“አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። ቃፍታ ሁመራ ከተማ ከሀዲው የህወሓት ጁንታ ነጻ ከወጣች ሶስት ሳምንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣ ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል። ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን … [Read more...] about የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
wolkayit
“ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመገኘት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥያቄያችን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸወን አሰምተዋል። ነዋሪዎቹ በህወሃት የግፍ አገዛዝ በጉልበት ወደትግራይ ክልል ተካለው ሲፈፀምባቸው የቆየው ግፍ ይበቃል ብለዋል። በዚህ የህልውና ጉዳይ በሆነው የህዝብ ትእይንት የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሠብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልእክት አስተላልፈዋል። ኮሎኔል ደመቀ ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጅ ሠጥተን አንጠይቅም ብለዋል። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጉዳይ ሌላ ጁንታ አይኖርም ብለን ሳንዘናጋ ሁላችንም … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ
ወልቃይት እንደ ካሽሚር
የወልቃይት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እና የዋልድባ መነኮሳትን ጨምሮ ከመቶ በላይ ከእስር ቤት የተለቀቁ የዴሞክራሲና የፍትህ ተቆርቋሪ ታጋዮች በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገላቸው የክብር ራት ግብዣ ላይ የተገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለታዳሚው ያደረገውን ንግግር ከተመስገን ባገኘነው ፈቃድ መሠረት ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አንባቢያን እንደወረደ በሚከተለው መንገድ አቅርበነዋል። በዕለቱም ለህሊና እስረኞች የተለያየ ስጦታም እንደተበረከተ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። እዚህ የተሰበሰባችሁ ታላላቆቼም፣ ታናናሾቼም በመጀመሪያ እንኳን ለዚህ ዕለት አበቃችሁ፤ አበቃን። በተለይም ባለፉት ሁለት አስርታት የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት፣ የፍትሕ፣ የዴሞክራሲ እና የፖለቲካ ጥያቄ አደባባይ እንዲወጣ በተወለዳችሁበት አፈር ላይ ተተክላችሁ ለከፈላችሁት ውድ ዋጋ ጥልቅ … [Read more...] about ወልቃይት እንደ ካሽሚር
ጠ/ሚ/ር አብይ “የወልቃይት ኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል”
“እኛ ትግሬ አንጠላም፣ እነሱ ግን አሁም ያሳድዱናል። ለምን ያሳድዱናል?” የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ በመቀሌ ንግግር ከፍተኛ አቧራ ያስነሳውን የወልቃይትን ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከኮሚቴው አባላት ጋር በመነጋገር መቁዋጫ አድርጎለታል። በቅድሚያ ጎንደር ላይ ባደረገው ንግር ይህንን ብሎ ነበር፤ "የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት። ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል። በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን። ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል”። ከማህበራዊ ድረገጽ በተገኘ መረጃ ደገሞ ከወልቃይት ኮሚቴ አባላት ጋር … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር አብይ “የወልቃይት ኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል”