• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም

September 8, 2023 02:31 pm by Editor 3 Comments

የኢትዮጵያ ክብርና ነፃነት በቆራጥ ልጆቿ መሥዋዕትነት የተገኘ መሆኑ የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለሀገራችን ሠላም፣ ለሠንደቅ ዓላማችን ክብር ሲሉ መሥዋዕትነት ከከፈሉ ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም አንዱ ናቸው፡፡ ዛሬ ጳጉሜ 2 ለኢትዮጵያ ሀገራቸው መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች የሚታሰቡበት እና የሚዘከሩበት ቀን እንደመሆኑ በዛሬው የአውደ ሰብ አምዳችን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያምን ባለታሪካችን አድርገናቸዋል፡፡

ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ተወልደው ያደጉት በጉራጌ ዞን ከቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሲሰ መንደር ውስጥ ነው፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን እዚያው እምድብር ከተማ የተማሩ ሲሆን፣ በ1948 ዓመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትነው በጥሩ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

የ8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁም የአምቦ እርሻ ልማት ትምህርት ገብተው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፤ በኋላም ወደ ጦር አካዳሚ በመግባት የ3 ዓመት ወታደራዊ ሳይንስና የአካዳሚ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በስመጥሩው የምርጥ መኮንኖች ማፍሪያ በሆነው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ሀረር) ጦር አካዳሚ ነው። 

ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ በመቀጠልም የጦር ሠራዊቱን በመቀላቀል የአየር ወለድ ሥልጠና የወሰዱ ሲሆን፤ ሙያቸውን ለማጠናከርም በእስራኤል የኮማንዶ ትምህርት፣ አሜሪካ የልዩ ኃይል፣ ሞስኮ እና ህንድን ጨምሮ በተለያዩ የውትድርና ሥልጠናዎችን ራሳቸውን አብቅተዋል፡፡  

በ1969 ዓ.ም የሶማሊያ ተስፋፊ ሃይል ኢትዮጵያን ወሮ ከጅግጅጋ እና ጎዴ አልፎ መጥቶ እስከ ሜኢሶ ድረስ በመቅረብ መሬቱን በፈንጅ አጥሮ ነበር፡፡ ይህ መሰናከል ለሠራዊቱ እና ለህዝቡ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ለማቅረብ በጣም ችግር ፈጠረ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም የሶማሊያ ግዛት ክልል ውስጥ ዘልቆ መግባት እና ፈንጅ መቅበር አንድ መንገድ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ግዳጅም ለብ/ጀነራል ተስፋዬ ተሰጠ፡፡ እሳቸው የሚመሩት ቡድንም ድንበር አቋርጦ ሶስት ቀን እና ሌሊት ፈንጂ በመቅበር የጠላትን እንቅስቃሴ አወከ፤ ትልቅ ውጤትም ማምጣት ተቻለ፡፡

በ1970ዎቹ መግቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጠለፋ ምክንያት በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም አንዳንድ ቦታዎች ላይ በረራ በመቆሙ ድርጅቱ ለሠራተኞቹ እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልተቻለበት ሁኔታ ላይ ደርሶ ነበር፡፡ ችግሩን ለመፍታትም የበረራ ደህንነት እንዲቋቋም መንግሥት ሲወስን የድህንነት ቡድን እንዲያቋቁም ለብ/ጀነራል ተስፋዬ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ እሳቸውም የሰለጠኑ የደህንነት አባላት ከአውሮፕላኖቹ ጋር እንዲጓዙ በማድረግ ችግሮቹን መፍታት ችለዋል፡፡

በሰላም ለመኖር መሰረቱ ሥነ- ሥርዓት ነው የሚሉት ብርጋዴን ጄኔራል ተስፋዬ ሀ/ማርያም “በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ጥይት በሚፈነዳበት ቦታ ሁሉ እኔ ያልተሳተፍኩበት በጣም ጥቂት ሲሆን፣ አብዛኛው በተሳተፍኩባቸው ቦታዎች በድል ወይም በስኬት ነው የተጠናቀቁት” በማለት ስለ ህይወት ተሞክሮአቸው ይገልጻሉ፡፡

በ1970ዎቹ እርሳቸው የሚመሩት የአየር ወለድ ጦር ናቅፋ ተራራ ላይ ለ6 ወራት በጠላት ተከቦ በህይወት ቆይቶ የጠላትን ከበባ ሰብሮ በህይወት እንደወጣ ሲነገሩ፣ ይህ ታሪካዊ ክስተት በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የተፈጠረ የአየር ወለድ ሠራዊት ጀብድ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡   

ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሃ/ማርያም በሶማሊያ ጦርነት ወቅት ለሠሩት ገድል እና በናቅፋ በሰሩት ጀብድና የአመራር ብቃት ከሻለቃነት ወደ ኮሎኔልነት በአንዴ ማደግ የቻሉ ወይም በ5 ዓመት የሚደረስበትን ወታደራዊ ማዕረግ በፈጥነት ማግኘት የቻሉ ጀግና ናቸው፡፡ ጀነራሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ለማንም ወታደር እና መኮንን ተሸልሞ የማያውቀውን “ወደር የሌለውን የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና ወታደራዊ ሜዳሊያም” ተሸልመዋል፡፡

ማንም ሰው ብቁ አሰልጣኝ ካገኝ አየር ወለድ መሆን እንደሚችል የሚገልጹት ብ/ጀነራል ተስፋዬ፣ እሳቸው ከሀረር ጦር አካዳሚ በመሰረታዊ ውትድርና ከሰለጠኑ በኋላ የአየር ወለድ ሥልጠና ያገኙት ከእስራኤሎች እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ 

“ኢትዮጵያ በየዘመኑ ጀግና የምታፈራ የጀግኖች ሀገር ናት” የሚሉት ብ/ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ለዚህም መላው የሀገሪቱ ህዝብ ትልቅ ኩራት ሊሰማውና ተስፋ ሊሰንቅ እንደሚገባም ይናገራሉ።

“የሀገሪቱን ዕድገት ጎታች ሆኖ ፈተና ውስጥ የከተተን ነገር የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ከሀዲዎች በየጊዜው የሚከፈትብን ጦርነት ነው፤ ይህንን የህልውናችንን ጠላት ለመዋጋት ደግሞ ወጣቱ ከጦር ሜዳው ተሳትፎ ባልተናነሰ መልኩ መነሳትና አንድነት መፍጠር ይኖርበታል” ይላሉ። (ኢዜአ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Literature, Middle Column, Social Tagged With: Tesfaye Habtemariam

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    September 14, 2023 11:13 am at 11:13 am

    ኢትዮጵያ አሉኝ ብላ ከምትጠራቸው ከሞትና ከስደት ከተረፉት ልጆቿ መካከል ብ/ጄ ተስፋዬ ሃብተማሪያም ቀዳሚው ነው። የጦር ሜዳ ውሎ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንደሚተርክልን “ላብ ደምን ያድናል” በማለት ለሃገሩ በአራቱ ማእዘናት የተፋለመ ሥራው በጠላትም ጭምር የተመሰከረለት ጀግና ነው።
    ሌላ ምን እላለሁ እንኳን ከዚያ ሁሉ የመጠላለፍና የሞት ፍልሚያ ወጥተህ እድሜ ጠግበህ ያኔ የሆነውና አሁን የሚሆነውን ሁሉ አይተህ አይ ጊዜ እንድትል ፈጣሪ እድሜውን ስለቸረህ በጣም ደስ ይለኛል። ያንተ ጀግንነት ለትውልድ በታሪክ ለማስተላለፍ ሰፋ ባለ መልኩ ፊልም/ድራማ ቢሰራ መልካም ይመስለኛል። መጽሃፍ ብቻውን በቂ አይሆንማና! ረጅም እድሜና ጤና ለኢትዮጵያ ባለውለታ ብ/ጄ ተስፋዬ ሃበተማሪያም ይሁን!

    Reply
  2. noah h.meskel says

    September 22, 2023 02:12 am at 2:12 am

    እኔም የአቶ ተሰፋን አሰተያየት እደግፋለሁ የእርሳቸውን (የብርጋዴር ጄነራልን) የጦር ገድል በፊልም ቢሰራ ለአዲሱ ትውልድ የሀገር ፍቅር ምን እንደሆነ ያሰተምራል::

    Reply
  3. Zeru metaferia says

    May 6, 2025 01:14 pm at 1:14 pm

    ጄኔራል ተስፋዬ 1992 ብላቴ እኔ ሰልጠኘሰ እሳቸው የማሰልጠኛው ኮማንደር ሆነው አውቃቸዋለሁ ኢትዮጵያ አሉኝ ብላ ከምትጠራቸው ከሞትና ከስደት ከተረፉት ልጆቿ መካከል ብ/ጄ ተስፋዬ ሃብተማሪያም ቀዳሚው ነው። የጦር ሜዳ ውሎ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንደሚተርክልን “ላብ ደምን ያድናል” በማለት ለሃገሩ በአራቱ ማእዘናት የተፋለመ ሥራው በጠላትም ጭምር የተመሰከረለት ጀግና ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule