"እናንተ የመለስናችሁ ለእረፍት እንጂ ጥያቂያችን መቋጫ አግኝቶ ትግል ስላበቃ አይደለም ። የወልቃይት-ጠገዴ ነፍጥ ገና ይጠብቃል እንጂ አይወርድም። እኔ በዚህ እድሜዬ ጋቢ ለብሼ ከዘራ ይዤ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነበር የሚያምርብኝ። ነገር ግን አሁንም በዚህ እድሜዬ ጠበንጃ ተሸክሜ የምታዩኝ የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ስለሆነ ነው። ጥያቄው እልባት ሲያገኝ እናንተም በሙሉ ልብ ወደ ልማታችሁ እኔም ገዘራ ይዤ ጋቢ ለብሸ የምሄድ ይሆናል"ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱየወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ሃላፊ "የወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ሲኖርም በምክንያት ሲሞትም በምክንያት ነው። አሁን እየተዳደርን ያለነው በምንፈልገው የቤጌምድር አማራ ማንነት ነው። በዚህም እንቀጥላለን። በህግ ጥያቄ ያለው ካለ በህግ ይጠይቀን።በህዝብ ፍላጎት መሰረት እስከሆነ ድረስ አስተዳደራችንም ድሮም … [Read more...] about የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ነው
demeke
ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
የህወሓት ዘመን ማብቂያው አካባቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ካለ በኋላ ለጠ/ሚ/ር ቦታ በተደረገው ሽኩቻ ዶ/ር ዐቢይ (የለማ ቡድን) አሸንፎ በወጣ ጊዜ የህወሓት ቡድን ወደ መቀሌ ሄዶ ሲመሽግ ስብሃት ነጋ በተፈጠረው ተናድዶ የሚከተለውን መናገሩ ታማጭ የመረጃ ምንጫችን አስታውቆናል። ስብሃት ነጋ በትግሪኛ የተናገረውና በአማርኛ ተተርጎመው የስብሃት ንግግር እንዲህ ይነበባል፤ “(ደመቀ) ለትህነግ ታማኝና ታዛዥ ነበር። ፈፅም! የተባለውን ነገር ለመፈፀም 'ለምን?' ብሎ እንኳን አያውቅም። አንድ ቀን ግን የሱዳን ግዛት የሆነውን አዋሳኝ መሬት ለመስጠት ‘ፈርም’ ሲባል ‘አይሆንም አልፈርምም!’ ብሎ አሻፈረኝ ሲል ያኔ ይህ ሰው አንድ ቀን እንደሚሸውደን እርግጠኛ ሁኜ ለጓዶቼ ነግሬያቸው ነበር። ሁሉም የእኔን እይታ ሳያቅማሙ ሲቀበሉኝ ጌታቸው (አሰፋ)ግን ‘አታስብ እሱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል። የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ