
- እስካሁን በደቡብ ጎንደር እና በጎጃም 127 እጃቸውን ሰጥተዋል
የመከላከያ ሠራዊት ባደረገው ተከታታይ ስምሪት ጠላትን በማሳደድ፣ በመክበብ እና በመደምሰስ ከፍተኛ ድሎችን አስመዝግቧል። በዚህ ኦፕሬሽን ክፉኛ አከርካሪው የተሰበረው ብረት ነካሽ ግማሹ ህይወቱን ለማዳን በየበረሀው ሲወሸቅ ቀሪው ደግሞ ለሠራዊታችን እጁን እየሰጠ ይገኛል።
በጎጃም በሚገኙ አራት ዞኖች እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው ምስራቅ ዕዝ እና ተደራቢ ክፍሎች ከአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ጋር ባደረጋቸው ዘመቻዎች መላወሻ ያጣው የፅንፈኛው ቡድን ከግንቦት አንድ ወዲህ ብቻ 127 ታጣቂዎቹ ለወገን እጃቸውን ሰጥተዋል።
እነዚህ ታጣቂዎች ሞርተር፣ ድሽቃ፣ ፒ ኬ ኤም/መትረየስን ጨምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን እና ትጥቆቻቸውን ጭምር በመያዝ ነው እጅ የሠጡት።
በተለይም በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች በደቡብ ጎንደር ከሚገኘው ሠራዊታችን እና የመስተዳድር አካላት ጋር በመነጋገር ከነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም ገብተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመቀላቀል ሰላማዊ ኑሯቸውን ለመምራት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
በቀጣይም የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የጥፋትን መንገድ በመተው ሰላማዊውን መንገድ የሚመርጡ የጽንፈኛው ቡድን አባላት በየአካባቢው ለሚገኘው ሠራዊታችን እና አስተዳደር እጅ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። (ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ነው)።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Sectarianism, Tribalism, Racism And Hatefull Politicalily Motivated So Called Liberatiin Front Are Agents Of Colonial Puppets Infilitrators Organizing These Young People To Pay Sacrifices Other To Take Power. This Criminal Entities Should face Justice, Possiblly To They Kill, Rape and destroyed lifes who knows. Invistigations should be takes place before they released to public life.