• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

November 15, 2022 01:54 pm by Editor Leave a Comment

በዛሬው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስለ ወልቃይት የተናገሩት፤

“ወልቃይትን በሚመለከት የሚነገሩ ሽረባዎች፣ ሴራዎች፣ conspiracies ብዙ እሰማለሁ። የኢትዮጵያ መንግስት በእነዚህ ሽረባዎች ውስጥ እጁ የለበትም። የወልቃይት ህዝብ እንዲገነዘብ የምንፈልገው፤ የሚወራው፣ የሚናፈሰው አሉባልታ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጁ የለበትም።”

“እኛ ደቡብ አፍሪካ የሄድንው ወልቃይት ወደ አማራ ይሁን ወደ ትግራይ ይሁን የሚለውን ለመወሰን አይደለም። የፕሪቶሪያው ‘ሰሚትም’ ይኸን ለመወሰን ስልጣን የለውም። ምን አገባው እና ነው የኢትዮጵያን መሬት እዚያ ሂድ እዚህ ሂድ የሚለው? እኛ እዚያ የሄድንው እንዴት ሰላም አምጥተን በንግግር ችግሮቻችንን እንፍታ ለማለት ነው። ለምን ወልቃይት ተስቦ እዚያ ውስጥ እንደሚገባ አላውቅም።”

“ወልቃይት ብቻ አይደለም፤ ሰሜን ሸዋ ላይ ኦሮሚያ እና አማራ ጥያቄ አላቸው። እሱም ደቡብ አፍሪካ ይሂድ? ሲዳማ እና ወላይታ፤ ብላቴ ላይ ጥያቄ አላቸው። እሱም ደቡብ አፍሪካ ይሂድ? ቦታው አይደለም። የተስማማነው በኢትዮጵያ ህግ እና ስርዓት ይፈጸም ነው።

“ከህገ መንግስት በፊት ነው የተወሰደው፤ በጉልበት በው የተወሰደው” ላሉት፤ የእኔ ፍላጎት ያ ስህተት እንዳይደገም ነው። ዛሬ እኔ በጉልበት፤ ነገ ታገሰ በጉልበት ከሆነ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። ወልቃይት ብንፈልግም ባንፈልግም የተወላገደ አማርኛ፣ የተወላገደ ትግርኛ የሚናገር፤ የሁለቱ ህዝቦች ድልድይ የሆነ ህዝብ ነው። ሁለቱንም ቋንቋ የሚናገር የተጋባ የተዋለደ ህዝብ ነው። ‘ወልቃይቴነቱን ነው አትንኩብኝ’ ያለው እንጂ ከእንግዲህ በኋላ ትግራይ ከሚባል ጋራ አልገናኝም፤ አልነጋገርም አላለም። ቢልም አይችልም።

“ይህን በህግ እና በስርዓት ብንፈጽም ለወልቃይት ይጠቅማል። ለአማራ ይጠቅማል። ለትግራይ ይጠቅማል።  የሚጎዳው ነገር የለም። በህግ እና ስርዓት እንፈጽም የሚለውን ነገር ከብዙ ተንኮል ጋር ማያያዝም አስፈላጊ አይደለም። እዚያ አካባቢ ጥያቄ ረዘም ላለ ጊዜ ነበረ። ከዚህ ቀደም ኮሚሽን ያቋቋምነው ለዚያ ብለን ነው። አሁንም ያኔም የነበረን አቋም በህግ አግባብ በምክክር በውይይት ይፈታ የሚል ነው።”

“ከአማራ ወገን ላለፉት 30 ዓመታት ብዙ ወልቃይቴዎች ሲፈናቀሉ፤ ሲሰደዱ ኖረዋል። እነሱ በሌሉበት ህዝበ ውሳኔ ቢባል፤ የተመናመነ ህዝብ ነው እና እንጎዳለን። በትግራይ በኩል አሁን በተፈጠረው ግጭት ብዙ ሰው ወጥቷል። ስለወጣ አሁን ባለው ቢወሰድ አማራ ክልል አድቫንቴንጅ ይወስዳል የሚሉ ስሞታዎች ይሰማሉ። ወልቃይቴ፤ ወልቃይቴ ነው፤ ይታወቃል። ከአድዋም የሄደ፤ ከደብረ ማርቆስም የሄደ ሰው ሊኖር ይችላል። ግን ወልቃይቴ ይታወቃል። አትላንታም ይኑር፣ አውስትራሊያም ይኑር፣ ጅማም ይኑር፤ ስለዚያ ቦታ ሀሳብ እንዲሰጥ ዕድል ካልተሰጠው በስተቀረ ዘላቂ ሰላም አያመጣም።

ጉዳዩ ወደዚያ ስለሄደ ወደዚህ ስለመጣ ሳይሆን ያ ህዝብ የራሱን ዕጣ ፈንታ እንዲወስን፤ ዲሞክራሲያው ዕድል እንዲያገኝ ማድረግ ከቻልን ብቻ ነው መፍትሔ የሚመጣው። እነዚያን ችግሮች በሚቀርፍ መንገድ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ። ጊዜ የወሰድንው፤ ጊዜ የጠበቅንው ለዚያ ነው።

ከህገ መንግስት በፊት ህወሓት በግድ ስለወሰደ አሁን እኛ ደግሞ በግድ ወስደን፤ እዚያ ዘመኑን በሙሉ ወታደር ልናቆም አንችልም። በስምምነት ካልሆነ በወታደር ነው የሚሆነው። በወታደር ከሆነ ዘላቂ አይሆንም። ጊዜ ይፈታዋል። አሁን ያለን ሰዎች ስናረጅ፣ ስንደክም፤ ልክ አሁን የተፈጠረው ይፈጠራል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: wolkayit

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule