የሕወሓትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀመሩትን ንትርካቸውን በመቀጠል፣ አሁን ደግሞ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ መወዛገብ ጀመሩ። የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ፕሪቶሪያ የተላከው ልዑክ ያልተወያዩበትን መስማማቱን ሲገልጹ፣ ልዑኩን የመሩት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ልዑኩ ወደ ፕሪቶሪያ የሄደው ስለመንግሥትነት ጉዳዮች ለመወያየት ሳይሆን ተኩስ ለማስቆም መሆኑንና በዚያው መሠረት ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን አስታውቀዋል። ሕወሓት ስምምነቱን እንዲፈርሙ የመረጣቸው ልዑካን ስህተት መፈጸማቸው የተናገሩት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት መጀመር የነበረበት ፖለቲካዊ ውይይት እስካሁን አለመጀመሩንና የክልሉም ሉዓላዊነት አለመረጋገጡን አስታውቀዋል። አቶ … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ፍልሚያ