• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ

September 25, 2026 02:39 pm by Editor Leave a Comment

የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ድል እያደረገ መሆኑ ተነገረ

በሴንትራል ኮማንድ ሥር ከሚገኙ የደህንነት እና የጸጥታ ምንጮች ለጎልጉል የደረሰው አዳዲስ ዜና እንደሚያመለክተው፣ በሁሉም የጦር ግንባሮች የተከፈተውን የጥፋት ዘመቻ በመመከት ላይ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በታጣቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ይገኛል።

የትህነግ (ህወሓት) ታጣቂ ኃይሎችና አጋሮቻቸው በየግንባሩ እየተገደሉ፣ የከባድ ጉዳት ሰለባ እየሆኑ እና የት እንዳሉ ጠፍተው በመበታተን ላይ ናቸው። ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች አሁንም በቀጠለበት በዚህ ሰዓት፣ ታጣቂዎቹ ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ አደጋ ገጥሟቸዋል።

1. በደጉዓ ዛታ አቅጣጫ

በዚህ አቅጣጫ በተካሄደው ከባድ ውጊያ ምክንያት የትህነግ “አርሚ 22” ሙሉ በሙሉ ተበታትኖ ወደ ሩባ ፅላረ ሸሽቶ ገብቷል። በዚህ ግንባር የተመዘገቡት አኃዞች የሚከተሉት ናቸው፡

  • 107 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 193 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 320 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል

2. በቆቦ አቅጣጫ

“አርሚ 24” ተብሎ የተጠራው የትህነግ ታጣቂ ኃይል ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዷል፡

  • 66 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 57 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 311 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል

3. በመርዋ ግንባር

በመርዋ የሚገኘው “አርሚ 26” ከመከላከያ ሠራዊት ጋር የሚያደርገው ውጊያ የቀጠለ ሲሆን፤ መከላከያ ሠራዊት ከባድ መሣሪያና እግረኛ ሠራዊት በመጠቀም አርሚውን ዳግም ሊዋጋ ወደማይችልበት ደረጃ አበታትኖታል። ባለፈው ነሐሴ ወር በድሮን ጥቃት ከተገደሉት 369 ታጣቂዎች ውጭ፣ የዛሬው ዕለት ብቻ፡

  • 52 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 87 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 428 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል

4. በአብዓላ ከተማ አቅጣጫ

በአብዓላ ከተማ አካባቢ “አርሚ 92” ከሚመለከተው የጸጥታ ኃይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ቅንጣት ደርሶበታል፡

  • 65 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 192 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 391 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል
  • 36 ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል

5. በምዕራብ አቅጣጫ (በፀሊሞይ)

አርሚ 42 እና አርሚ 17 ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በፀሊሞይ ሲያደርጉት የቆዩት ውጊያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ቆሟል። አርሚ 17 ከዚህ በፊት ከምርኮኞችና ከ300 በላይ አባላቱ እጃቸውን ለመከላከያ መስጠታቸውን ተከትሎ በህወሓት አመራር ዘንድ እምነት ስላጣ፣ ውጊያው ሲጀመር ወደኋላ እንዲመለስ ተደርጓል። አርሚ 42 በበኩሉ በቀጥታ ታዝዞ ባህላዊ ውጊያ ለማድረግ ቢሞክርም፣ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ሙሉ በሙሉ ተበታትኗል።

  • 104 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 232 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 455 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል

ማጠቃለያ

በሁሉም አቅጣጫዎች የተሰለፈው የትህነግ የታጠቀ ኃይል እጅግ አሳዛኝና አዋራጅ ሽንፈት እየገጠመው ይገኛል። በዕለቱ ብቻ በሁሉም ግንባሮች የተመዘገበው አጠቃላይ ኪሳራ፡

  • 394 ታጣቂዎች ተገድለዋል
  • 761 ታጣቂዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
  • 1,905 ታጣቂዎች ተበታትነው የት እንዳሉ ጠፍተዋል

ለጉልጉል አሰ‍እተያየታቸውን የሰጡ የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ ይህ የግምባር ሪፖርት የትህነግ እና ሰሞኑን የትብብር ኃይሎች ብሎ የመሠረታቸው ቡድኖች ዕድሜ በእጅጉ ያጠረ መሆኑን የሚያመለክት ነው ብለዋል። የማይወክሉት ሕዝብ የህልውና አደጋ አለበት ሲሉ እንደነበር ያስታወሱት ባለሙያው፤ ይልቁንስ አሁን ላይ ያልወከላቸው ሕዝብ የህልውና አደጋ አለበት ከማለት ይልቅ የራሳቸው ህልውና ሊያሳስባቸው ይገባል ብለዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tdf, TPF, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule