የኢትዮጵያ ክብርና ነፃነት በቆራጥ ልጆቿ መሥዋዕትነት የተገኘ መሆኑ የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለሀገራችን ሠላም፣ ለሠንደቅ ዓላማችን ክብር ሲሉ መሥዋዕትነት ከከፈሉ ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም አንዱ ናቸው፡፡ ዛሬ ጳጉሜ 2 ለኢትዮጵያ ሀገራቸው መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች የሚታሰቡበት እና የሚዘከሩበት ቀን እንደመሆኑ በዛሬው የአውደ ሰብ አምዳችን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያምን ባለታሪካችን አድርገናቸዋል፡፡ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ተወልደው ያደጉት በጉራጌ ዞን ከቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሲሰ መንደር ውስጥ ነው፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን እዚያው እምድብር ከተማ የተማሩ ሲሆን፣ በ1948 ዓመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትነው በጥሩ ውጤት … [Read more...] about ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም