በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዱ መሪዎች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል። በሥልጠናው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው፣ የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ የዞኑ መካከለኛና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። ሥልጠናው በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ ሕዝቡን ለማገልገል እና የጸጥታ መዋቅሩን አደራጅቶ ለመደገፍ እና ለመምራት ዓላማ አድርጎ መሰጠቱ ተገልጿል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የተደራጀና የተቀናጀ ሕዝብ ችግሮችን መቋቋምና ፈተናዎችን ማለፍ ይችላል ብለዋል። ለዚህም ከላይ እስከ ታች ያለውን መሪ ወታደራዊ … [Read more...] about ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ
Tekeze Guard
የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የቃብትያ ሁመራ ወረዳና የዞኑ “የተከዜ ዘብ” በባለፉት ሳምንታት ሲሰለጥኑ የቆዩትን ሰልጣኞች በዛሬ ቀን በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ፣ የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተመርቀዋል። ወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት መጠበቂያ መሠረት ናት። ከጥንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሏል። በተከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር ሉዓላዊነት ከነክብሩ ኖሯል። ኢትዮጵያውያን ለነፃነታቸው እና ለሉዓላዊነታቸው በአንድነት እና በኅብረት እየተነሱ ጠላታቸውን ድል ሲመቱ ኖረዋል። ድል ማድረግ የኢትዮጵያውያን የሥነ-ልቦና እና የባህሪ … [Read more...] about የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ