
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የቃብትያ ሁመራ ወረዳና የዞኑ “የተከዜ ዘብ” በባለፉት ሳምንታት ሲሰለጥኑ የቆዩትን ሰልጣኞች በዛሬ ቀን በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ፣ የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተመርቀዋል።
ወልቃይት ጠገዴ የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት መጠበቂያ መሠረት ናት። ከጥንት እስከ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አያሌ መስዋዕትነት ተከፍሏል።
በተከፈለው መስዋዕትነትም የሀገር ሉዓላዊነት ከነክብሩ ኖሯል። ኢትዮጵያውያን ለነፃነታቸው እና ለሉዓላዊነታቸው በአንድነት እና በኅብረት እየተነሱ ጠላታቸውን ድል ሲመቱ ኖረዋል።
ድል ማድረግ የኢትዮጵያውያን የሥነ-ልቦና እና የባህሪ መገለጫ ነው። የጎንደር አማራዎች ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ጀግኖች ለዘመናት የሀገራችን ጠረፍ የሚጠብቁ፣ የሀገራቸውን የአኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠብቁ፣ የጭንቅ ዘመን መከቶች ናቸው።
ለዘመናት የሀገር ጠረፍ ጠባቂዎች ኾነው ኖረዋል። ዛሬም እኛ ልጆቻቸው እንደ አባቶቻችን ሁሉ የተከዜ ዘቦች የኢትዮጵያ ጽኑ ጠረፍ ጠባቂዎች ሆነን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በጽናት ቆመናል።
የሀገር ሉዓዊነት መጠበቅና ማስጠበቅ ከአባቶቻችን የወረስነው የጀግንነት እና የቃል ኪዳን ውርስ ነው። የአባቶቻችን ውርስ የሆነውን ሉዓላዊነት መጠበቅ፣ የሀገር ዳር ድንበር ማስከበር በደጀንነትና በጀግንነት አፅንተን እናኖረዋለን።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ህዝብ በጎንደር አማራ ማንነት፣ በሉዓላዊነት፣ በኢትዮጵያዊነት እና በሀገር አንድነት አይደራደርም። ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ለሕዝብ አንድነት እና ለለወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት በጽናት ይቆማል።
ኢትዮጵያን ለማሳነስ አዲስ ታላቅ ሀገር ለመመስረትና ለመገንጠል የሚቃዡት ህወሃት-ትህነግና መሰሎቹን ይቃወማል። በጽናትም ይታገላል። የተከዜ ዘቦች፣ ጠረፍ ጠባቂዎች መሆናችንን በደምና በአጥንት እያስመሰከርን እንቀጥላለን።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና አንድነት የሚዳፈሩትን የሀገርና የሕዝብ ጠላቶችን ከጀግናው የሀገር መከላከያ ጋር ሁኖ ይታገላል። በአማራዊ ማንነቱ እና በነፃነቱ የሚመጡበትን ጠላቶቹን አይታገስም።
እጅ መንሳት እንጂ እጅ መስጠት የለም!!
ወልቃይት ጠገዴ ጎንደር ነው፣ ጎንደር አማራ ነው ፣አማራ ኢትዮጵያ ነው!!
(አቶ አሸተ ደምለው (በአብክመ የወልቃይት ጠገዴ ሰ/ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ – ከአስፋው አብርሃ ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply