እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
zeray
የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ
ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ የነበረው ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣኑ ተነስቷል። አንደበቱ በቅጡ ያልተገራና ፍጹም የህወሓትን ዓላማ በአደባባይ በማስፈጸም የሚታወቀው ዘርዓይ፤ ከዚህ እንደፈለገ ከሚነዳው መ/ቤት መልቀቁ በሚዲያው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ ታላቅ አዎንታዊ እርምጃ ተወስዷል። አንዳንድ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በላይ በቀለ፣ መሠረት አታላይ፣ ዮናስ ዲባባ፣ አስካለ በላይ፣ ካሳሁን ፈይሳ፣ እና ሌሎችም የሙያው ሰዎች በዚሁ የህወሓት ተጋዳላይ ትዕዛዝ ከሥራቸው እንዲለቁ መገደዳቸው ይታወቃል። ዘርዓይ በሥልጣን በቆየባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የነበሩ ሲሆን በክልላዊ ነጻነት የሚንቀሳቀሱትን የአማራ ሚዲያና የኦሮሚያ … [Read more...] about የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ