ሰሞኑን በሸዋ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ባለበት እንደሚቀጥል፣ ሌሎች አደረጃጀቶች ለመቀላቀል ከፈለጉ በራሳቸው ተደራጅተው ወደ አሕፋድ እንዲመጡ ተጠየቀ። ከጥቂት ቀናት በፊት በሸዋ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱን እና ተዋጊዎችም መሞታቸውን በፋኖ ውስጥ ያሉት አዋጊዎች ገልጸዋል። ጉዳዩ የተከሰተው በደብረሲና አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የራምቦ ክፍለጦርን ወደ ሬማ እንዲሄድ በተደረገው ውሳኔ ነው። ውሳኔው የተላለፈው በወታደራዊ አመራሮች ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ የተፈጸመ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ሬማ በሚባለው አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው በአጼ ፋሲል ክፍለጦር ሥር የሚገኘው … [Read more...] about “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ
Eskinder Nega
ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ
የአማራ ፋኖዎች አንድ እየሆኑ ነው። ሆኖም አሁንም በእስክንድር ነጋ ከሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጋር በተገናኘ የተወሰኑ የፋኖ ወገኖችንም ማሰባሰብም ያስፈልጋል። እነ ኮሎኔል ፋንታሁን፣ እነ ሻለቃ መከታው፣ እነ ሻለቃ ከፍያለው ደሴ፣ እነ ሻለቃ ደረጄ በላይ የመሳሰሉትን። እነዚህ ወገኖች የህዝብ ፋኖዎች እንጂ የግለሰብ ክቡር ዘበኞች ባይሆኑ ጥሩ ነው። ለራሳቸው ሲሉ። ምን አልባት ከእስክንድር ነጋና ለእስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑ፣ በአገር ቤትም በውጭ አገር የሚገኙ፣ የተዛባ መረጃ ስለደረስቸው ይሆናል አሁን የያዙትን አቋም እየያዙ ያሉት። በዚህ ረገድ እነዚህ ወገኖች እውነታውን እንዲያውቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው። አሁንም "እስክንድር፣ እስክንድር" የምትሉ ወገኖች በጭፍንና በስሜት ሳይሆን ነገሮች በማስረጃ ማገናዘብ መጀመር አለባችሁ። እስክንድር ነጋ "አሜሪካ መኖር ሲችል … [Read more...] about ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ
ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!
የመሠረት ሚዲያ ባለቤት አቶ ኤሊያስ መሠረትን በስም ጠቅሶ የመንግሥት ተከፋይ እንደሆነ የፋኖ አንድ ክንፍ መሪ እስክንድር ነጋ በይፋ ተናገረ። እስክንድር “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ” ሲል አመልክቷል። እስክንድር ይህን ያለው ከEMS ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲሆን፣ መነሻው አቶ ኤሊያስ መሠረት በአባቱ ስም እንደሰየመው በሚገልጸው የግሉ ሚዲያ ላይ እስክንድርን ጠቅሶ “ከመንግሥት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ” በማለት ሪፖርት ማድረጉን ተከትሎ ነው። አቶ ኤሊያስ “መሠረት ሚዲያ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ በሠሩ እና አሁንም እየሠሩ ባሉ ጋዜጠኞች ሚዛናዊ፣ አዳዲስ እና ፈጣን መረጃዎችን ለአንባቢዎች ያደርሳል” በሚል መሪ እሳቤ እንደሚሠራ በማኅበራዊ ገጹ ላይ አስፍረዋል። እስክንድር ነጋ በቃለ ምልልሱ “ኤሊያስ … [Read more...] about ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!
ከትሕነግ ጋር ለማበር ወልቃይትን መስዋዕት የሚያደርጉ የ”አማራ ነጻ አውጪዎች”
ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ጋር አብሮ "የጠብ መንጃ ትግሉን ማጧጧፍ" በሚል ከውሳኔ የደረሱ ክፋይ የ"አማራ ነጻ አውጪ" ኃይሎች መኖራቸው ተሰማ። ለስምምነቱ ትሕነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለውንና አሁን "ነጻ ወጥቷል" የሚባለውን ወልቃይት ተላልፎ እንዲሰጥ ፈቃደኝነት ያለበት እንደሆነ ተመልክቷል። ራሳቸውን በተለያዩ አካባቢያዊና አደረጃጀት ከሰየሙት መካከል አሁን አንድ ለመሆን እየሠሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው በዝናቡ የሚመራው የጎጃም ዕዝና የዘመነ ካሴ ኃይል ነው ይህን ስምምነት ለማድረግ እየሠራ እንደሆነ የተሰማው። “ጊዜው አሁን ነው፤ ይህንን ጊዜ ልንጠቀምበት ይገባል” በሚል በገሃድ ወልቃይትን ዳግም በኃይል ለመያዝ ደብረጽዮን በቅርቡ መናገሩ ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሕዝብ ጋር በተለያዩ ከተሞች ውይይት ያደረገው ጌታቸው ረዳም “እኛ ሥራችንን መሥራት … [Read more...] about ከትሕነግ ጋር ለማበር ወልቃይትን መስዋዕት የሚያደርጉ የ”አማራ ነጻ አውጪዎች”