ሰሞኑን በሸዋ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ባለበት እንደሚቀጥል፣ ሌሎች አደረጃጀቶች ለመቀላቀል ከፈለጉ በራሳቸው ተደራጅተው ወደ አሕፋድ እንዲመጡ ተጠየቀ። ከጥቂት ቀናት በፊት በሸዋ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱን እና ተዋጊዎችም መሞታቸውን በፋኖ ውስጥ ያሉት አዋጊዎች ገልጸዋል። ጉዳዩ የተከሰተው በደብረሲና አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የራምቦ ክፍለጦርን ወደ ሬማ እንዲሄድ በተደረገው ውሳኔ ነው። ውሳኔው የተላለፈው በወታደራዊ አመራሮች ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ የተፈጸመ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ሬማ በሚባለው አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው በአጼ ፋሲል ክፍለጦር ሥር የሚገኘው … [Read more...] about “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ