• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ

September 22, 2026 10:56 pm by Editor Leave a Comment

* የትህነግና የፋኖ ጥምረት ዕዝ መበጠሱ፤ አርሚዎች መናበብ አለመቻላቸው ተገለጸ

በትግራይ ደቡባዊ ዞን፣ በራያ አላማጣና በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በተመረጡ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ከአስራ ሰባት ጊዜ በላይ እጅግ የበረታና ተከታታይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታወቀ። ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የተሰነዘረውና የፊት ለፊት የእግረኛ ውጊያ ሳይካሄድበት በቴክኖሎጂ ብቻ የተመራው ይህ ጥቃት፣ በታጣቂ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጽምዶ ታጣቂዎች የተገደሉ፣ የቆሰሉና የሎጂስቲክ ክምችታቸውም ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት ተነግሯል። የትህነግና የፋኖ ጽምዶ ዕዝ ሠንሠለቱ የተበጠሰና በርካታ አርሚዎች መናበብ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ታውቋል።   

ጎልጉል ከተለያዩ ወታደራዊ ምንጮችና ከአካባቢው እማኞች ያሰባሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተካሄዱት ተከታታይ የአየር ጥቃቶች በአጠቃላይ 273 የትህነግና የፋኖ ታጣቂዎች ሲገደሉ 412 የሚሆኑት ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል።

በትህነግ ታጣቂዎች ላይ የደረሰ ሰብዓዊ ጉዳት፡ 227 የሞቱ ሲሆን 378 ደግሞ ቆስለዋል።

መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3:20 ላይ በራያ አላማጣ «ዝኽረ መለስ» ትምህርት ቤት በተደረገው የድሮን ጥቃት 200 የሚሆኑ የትህነግ ታጣቂዎች ወዲያውኑ የተገደሉ ሲሆን፣ 300 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የአላማጣ ከተማ ሆስፒታል ደጆች በቆሰሉ ታጣቂዎች ተጨናንቀው መዋላቸውን የጎልጉል መረጃ ይጠቁማል።

መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ሌሊት 9:20 ላይ በዛታ ወረዳ ሓድሽ መንደር ቀበሌ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ በነበረ ይዞታ ላይ በትህነግ ታጣቂዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 8 ታጣቂዎች ተገድለው 5 ቆስለዋል። በኩቢ ቀረንሳ በተባለ ቦታ ደግሞ 19 የትህነግ ታጣቂዎች ሲገደሉ 23 የሚሆኑት ቆስለዋል።

ከትህነግ ጋት ተጣምዶ ጥቃት ለመሰንዘር የተነሳው የፋኖ ቡድ ላይ በተደረገው የድሮን ጥቃት 46 ታጣቂዎች የሞቱ ሲሆን 34 ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ወለቃ ቀበሌ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 21 ታጣቂዎች ሲገደሉ 18 ደግሞ ቆስለዋል። በተመሳሳይ በግዳን ወረዳ 018 ቀበሌ አስቂት ላይ በተሰነዘረ እርምጃ 25 ታጣቂዎች ተገድለው 16 መቁሰላቸው ተረጋግጧል።

መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማርፈጃው የተካሄደው የድሮን ጥቃት በአርሚ 26 የ261ኛ ኮር አባላት ላይ የደረሰውን ጉዳት በከፍተኛነቱ ተመዝግቧል። ለትህነግ ወታደራዊ ክፍል ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት፣ የደረሰው ሰብአዊ ጉዳት በቁጥር አይገለጽ እንጂ ትህነግን ክፉኛ አስደንግጧል።

የደረሰው ሰብአዊ ጉዳት እጅግ የበረታ በመሆኑ የአርሚ 26 አስተባባሪዎች የቆሰሉ ታጣቂዎችን መሆኒ ከተማ ወደሚገኘው የግንባሩ የሕክምና ማዕከል በፍጥነት ለማጓጓዝ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ በየስርቻውና በየኪሱ የተበተኑት አስከሬንና ቁስለኛ ብዛት ሙሉ በሙሉ ለማወቅ እንደማይቻል ተገልጿል።

በአካባቢው በሚገኙ የሕክምና መስጫ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ባለሙያዎችን ታማኞች አይደላችሁም፤ መረጃ ታቀብላላችሁ በሚል ትህነግ አስቀድሞ ከሥራቸው እንዳባረራቸው ተነግሯል። የተባረሩት ወደ አማራ ክልል ገብተው በክልሉ መስተዳድር ደመወዝ እየተከፈላቸው ያለ ሲሆን ትህነግ ከትግራይ ታማኝ ናቸው ብሎ ያመጣቸው ልምድ የሌላቸውና ባለሙያ ያልሆኑ ሠራተኞች ቁስለኞችን ለማከምም ሆነ ሁኔታውን ለመቆጣጠር እንዳቃታቸው ጎልጉል ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ከአላማጣ ወደ መሆኒ መግቢያ ላይ የሚገኘው እና ፋጣ (ጀሃን) የተባለው ትምህርት ቤት ላለፉት አራት ቀናት ከባድ መሳሪያና ተተኳሽ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ተጨናንቆ የነበረ በመሆኑ፣ የድሮኑ ጥቃት በአካባቢው ላይ የነበረውን የጦር መሳሪያ ክምችት ሙሉ በሙሉ አውድሞታል።

ጥቃቱን ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት የሚሰማ ኃይለኛ ፍንዳታና ተቀጣጣይ ድምፅ የተሰማ ሲሆን፣ ታጣቂዎች “ምስልና ቪዲዮ ይነሳል” በሚል ስጋት ነዋሪዎችን ወደ ስፍራው እንዳይጠጉ ከልክለዋል። በእያሱ በርሄ ትምህርት ቤትም በኦራል ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ተተኳሽ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

የፌዴራል መንግሥት የአየር መከላከያ ኃይል የሰነዘረው የተቀናጀ ጥቃት በአዲስ መንግሥት ምስረታ ዋዜማ በራያ ቆቦና በአፋር ግንባር ጦርነት ለመክፈትና ይዞታ ለማስፋት በትህነግ ታቅዶ የነበረውን ወታደራዊ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አክሽፎታል።

ሰባት ነጻ አውጪ ድርጅቶችና ግንባሮች “የህልውና ስጋት አሰባሰባቸው” በሚል የመሠረቱት አዲስ ኅብረትም ወደ ከባድ መከፋፈል አምርቷል።

ጥቃቱ ያመጣው ከፍተኛ ሰብአዊ መርዶ የትህነግን ወታደራዊ አመራር ክፉኛ ያስደነገጠ ሲሆን፣ የበርካታ አርሚዎች (በተለይም በአርሚ 26 የሥር መዋቅሮች) የእዝ ሰንሰለት ተበጥሷል። አመራሩ ለራሱ ደኅንነት በመስጋቱ የተበታተነውን ታጣቂ ማሰባሰብ አልቻለም።

ይህን የታጣቂ ኃይሎች መናጋትና ግራ መጋባት እንደ ሰርግና ምላሽ የተጠቀመበትና ቀድሞውኑ ዓላማ በሌለው ጦርነት ማለቅ ያልፈለገው የትህነግ ታጣቂ በሰፊው መክዳት ጀምሯል።

የትግራይ ሰላም ኃይሎች አመራር ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ5,000 በላይ ታጣቂዎች ትህነግን ከድተው ወደ መከላከያ ሰራዊትና ወደ ሰላም ኃይሉ ተቀላቅለዋል። አመራሩ አክለውም “በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለ ቡድኑ በአንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መፍረሱ አይቀሬ ነው” ብለዋል።

እስከ አሁን ባለው መረጃ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ሆነ የትህነግ የፖለቲካም ሆነ የታጣቂ ክንፍ ስለ ጥቃቱና ስለደረሰው የጉዳት መጠን በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Slider Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
Copyright © 2026 · Goolgule