
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የምልምል ሰልጣኞች የስልጠና መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
በሥልጠና መክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ሥልጠናው መጀመሩን በይፋ ያበሰሩት በሰላም ማሰከበር ማዕከል የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ መከላከያ ወድ ህይወቱን ሳይሰስት የሚሰጠውን ሃገራዊ ተልዕኮ በስኬት የሚፈፅም የሀገር ኩራት መሆኑን አንስተዋል።
ውትድርና ሀገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ ለሃገር ዘብ እቆማለሁ ብሎ በፍላጎት በተነሳሽነት በቁርጠኝነት እና በታማኝነት አገልግሎት የሚሰጥበት የሚያኮራ ሙያ መሆኑንም አዛዡ ገልፀዋል፡፡
ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ከመላው የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ተመልምለው መመልመያ መሥፈርቱን አሟልተው የመጡ አዲስ ወጣቶችን እያሠለጠነ የሚያበቃ ነውና እናንተም አዲስ ሰልጣኝ ምልምል ሠልጣኞች የሚሠጣችሁን ሥልጠና በሚገባ መፈፀም አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል። (መከላከያ ሠራዊት)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply