በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የራዲዮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የተቋሙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት ነው ተመርቆ የተከፈተው። የመከላከያ ሰራዊታችን አገራችን በየጊዜው የገጠሟትን ፈተናዎች በሌሎች አገራት ቴክኖሎጂዎች ላይ በመመርኮዝ ግዳጅ እየተወጣ እንደዘለቀ አውስተው የተመረቀው የወታደራዊ ራዲዮ ፋብሪካ የሰራዊቱን የተልዕኮ አፈፃፀምና የግዳጅ ስምሪት የሚያቀላጥፍ እንደሆነ ተናግረዋል። "ወታደራዊ ራዲዮው በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ የመጨረሻው የዲጅታል ስታንዳርድ ራዲዮ ነው።" ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ይህንኑ እውን በማድረግ ረገድ የቻይናው ሀይቴራ ካምፓኒ እና የመከላከያ … [Read more...] about ዘመኑን የጠበቀ የወታደራዊ ሬዲዮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተከፈተ
endf
የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
በ116ኛው የሠራዊት ቀን ሲከበር ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበትን ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” በማለት ቀኑ ለምን እንደተመረጠ ይፋ አደረጉ። ከዚህ ሌላ ፊልድ ማርሻሉ በንግግራቸው፤ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ከጀግኖች የተረከብናትን ኢትዮጵያ እንደተከበረች እና ማንነቷ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል ወታደራዊ ዝግጁነታችንን አሳድገንና ቁመናችንን አዘምነን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አሣውቀዋል። የሠራዊቱ አባላት የተሠጣቸውን ታላቅ አደራ በድል ለመወጣት የመፈጸም ብቃታቸውን በማሣደግ በዓላማ ጽናታቸው እንዲቀጥሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳስበዋል፡፡ ሠራዊቱ ሀገሩን እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን … [Read more...] about የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
ጥቅምት 15 ለምን?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአዲስ መልክ ጥቅምት 15 ቀን ላይ መከበሩ ለምን እንደሆነ ከዚህ በታች ለመረዳት እንዲቻል በቀላሉ የተሠራውን መግለጫ ይመልከቱ። ስለ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማዕረግ ምልክቶች ምን ያህል ያውቃሉ? ከ"ፊልድ ማርሻል ጄነራል" ጀምሮ እስከ "ምክትል አስር ዓለቃ" ድረስ በአጠቃላይ 18 ማዕረጎች ይገኛሉ። የማዕረጎቹን ዝርዝር ከነምልክቱ እነሆ፦ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ጥቅምት 15 ለምን?
“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
"በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮ ለ116ኛው የሠራዊት ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የረዥም ዓመታት ሀገርን ከጠላት የመከላከል የተጋድሎ ታሪክ ካላቸው ሀገራት መካከል በጀግኖች ልጆቿ የአይበገሬነት ፊት የምትሠለፍ ታሪካዊት ሀገር ናት። ከቀደመው ዘመን ጀምረን አሁን ላይ ያለውን እውነታ እንኳ ብንቃኝ ኢትዮጵያ በርካታ የውጪ ወራሪ ሀገራት ያሠፈሠፉባት ጥቂት የማይባሉ የውስጥ እርስ በርስ ግጭቶች የተከሰቱባት በባንዳዎች የተፈተነችበትና በየትኛውም ዘመን ያልተንበረከከች የወራሪዎችን ፈተና አልፋ ዛሬ ላይ የደረሠች ሥለመሆኗ የታሪክ ድርሳናት መዝግቧል። በሀገራችን የጀግንነት የታሪክ መዝገብ ያልሠፈሩ ግን ደግሞ አለም ያወቃቸው ቱባ ባህሎችና ድንቅ ታሪኮች ያላት ኢትዮጵያ በታሪክ … [Read more...] about “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
“ውትድርና ሕይወቴ ነው”
ኢትዮጵያዊያን በሀገራችው ሰማይ ስር የመጣን ጠላት በማሽመድመድ ካስመዘገቡት ደማቅ ታሪክ ፊት ለፊት ትልቁን ድርሻ ከሚወስዱት አንዱ ናቸው። ለሀገራቸው በዋሉት ውለታ ከሚተረክላቸው ቀዳሚ ባለ ታሪኮች ቀድመው ይጠቀሳሉ። ሙሉ ህይወታቸውን ለሀገራቸው የሰጡ ናቸው። ጀግና ተዋጊ፣ የበቁ የጦር መሪ፣ የተሳካላቸው የጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል። በበርካታ የጦር ሜዳ ውጊያዎች ተሳትፈው የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የህዝብን ነፃነት ያስከበረ ደማቅ ድል አስመዝግበዋል። ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም። ጄኔራል መኮንኑ በ1934 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ከቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሲሰ መንደር ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም እዚያው እምድብር ከተማ ተምረው በ1948 ዓመተ ምህረትም አጠናቀዋል። ከ1949-1952 ዓ.ም ድረስ አምቦ የእርሻ ልማት … [Read more...] about “ውትድርና ሕይወቴ ነው”
መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው
አየር ኃይል የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አስተማማኝና ዘመናዊ አየር ኃይል የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ አየር ኃይሉ በሁሉም ረገድ በመዘመንና ስኬታማ በመሆን ሀገር የምትኮራበት ታላቅ ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ላይ በውጊያ መሠረተ-ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና አጠቃቀም በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን በተቋሙ የተለያዩ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስተማማኝ የሀገር መከታ በመሆን ለየትኛውም ግዳጅ አፈጻጸም ብቁና ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ዘመናዊ ተቋም የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በአየር ኃይል … [Read more...] about መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች
የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ያሠለጠናቸውን የመሠረታዊ ኮማንዶ አባላት አሥመርቋል።በዚሁ የምርቃት መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ከተናገሩት የተወሠደ፦ 👉 የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆን ያኮራል ፤👉 ሠራዊቱ ሁለት ዓላማዎች አሉት 1ኛ ጥፋት ውድመት እና ሌላ ክስተት እንዳይፈጠር ውጊያን ማሥቀረት 2ኛ ውጊያን መጨረስ ፤👉 ውጊያን ሠው ጀምሮ ሠው አይጨርሰውም የምንዋጋው በቴክኖሎጂ የምንጨርሰው በሠራዊቱ ነው ፤👉 ውጊያን ጨርሳችሁ ድል የምታደርጉት እና የኩሩ ህዝቦች መዝሙር የምትዘምሩት እናንተው ናችሁ ፤👉 ለሀገራችሁ ሶስት ነገሮችን ስጡ 1ኛ እንድታሥቡ አዕምሯችሁን 2ኛ ለሀገር ፍቅር ልባችሁን 3ኛ እንድትሠሩ እጃችሁን ፤👉 ኢትዮጵያ የሀገር ፍቅር እና የመለዮ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች
“ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
አሁናዊ የመከላከያ ሠራዊቱን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሠራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ መግለጫው በተለያዩ አካላት በሠራዊቱ ላይ እየተናፈሱ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የተሰጠ ነው ብለዋል። ሠራዊቱ ካለፉት ዓመታት በነበረበት ቁመና ላይ እንዳለ የሚያስቡ አካላት ካሉ የቆሙት እነርሱ እንጂ ሠራዊቱ ተራማጅ ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፣ ሠራዊቱ ዘርፈ ብዙ ግዳጁን እየተወጣ ነው ብለዋል። "ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ" የሚል አካል ላይ ሠራዊቱ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ሠራዊቱን መቋቋም ያልቻሉ አካላት በሠራዊቱ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት። በተለይ አሁን ላይ … [Read more...] about “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
“ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን”
”ነገሮች ተበላሽተዋል” በሚል የፋኖ አሰባሳቢ ኮሚቴ ናቸው የሚባሉት ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ከመስከረም ጋር በስልክ ያደረጉትን ንግግር ይፋ በሆነ ማግስት በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ። ክልሉን ጠቅሶ የአማራ ማስ ሚዲያ ይፋ እንዳደረገው በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ህይወታቸው ተመልሰዋል ብሏል። “ተታለን ነው” በሚል ሽማግሌ የላኩትን የሰሜን ወሎ ፋኖዎች ጥያቄ ለመቀበል የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ከዚህ በኋላ ምንም አይነት መንገድ እንዳይዘጋ፣ምንም አይነት የታጠቀ አካል ከተማ ውስጥ እንዳናገኝ … [Read more...] about “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን”
የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
የኮማንዶ ብርጌዱ የተሣካ የተልዕኮ አፈፃፀሙ ታይቶና ተገምግሞ በ1992 ዓ.ም በክፍለጦር ደረጃ ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከክፍለጦር በላይ ሆኖ መደራጀቱም እንዲሁ፡፡ በሀገራችን ላይ የሚፈፀም ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት እና መደምሰስ የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር በማሰብ የልዩ ኃይልና የአየር ወለድ አሃዱዎችን በማሥፋት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የሚለውን ስያሜ እና አደረጃጀት አሁን ላይም ይዞ ይገኛል፡፡ የሚሠጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእምነት የሚፈፅምና በከፍተኛ ፅናት ዘብ የሚቆም እንዲሁም በተሰማራበት የውጊያ ውሎ የውጊያው ማርሽ ቀያሪ እና አይበገሬ ሠራዊት በመገንባት ባሳለፍናቸው ዘመቻዎች አኩሪ የጀግንነት ገድል እንደ ዕዝ በመፈፀም የላቀ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ሥር ካሉት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ … [Read more...] about የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል