እስካሁን በደቡብ ጎንደር እና በጎጃም 127 እጃቸውን ሰጥተዋል የመከላከያ ሠራዊት ባደረገው ተከታታይ ስምሪት ጠላትን በማሳደድ፣ በመክበብ እና በመደምሰስ ከፍተኛ ድሎችን አስመዝግቧል። በዚህ ኦፕሬሽን ክፉኛ አከርካሪው የተሰበረው ብረት ነካሽ ግማሹ ህይወቱን ለማዳን በየበረሀው ሲወሸቅ ቀሪው ደግሞ ለሠራዊታችን እጁን እየሰጠ ይገኛል። በጎጃም በሚገኙ አራት ዞኖች እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው ምስራቅ ዕዝ እና ተደራቢ ክፍሎች ከአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ጋር ባደረጋቸው ዘመቻዎች መላወሻ ያጣው የፅንፈኛው ቡድን ከግንቦት አንድ ወዲህ ብቻ 127 ታጣቂዎቹ ለወገን እጃቸውን ሰጥተዋል። እነዚህ ታጣቂዎች ሞርተር፣ ድሽቃ፣ ፒ ኬ ኤም/መትረየስን ጨምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን እና ትጥቆቻቸውን ጭምር በመያዝ ነው እጅ የሠጡት። በተለይም በጸዳሉ ደሴ የተመሩት … [Read more...] about በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ
Amhara Fano
የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ
የእስክንድር አፋሕድ ጥሪ አቀረበ ለበርካታ ወራት ኅብረት ለመፍጠር ታስቦ ሲሠራበት የቆየው የአማራ ፋኖ ኅብረት በቋራ ጎንደር መመሥረቱ ተሰምቷል። የኅብረቱ ዓላማና ግብ ወደ አንድነትን ለማምጣትና የተቀናጀ ጥቃት ለመሰንዘር ሳይሆን ዓቅምን አስተባብሮ ለድርድር ለመቅረብ የታለመ እንደሆነ እየተነገረ ነው። እስክንድር ነጋ የሚመራው አፋሕድ ባወጣው መግለጫ “ከተቻለ እንዋሃድ፣ ካልሆነም አንቀናጅ ካልሆነ ቢያንስ እናበብ” ብሏል። ከጎንደር፣ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎጃም የተሰባሰቡ የፋኖ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አንድ የፋኖ አደረጃጀት መመሥረታቸውን ተናግረዋል። ስሙንም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በማለት መሰየማቸውን አስታውቀዋል። የወጣው መግለጫ እንደሚለው “የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ - አማራ)፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የአማራ ፋኖ … [Read more...] about የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ
ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ
* ሸኔም ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል በሁሉም የጎጃም ዞኖች እና በደቡብ ጎንደር የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ክፍሎች በፋኖ ላይ በወሰዱት እርምጃ አመራሮችን ጨምሮ በርካታዎችን መግደላቸው፣ መማረካቸው እንዲሁም መሥሪያዎችንና ተተኳሾችን መማረካቸውን የመከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል። በሸኔም ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በ6ኛ ዕዝ የኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮን ጠቅሶ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ በፅንፈኛው እና አሸባሪው ሸኔ ላይ የምንወስደውን እርምጃ አጠናክረን ቀጥለናል አመርቂ ውጤትም ተገኝቷል ይላል የወጣው መረጃ። ከዚህም በተጨማሪ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ ሰሞኑን በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ እርምጃ በመውሰድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሣራ ማድረስ ተችሏል ማለታቸውን ዘግቧል። በፋኖ ላይ የደረሰውን በተመለከተ፤ መረጃው የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ … [Read more...] about ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ
“አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ
ሰሞኑን በሸዋ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ባለበት እንደሚቀጥል፣ ሌሎች አደረጃጀቶች ለመቀላቀል ከፈለጉ በራሳቸው ተደራጅተው ወደ አሕፋድ እንዲመጡ ተጠየቀ። ከጥቂት ቀናት በፊት በሸዋ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱን እና ተዋጊዎችም መሞታቸውን በፋኖ ውስጥ ያሉት አዋጊዎች ገልጸዋል። ጉዳዩ የተከሰተው በደብረሲና አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የራምቦ ክፍለጦርን ወደ ሬማ እንዲሄድ በተደረገው ውሳኔ ነው። ውሳኔው የተላለፈው በወታደራዊ አመራሮች ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ የተፈጸመ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ሬማ በሚባለው አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው በአጼ ፋሲል ክፍለጦር ሥር የሚገኘው … [Read more...] about “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ
ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ
የአማራ ፋኖዎች አንድ እየሆኑ ነው። ሆኖም አሁንም በእስክንድር ነጋ ከሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጋር በተገናኘ የተወሰኑ የፋኖ ወገኖችንም ማሰባሰብም ያስፈልጋል። እነ ኮሎኔል ፋንታሁን፣ እነ ሻለቃ መከታው፣ እነ ሻለቃ ከፍያለው ደሴ፣ እነ ሻለቃ ደረጄ በላይ የመሳሰሉትን። እነዚህ ወገኖች የህዝብ ፋኖዎች እንጂ የግለሰብ ክቡር ዘበኞች ባይሆኑ ጥሩ ነው። ለራሳቸው ሲሉ። ምን አልባት ከእስክንድር ነጋና ለእስክንድር ነጋ ቅርብ የሆኑ፣ በአገር ቤትም በውጭ አገር የሚገኙ፣ የተዛባ መረጃ ስለደረስቸው ይሆናል አሁን የያዙትን አቋም እየያዙ ያሉት። በዚህ ረገድ እነዚህ ወገኖች እውነታውን እንዲያውቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው። አሁንም "እስክንድር፣ እስክንድር" የምትሉ ወገኖች በጭፍንና በስሜት ሳይሆን ነገሮች በማስረጃ ማገናዘብ መጀመር አለባችሁ። እስክንድር ነጋ "አሜሪካ መኖር ሲችል … [Read more...] about ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ