የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች መምጣት አለመምጣት በአገራዊው የምርጫ ሂደት ላይ የሚያሳድረው አንዳችም ተጽዕኖ እንደሌለ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)ፕሬዚዳንትና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስታወቁ ። ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች መምጣት አለመምጣት በአገራዊው የምርጫ ሂደት ላይ የሚያሳድረው አንዳችም ተጽእኖ የለም፤ ምክንያቱም ታዛቢዎች ባሉበት ባለፉት ምርጫዎች ወቅትም ውዝግብን ከመጫር ባሻገር የፈየዱልን አንዳችም ነገር የለም። በተለይም በ1997ቱ ምርጫ ወቅት የአውሮፓ ህብረት ታዘብኩ ብሎ ያወጣው መረጃ እንደ አገር ብዙ ዋጋ የከፈልንበት ብዙ ትርምስ የተፈጠረበት ከመሆኑ አንጻር አሁን ላይ አንመጣም ማለታቸው የሚያጎለው አንዳችም … [Read more...] about “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ውዝግብን ከመጫር ባሻገር የፈየዱልን አንዳችም ነገር የለም” ፕ/ር በየነ
beyene
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል። የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ