን?”