ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህወሓት መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤ እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው። ደብረፅዮን ወደ ህወሓት የተቀላቀለው በመጨረሻው 1974 ዓም አካባቢ ነው። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታዬ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!! የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋን መምራት ይችላል ወይ? ነው፤የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲልም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታለች፤ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ አባይ … [Read more...] about ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
debretsion
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
“ዶክተሩ” ደብረጽዮን ምላሽ አለው
“… የአመራሩ ድክመት ድርጅቱን ጎድቷል፤ … የበላይ አመራሩ ሥራውን ሲገመግም ብዙ ጉድለት ተገኝቶበታል” በማለት ለፋና ቃለምልልስ የሰጠው አዲሱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር የወንበዴዎች ቡድን መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ነው። በበፊቱ አመራር ውስጥ ምክትል ሊቀመንበር የነበረው ደብረጽዮን፤ 35 ቀናት በፈጀውና ዋናው ችግር አመራሩ መሆኑን በገመገመው ስብሰባ መሠረት መባረር ሲገባው ይልቁንም ሊቀመንበር ሆኗል። Capella University ከተባለው የዲግሪ ወፍጮ ቤት “የዶክትሬት ዲግሪ” ተቀብሏል የሚባልለት ደብረጽዮን እንደ ቀድሞ አመራር “የበላይ አመራሩ ጉድለት ተገኝቶበታል” ካለው ድርጅት ራሱን ማግለል ሲገባው ራሱን በዓለምአቀፍ የአሻባሪነት የመረጃ ቋት ውስጥ የተመዘገበው ህወሓት ሊቀመንበር አድርጎ ራሱን ሾሟል። በከሁለት ቀናት በፊት “በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ … [Read more...] about “ዶክተሩ” ደብረጽዮን ምላሽ አለው
ግልፅ ደብዳቤ ለህወሃት
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ግልፅ ደብዳቤ ለህወሃት
አልሰሙም አልታረሙም
እነሆ ራሳቸው በጠሩዋቸው ጉባዔዎችና ኮንፍረንሶች ላይ ሁሉ በተደጋጋሚ ተነግረዋል አልሰሙም፤ ተመክረዋልም አልታረሙም። እኒህም የኢትዮጵያ ገዢዎች የኢህአዴጋውያን አዛዦች የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ህወሃታውያን ናቸው። ማስረጃ ቢባል ማርሻል መለስ ከመራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉባዔ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ የዘለቁት መሰል ጉባዔዎች ዋቢዎቻችን ናቸው(1)። እነሆም ህወሃታውያኑ በወጣትነት ዘመናቸው በሽፍትነትና ዘረኝነት እንደታበዩ ገድለው ዘርፈውና አጥፍተው በጎልማሳነታቸው ምኒልክ ቤተመንግሥትን በጠመንጃ ማረኩ። እነሆም በስተርጅና ዘመናቸው ባልገነቡት ቤተመንግሥት እየፏለሉ ከሽፍትነት የድውይ አስተሳሰባቸው፤ ከድኩም ባህሪያቸው፤ ከመሃይምነታቸው፤ ከመሰሪ ተፈጥሯቸው፤ ከናዚስት ዕምነታቸው ይታረሙና ይፀዱ ዘንድ ግን ከቶም አልተቻላቸውም። እነሆም በኢትዮጵያ መንበር ላይ ተኮፍሰው … [Read more...] about አልሰሙም አልታረሙም