• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

November 12, 2012 06:41 am by Editor 1 Comment

ኢህአዴግ በ “ልማት ሠራዊት” ግንባታ ችግር ገጠመኝ አለ

ኢህአዴግ በልማት ሠራዊት ግንባታ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ። ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በብአዴን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቁት አሁን የተፈጠረው ስሜት “መነቃቃት ነው” ካሉ በኋላ “መነቃቃት በመፈጠሩ የተሰራው ስራ የዘመቻ ነው” ብለዋል። አቶ ደመቀ “የአመለካከት ችግር አለ” በማለት የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደተጋረጠበት አመልክተዋል።

የብአዴንን ግምገማ ከፋፍሎ ካሳየው የአማራ ቴሌቪዥን ለመረዳት እንደተቻለው አቶ በረከት ስምኦንም አቶ ደመቀን አግዘዋል። ከ2003 ጋር ሲነጻጸር በተጠናቀቀው ዓመት የተሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው “የልማት ሰራዊት ግን አልፈጠርንም” ብለዋል። የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና ምክትል ር/መስተዳድር አቶ ጉዱ አንዳርጋቸው “የተጀመረው ልማት ሊቀጥል አይችልም የሚል ጥርጥር አለ” ሲሉ ተደምጠዋል። በማያያዘም “በዚህ ዓመት የልማት ሰራዊት መገንባት የህልውና ጉዳይ ነው” የሚል ፖለቲካዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ ደቡብ ክልል ደኢህዴን ባካሄደው ግምገማ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊው “የመንግሥት ሠራተኛው አንድ ለአምስት እንዲደራጅ ሲጠየቅ ‘ፖለቲካ ውስጥ አታስገቡን’ በማለቱ የልማት ሰራዊት ግንባታው ችግር እንደገጠመው ገምግመናል” ማለታቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ቀንጭቦ ካቀረበው ፕሮግራም ለማዳመጥ ተችሏል።

በተመሳሳይ ኦሮሚያን ይመራል የሚባለው ኦህዴድም ባጋጠመው የውስጥ “መባላት” ከላይ የወረደውን አደረጃጀትና በልማት ሰራዊት ግንባታ ስም የሚዘረጋውን የቁጥጥርና የስለላ ሰንሰለት መተግበር አለመቻሉ ታውቋል። “የአቶ መለስን ውርስ እንከተላለን፣እናስጠብቃለን” በማለት የተማማሉት የኢህአዴግ የበላይ አመራሮች በከፍተኛ ደረጃ ችግሩን ማመናቸውና ራሳቸው ማንጸባረቃቸው ፖለቲካዊ ትርጉም እንዳለው አስተያየት ተሰጥቶበታል። ከመለስ ሞት በኋላ በኢህአዴግ ውስጥ የተከሰተውን ከፍተኛ ክፍተትና የአመራር መላላት እንደሚያሳይም ተጠቁሟል፡፡

“ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ” እስክንድር ነጋ

(በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

ከነገ በስቲያ (ማክሰኞ ህዳር አራት) በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ይሰየማል፡፡

በትላንትናው ዕለት የክስ ቻርጅና መንግስት እወርሳቸዋለሁ ያላቸውን የእስክንድር ሁለት ቤቶች ካርታ የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል፡፡ (በነገራችን ላይ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ቤቶች አንዱ በእናቱ ስም ያለ ሲሆን የዛሬ ዓመት አካባቢ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የቤቱን ስም ለማዞር ፈልጋ “ካርታው የለም” በሚል አንዴ ቀበሌ፣ ሌላ ጊዜ ክፍለ ከተማ፣ ቀጥሎ አዲስ አበባ መስተዳደር ስትመላለስ ከርማ ሊገኝ ስላልቻለ ሰልችቷት ትታው ነበር፡፡ ትላንት ግን ዓቃቤ ህግ ከክስ ቻርጁ ጋር አያይዞ አቅርቦታል፤ እናም ምናልባት ያን ጊዜ “ካርታው የለም” የተባለው ሆነ ተብሎ ተደብቆ ሊሆን ይችላል።)

የሆነ ሆኖ እስክንድር ማክሰኞ ፍርድ ቤት ቀርቦ “ቤቴን አትውረሱብኝ” ብሎ ስለማይከራከር “በዕለቱ ፍርድ ቤት መሄድ አልፈልግም” ሲል ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ ግን “የግድ ማቅረብ ስላለብን ይዘንህ እንሄዳለን” የሚል ምላሽ ሰጥተውታል፡፡ እናም እስክንድር በዕለቱ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም አይነት ምላሽ ላለመስጠት ወስኗል፡፡ ባለቤቱም “የሚስትነቴን ድርሻ አትውረሱብኝ” ብላ አትከራከርም፡፡ ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ይወስን የሚል አቋም ነው ያላት፡፡

በዛሬው ዕለት ሊጠይቀው ቃሊቲ የመጣውን የሰባት ዓመቱን ህፃን ልጁን ጠባቂ ፖሊሶች እየሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ፡፡ አይዞህ! ስርዓት ተቀያየሪ ነው፤ ንጉሱ የወረሱት በደርግ ተመልሷል፤ ደርግ የወረሰው በኢህአዴግ ጊዜ ተመልሷል፤ ኢህአዴግ የወረሰው ደግሞ ኢህአዴግ ሲወድቅ መመለሱ አይቀሬ ነው” ብሎታል፡፡ በ1993 ዓ.ም ግምቱ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የእስክንድር እናት ቤት በግፍ እንደተወረሰ ይታወቃል፡፡
ዜናውን ያደረሱልን ጋዜጠኛ ተመስገን በመጨረሻ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ “እስቲ አሁን እንኳን ምንአለበት ትንሽ እንደ ሰው አስባችሁ ልጁን የሚያሳድግበትን ንብረት ብትተውለት? … ዛሬም በትላንቱ መንገድ፣ ዛሬም በመለስ ጫማ፣ ዛሬም በመለስ ራዕይ… አቤት! እንዴት ልብ የሚያደማ ነገር ነው! ይህ ምን አይነት ጭካኔ ነው?” ብለዋል።

ስዩም መስፍን ታመዋል

በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ አምባሳደር ስዩም መስፍን በጠና መታመማቸውን የኢሳት ሬድዮ አስታወቀ። ኢሳት የአይን እማኞችን በመጥቀስ እንደዘገበው አቶ ስዩም ሲያትል አብዛኛውን የካንሰር ታካሚዎች በሚስተናገዱበት የራዲዮሎጂ ህክምና መስጫ የወረፋ መጠበቂያ ክፍል ውስጥ ከጠባቂዎቻቸው ጋር ታይተዋል።

በወቅቱ ጉዳት ይታይባቸው እንደነበር ያስታወቀው ኢሳት ሬዲዮ ያነጋገራቸው የቀድሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሠራተኛ የሆኑት አቶ ሙሉነህ ዮሃንስ እንዳሉት አቶ ስዩም በሽታቸውን ተኝተው እንዲከታተሉ ተደርጓል። ሲያትልን በተለይ የመረጡበትን ምክንያት እንዲያስረዱ ለተጠየቁት አቶ ስዩም ቀደም ሲል ሲያትል ቤት እንዳላቸው በስፋት ሲነገርባቸው ስለነበር ከዚያ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ሰጥተዋል። አቶ ስዩም ለሃያ ዓመት ያህል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ።

የአባይ ግድብ ሰራተኞች አመጹ

“የባንዲራ ፕሮጀክት” በመባል የሚታወቀው የአባይ ግድብ ሰራተኞች ከክፍያና ከተለያዩ አገልግሎት መጓደል ጋር በተያያዘ የስራ ማቆም አድማ አድርገው እንደነበር ኢሳት አስታውቋል። ኢሳት በዘገባው ሰራተኞቹ በማስፈራሪያ ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክቷል።

ፕሮጀክቱን ያለጨረታ የተረከበው የሳሊኒ ኮንስትራክሽን “ከግብጽ ጋር የተመሳጠረ” በሚያስመስል መልኩ ስራውን እያጓተተ እንደሆነ በስፍራው የሚሰሩትን በመጥቀስ የኢሳት ቴሌቪዥን የግድቡ ግንባታ አሁን ባለው ይዞታ በሃያ ዓመት እንኳ ሊያልቅ እንደማይችል አመልክቷል። መንግስት ፕሮጀክቱ በሰባት ዓመት ይጠናቀቃል ማለቱ ይታወሳል።

ደምሴ ዳምጤ አረፈ

ለሃገሩ ባለው ፍቅር የሚታወቀው አንጋፋ የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ በሳምንቱ አጋማሽ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። ላለፉት አራት አስርተ ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ አገልግሎት የሰጠው ደምሴ ዜና እረፍቱ እንደተገለጸ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ በተለያዩ ድረገጾች ምስሉን ከኢትዮጵያ ሠንደቅዓላማ ጋር በማሳሳም ሃዘናቸውን ገልጸውለታል።

በአገር ቤትና በውጪ አገር የሚገኙ መገናኛዎች ሰፊ ሽፋን የሰጡት የደምሴ ዳምጤ ህልፈት ብዙዎችን አሳዝኗል። ኢትዮጵያ ስታሸነፍ ሳግ እያነቀው የሚዘግበውና በቀጥታ ስርጭት በርካታ ውድድሮችን ያስተላለፈው ደምሴ በአገራችን ስፖርት መውደቅ ክፉኛ ያዝን ነበር፡፡ አንዳንዴ ሲብስበት የሚያቀርባቸው ሃዘን ተሞላባቸው ሪፖርቶቹ አገር ወዳድነቱን የሚመሰክሩለት ናቸው።

ዘመኑን ለውጪ አገር ሳይሆን ለአገር ውስጥ ስፖርት ትኩረት በመስጠት ያሳለፈው ደምሴ ዳምጤ የእውቁን ጋዜጠና ሰለሞን ተሰማ ፋና ተከትሎ ሙያውን በብቃት የተወጣ ታታሪ ኢትዮጵያዊ ነበር። ኢትዮጵያን ማስቀደምና አገርን ማክበር፣ ብሎም ለሠንደቅዓላማ ክብር መስጠት ማለት እንዴት እንደሆነ ያስተማረው ደምሴ የሶስት ልጆች አባት ነበር። ደምሴ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ታዋቂ ስፖርተኞች፣ ባለስልጣናትና አድናቂዎቹ በእንባ አጅበውት በክብር ስላሴ ካቴድራል እንዲያርፍ ተደርጓል። ያለ ማስታወቂያና ቅስቀሳ በደምሴ የቀብር ስነስርዓት ላይ የተገኙት ወገኖች ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ ሲሆን የተበረከተለት አበባ ለቁጥር የሚታክት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የደምሴ የቀብር ስነስርዓት “በሰው መወደድን በተግባር ያሳየ” ተብሏል።

መድረክ በምርጫ ጉዳይ ማሳሰቢያ ሰጠ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ኢህአዴግ አካሄድኩ ያለውን ሽግግር “ምደባና ሽግሽግ” ሲል ወርፎታል። መድረክ ባለፈው ዓርብ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጸው ምደባው የመተካካት ይዘትና ቅርጽ የለውም በማለት መናገሩን የዘገበው የሪፖርተር የእሁድ እትም ጋዜጣ ነው። መድረክ በመግለጫው አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትርም ከመለስ ጋር አመሳስሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በሥልጣን ዘመናቸው “አፋቸውን አስያዟቸው” ለመባል በፓርላማ ንግግራቸው “እጅ እንቆርጣለን” የመሳሰሉ ማስፈራሪያ አዘል ንግግሮች ሲያደርጉ መኖራቸውን ያወሳው መድረክ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር በመድረክ ላይ “እሳት መርገጥ ነው” የሚል ንግግር ማድረጋቸው፣ “እውነትም የታላቁ መሪያቸውን ፈለግ ሳያዛንፉ መከተላቸውን ያሳያል” ብሏል፡፡

መድረክ በመግለጫው ትኩረት የሰጠው ሌላ ጉዳይ የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅን በተመለከተ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት ግንባሩ አዋጁን ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ሳይሆን መቀጠሉን ነው፡፡ አሁንም በቅርቡ በናዝሬት (አዳማ) በተደረገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ጉባዔ ላይ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተስማምተውታል ተብሎ በመንግሥት ሚዲያ የቀረበውን የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ፣ የመድረክ የአመራር አባል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ግልጽ የሆነ ማደናገሪያና ቅጥፈት ብለውታል፡፡ በዚሁ የማደናገሪያ ስልት መሠረት ኢህአዴግ ቀደም ሲል በፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲፈረም ያቀረበው ሰነድ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎችን ቆርጦ መሆኑን ገልጸው፣ በምርጫ 2002 ምርጫውን ለማጭበርበር የተጠቀመበት መሣርያ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ “የዚሁ የቅጥፈት ስልት ሰለባ አንሆንም” በማለት፡፡

አሁንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በማስገንዘብ መድረክ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ሲያቀርበው የቆየው ጥያቄ ችላ መባሉንም በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ ኢህአዴግ ቀድሞውንም ይታወቅባቸዋል ያላቸውን ከአሥራ አንድ በላይ ያለ አግባብ በሥልጣን መገልገል ተግባራት ዘርዝሮ በመግለጫው ላይ አስፍሯል፡፡

በሕጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ላይ የሚያካሄደው አፈናና ሥርዓት አልበኝነት ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ በመላ አገሪቱ “አንድ ለአምስት” በሚል አደረጃጀት አንዱ ሌላውን እንዲሰልለው እየተደረገ መሆኑን፣ ሥራ ፈላጊ ምሩቅ ወጣቶች በመንግሥት ተቀጥረው እንዲሠሩ በሊግ ወይም በፌዴሬሽን መደራጀታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ መመርያ መተላለፉን መድረክ ከጠቀሳቸው ከቀዳሚዎቹ መካከል ናቸው፡፡

በፕሬስ ነፃነት ላይ እየተወሰዱ ያሉ ሕገወጥ ያላቸውን ተግባራት፣ በሐሰት ክስ በሽብርተኝነት ስለተከሰሱ የፖለቲካ እስረኞች፣ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መደረጉንና ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች አግባብ ያለው መፍትሔ አለመሰጠቱም ከዝርዝሮቹ መካከል ናቸው፡፡ “ሕገወጥ ግንባታ” በሚል ሰበብ በውድቅት ሌሊት ቤት የማፍረስ የጭካኔ ዕርምጃ ተፈጽሞባቸዋል ያላቸውን የአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎችን የጠቀሰ ሲሆን፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬት በነፃ ሊባል በሚችል ክፍያ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑን በመግለጫው ላይ አስፍሯል፡፡ መድረክ ስለ ነጻ ፕሬስ፣ ስለ ኑሮ ውድነትና ዋጋ ግሽበት አጽንዖት በመስጠት ማሳሰቢያውን አስተላልፏል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: beyene, demeke, demissie, eskinder, medrek, Right Column - Primary Sidebar, seyoum

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    November 12, 2012 08:07 pm at 8:07 pm

    This puppet of woyane ethnic fascists sold/give away Ethiopian land for Sudan and now as a deputy Prime Minister for sure he will loot and terrorize more. The hat he is wearing symbolizes how he is hodam and trying in all means loyality to his masters – woyane ethnic fascists

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule