ህወሓት – ጨቋኝ ቡድን ወይስ ወራሪ ጠላት? 1) ጨቋኝ ቡድን እና ወራሪ ጠላት አንድ መንግሥት በሚመራው ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ በጭካኔ የተሞላ ግፍና በደል የሚፈፅም የፖለቲካ ቡድን አምባገነን ወይም ጨቋኝ ብቻ ሊባል አይችልም። የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት በሚያፈርስ መልኩ ዘረፋና ሌብነት የሚፈፅም ቡድን ሙሰኛ ወይም በዝባዥ ብቻ ሊባል አይችልም። እንደ ህወሓት በሰው ልጅ ላይ ጨካኝ እና በሀገሩ ላይ ዘራፊ የሆነ መንግስት ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። አብዛኞቹ አምባገነን መንግስታት በዜጎች ላይ ግፍና በደል የሚፈፅሙት የሀገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር በሚል ሰበብ ነው። ስለዚህ በዜጎች ላይ ጨቋኝ እና ጨካኝ ቢሆኑም ለሚመሩት ሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት በፅናት የሚታገሉ ናቸው። በሌላ በኩል ለሚያስተዳደሩት ሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት ደንታ-ቢስ የሆነና በዜጎች … [Read more...] about “የስብሃት ማፊያ ቡድን” – ህወሓት መፍረስ፤ EFFORT መወረስ አለበት
seyoum
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል። የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ