በፓሪስ ኦሊምፒክ ዋዜማ የተቀሰቀው የእነ ኃይሌና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውዝግብ ወደ ሕግ ማምራቱ ይፋ ሲሆን “ቀድሞም ቢሆን መሆን የነበረበት ጉዳይ ይህ ነበር። አበጃችሁ” ሲሉ ጉዳይን በረጋ መንፈስ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር። በሕግ ሕግን ማስከበርና፣ በሕግ መብትን ማስጠበቅ እንደሚቻል የሚያሳይ፣ ለሌላው ወገን ደግሞ በሕግ ራስን መከላከልና በሕግ መጠየቅ እንዳለ የሚያስተምር አግባብ እንደሆነ አመልክተው ነበር። ሻለቃ ኃይሌና አትሌት ገዛኸኝ አበራ የሚመሩትና ሁለት ፌዴሬሽኖች የተካተቱበት ወገን ዶክተር አሸብር የሚመሩትን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስሰው ኮሚቴው የሚያንቀሳቅሳቸውን የባንክ ሂሳቦችና፣ የዕለት ተለት ክንውን ማካሄድ እንዳይችል አስወስነው የነበረው በሕግ በመሆኑ ዜናው ፍሞ ነበር። ጅማሮውን የትግላቸው ውጤት አድርገው ያቀረቡም ጥቂቶች … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጣለበት ዕግድ ተነሳለት
Social
የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የዘንድሮና የአምናው መጠነኛ ንጽጽር
በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 ወይም 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከትላንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ያሰባሰብነው ከመንግሥታዊ ሚዲያና ከቲክቫህ ነው። በአጠቃላይ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ከሐረሪ ክልል ውጭ ሁሉም ክልሎች ላይ አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት 273 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ 1ሺ 220 ተማሪዎች ከ500 በላይ ያመጡ ናቸው ተብሏል።እንዲሁም በዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 5.4 በመቶ ፈተናውን አልፈዋል ይህም ማለት … [Read more...] about የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የዘንድሮና የአምናው መጠነኛ ንጽጽር
የኢቲቪ ባለሥልጣናት ኦሊምፒክና አትሌቲክስ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ እንዲሠራ አዘዙ
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለሥልጣናት በኦሊምፒክና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ ትኩረት ያደረገ የፕሮፓጋንዳ ሥራ እንዲሠራ መመሪያ መስጠታቸው ተሰማ። መመሪያው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ኢቲቪ የሚያቀርበው ዘገባ የሕግ ጥያቄ ማስደገፊያ እንዲሆን ተደርጎ ለመረጃነት እየተዘጋጀ መሆኑ ከሌሎች ወገኖች ተደምጧል። ከፓሪሱ ኦሊምፒክ መጀመር ቀደም ብሎ በማኅበራዊ ሚዲያው የተጀመረው ዘመቻ ሁለት ቡድኖች ጎራ ለይተው ውዝግብ መጀመራቸውን አመላካች እንደነበር ይታወሳል። ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴና አትሌት ገዛኸኝ አበራ ጎራ ለይተውና ተመሳሳይ አቋም ይዘው የለኮሱት ተቃውሞ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀናት በፊት ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ተቃውሟቸውን ለመግዛትና ለማሰራጨት ጊዜ አልወሰደም። ከወራት በፊት በተጠናቀቀ ምርጫ ላይ ቅሬታ በማንሳት የተጀመረው ክስ ውድድሩ ከተጀመረ በኋላም ከፓሪስ በሚወጡ ዐውዳቸውን … [Read more...] about የኢቲቪ ባለሥልጣናት ኦሊምፒክና አትሌቲክስ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ እንዲሠራ አዘዙ
“የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው”
ሁሉም ባይባልም አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና የፖለቲካ ፕሮግራም ሶሻል ዴሞክራሲ ወይም ሊበራል ዴሞክራሲ ወይም ምርጫን ማዕከሉ ያደረገ ዴሞክራሲያዊ ፖሊሲ ነው። የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ደግሞ ገበያ መር ኢኮኖሚ ነው። እነዚሁ ፓርቲዎች በምርጫ ክርክር ሲደረግ በዋናነት እያነሱ የሚከራከሩት መንግሥት ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮታል፤ የዕዝ ኢኮኖሚ ነው አገሪቱን ለችግር የዳረጋት፣ የኢኮኖሚው አካሄድ በገበያ እንጂ በመንግሥት መመራት የለበትም በሚል የከረረ ተቃውሞ በማቅረብ ሲቃወሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰምተናል። ባለፈው ሰኞ መንግሥት የአገሪቱን ዐቢይ (ማክሮ) ኢኮኖሚ ወደ ገበያ መር የሚወስድ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ እነዚሁ ተቃዋሚዎች “እሰይ ስለቴ ሰመረ” ባይሉም ቢያንስ ለዓመታት ሲሟገቱለት የነበረው ሃሳብ ድል አድርጎ በማየታቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሊያሰሙ የሚጠበቅ … [Read more...] about “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው”
የፖሊሲ ጥሰት በፈጸሙ 44 የግል ኮሌጆች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የ18 የግል ኮሌጆች ፍቃድ ታገደ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አደረግኩት ባለው ድንገተኛ የቁጥጥር ስራ የፖሊሲ ጥሰት ፈፅመዋል ያላቸውን 18 የግል ኮሌጆች ፍቃድ አግዷል፡፡ ከታገዱት በተጨማሪ መለስተኛ የፖሊሲ ጥሰት በፈፀሙ 26 የግል ኮሌጆች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም ድንገተኛ ቁጥጥር የተደረገባቸው 59 የግል ኮሌጆች ሲሆኑ 18ቱ ታግደዋል፤ 26ቱ ከቀላል እስከ ከባድ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በድምሩ 44 የግል ኮሌጆች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል፡፡ ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍና በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ … [Read more...] about የፖሊሲ ጥሰት በፈጸሙ 44 የግል ኮሌጆች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 77 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በቅርቡ የተደረገውን የዶላር ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 77 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮዉ ሃምሌ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገዉ የክትትል ሥራ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 11 እንዲሁም በየካ ክ/ከ 2 በድምሩ 13 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያስተወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተማ በተደረገ የአሰሳ ስራ 77 ንግድ ሱቆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል። ኃላፊው ጨምረውም አብዛኛው የተወሰዱ እርምጃዎች በማኅበረሰቡ ጠቆማ እንደሆነ ገልጸው የከተማው ነዋሪዎች አሁንም የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግድ ድርጅቶችና ሱቆች በአቅራቢያቸው በሚገኝ ወረዳ መጠቆም እንዳለባቸዉ … [Read more...] about ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 77 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ቆሻሻ የሚጥሉና ዘንባባ የሚገጩ ቅጣት አንሷል ተባለ
በአዲስ አበባ በየቦታው ቆሻሻ ለሚጥሉና በቅርቡ የተተከሉትን ዘንባባዎች ለሚገጩ የሚከፈለው ቅጣት ያነሰ መሆኑን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ተግባሩን ለመከላከል የሌሎች አገራት ልምድ ተግባራዊ እንዲደረግና ጥፋቱን ለመቀነስ የቅጣት መጠኑ መጨመር እንዳለበት ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ኢመደበኛ ጥናት ሁሉም ተጠያቂዎች የሰጡት ምላሽ ጥፋቱን በሚፈጽሙ ላይ የተበየነው ቅጣት ከዚህ መጨመር እንዳለበት ነው። ሌላው የሰጡት ምላሽ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በማጥናት በአገራችን ላይ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ጥንቃቄ የሰጡት ምላሽ ሁሉም ሰው አውቆ ዘንባባ ስለማይገጭ እንደ አገጫጩ ምክንያትና ዐውድ ቅጣቱም በዚያው መልኩ አጥፊዎችን ከአደጋ አድራሾች … [Read more...] about ቆሻሻ የሚጥሉና ዘንባባ የሚገጩ ቅጣት አንሷል ተባለ
ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ ከባለቤቱ 500ሺ ብር የተቀበለው ግለሰብ ተያዘ
የ63 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እና የ5 ልጆች አባት የሆነው አቶ ገብረ ተንሳኢ ተክላይ ከወይዘሮ ዘነበች በርሄ ጋር ለ14 አመታት በትዳር ተጣምረው በአሶሳ ከተማ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው 4 ልጆችን አፍርተዋል። በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ምንም አይነት እንከን እንደሌለ የሚገልፀው አቶ ገብረተንሳኢ ተክላይ ወይዘሮ ዘነበችን ከማግባቱ በፊት አንዲት ሴት ልጅ እንዳለችውና እሷም ለብቻዋ አዲስ አበባ እንደምትኖር በመግለፅ ይህንን እኩይ ተግባር ለመፈፀም የተነሳሳውም የግል ልጁን ለመርዳት እንደሆነ ተናግሯል። ከሚኖርበት አሶሳ ከተማ ወደ ነቀምት ከተማ በመጓዝ "ኦጌቲ" በሚባል ሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት አልጋ ይዞ በመተኛት ከሆቴሉ አስተናጋጆች የ21 ዓመት ልጅ የሆነውን ወጣት ገመቹ ዮናስን በመግባባት የአጋችና ታጋች ድራማውን አብሮት እንዲሰራና ለዚህም ታግቻለሁ ብሎ ከሚላክለት ብር … [Read more...] about ሳይታገት ታግቻለሁ ብሎ ከባለቤቱ 500ሺ ብር የተቀበለው ግለሰብ ተያዘ
ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
"... አሁን ቱሪስት የለም" የላሊበላ ነዋሪ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ‼️ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA) ጥር 7 2016 የታተመው … [Read more...] about ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
ትግራይ እየፈረሰች ነው – ሐይቲ በኢትዮጵያ
"አሁን ማንም ሰው ነው አግቶ የሚወስድህ፤ የሚጠብቅ የፀጥታ አካል የለም" ትህነግ በእብሪት ተሞልቶ መቀሌ መሽጎ በነበረበት ወቅት አገሪቱ በግጭት ስትታመስ፤ ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ ለውጡ ነውጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በመፍረስ አደጋ ውስጥ ሆና ሳለ የሰላም ጉዳይ ያሳሰባቸው እናቶች ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተጉዘው ነበር። በሁሉም ቦታዎች የክብር አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ የተጓዙት ወደ መቀሌ ነበር። የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ የሰላም ሠንደቅ በማውለብለብ እያለቀሱ መሬት ላይ ተደፍተው “ሰላም ላገራችን” ብለው ልመናቸውን ሲያቀርቡ የወንበዴው ቡድን መሪና በወቅቱ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እያላገጠ “እኛ ክልል ሰላም ነው፤ ይልቅ ሌላ ክልል ነው ሰላም የጠፋው፤ ስለዚህ እዚያ ብትሔዱ ይሻላል፤ እኛ ጋር ለምን እንደመጣችሁ አናውቀም?” በማለት ነበር … [Read more...] about ትግራይ እየፈረሰች ነው – ሐይቲ በኢትዮጵያ