• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ

February 4, 2026 12:14 pm by Editor Leave a Comment

* በስጋት ከቀያቸው የተፈናቀሉት የትግራይ ተወላጆች ቤታቸው ሳይፈርስ፣ ንብረታቸው ሳይጎድል ለዓመታት ጠብቋቸዋል

በትላንትናው የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢሉባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን አስመልክቶ የተናገሩ የብዙዎችን ልብ የነካና ኢትዮጵያዊነትን አድምቆ ያሳየ መረጃ ነበር።

“ለምሳሌ ጦርነት ሲጀመር” አሉ ዐቢይ “ከኢሉባቡር ሸሽተው ትግራይ የሄዱ አርሶ አደሮች ነበሩ። ከዛ የመጣችሁ ሰዎች አጥኑ ይሄን ጉዳይ ትክክለኛ መረጃ ነው።

“ሰዎቹ ሸሽተው ትግራይ ገብተዋል፤ ኢሉባቡር ያሉ አርሶአደሮች ከእነርሱ ማሳ ቡና ለቅመው ሸጠው ገንዘቡን በአካውንታቸው ያስገባሉ፤ ሰዎቹ የሉም። ከእርሻቸው ላይ የተመረተ ምርት ሸጠው ገንዘቡን በራሳቸው አካውንት ያስገባሉ።

“ሰዎቹ ‘የኛ ሰዎች በሌለንበት ሰርተው አካውንታችን እያስገቡ ነውና በቃ እንመለስ’ ብለው ተመልሰው ኢሊሉባቡር አሉ አሁን፣ እየኖሩ ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ማብራሪያቸው ላይ የጠቀሱት ይህ የአብሮነት እሴት፣ ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥም ጠንካራ መሰረት እንዳላት ማሳያ ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ጦርነቱ ሲጀመር በኢሉአባቦር የነበሩ አርሶ አደሮች ከአካባቢው ሸሽተው ትግራይ ከገቡ የትግራይ ተወላጆች ማሳ ላይ ቡና ለቅመው፣ ሸጠው ገንዘቡን በአካውንታቸው ያስገቡ እንደነበር ገልፀዋል።

ይህንን ያዩት አርሶአደሮችም ተመልሰው ከቤታቸው ገብተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚነስትሩ በራያ፣ በፀለምት እና በኦሮሚያ አካባቢዎች ሌሎችም ወደ ቄያቸው ተመልሰው እየኖሩ ነው ብለዋል።

ከዓመታት በፊት በኢሉአባቦር ዞን ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በጸጥታ ስጋት ምክንያት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ትግራይ ተሰደው ነበር።

ከእነዚህም መካከል አቶ መሀሪ ወልዴ እና አቶ መኮንን በርሄ ይገኙበታል። ተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች ከዓመታት በኋላ ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ሲመለሱ የጠበቃቸው ነገር እጅግ አስገራሚ ነበር።

ቤታቸው አልፈረሰም፤ አደራቸውም ተጠብቋል፤ ገቢያቸውም አልተቋረጠም። ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ትግራይ የተሰደዱት ተፈናቃዮች የመኖሪያቸው “ቆርቆሮው ጥርኝ ሳይነካ፣ አጥራቸው ሳይነቃነቅ” ጠብቋቸዋል።

በስደት በነበሩበት ወቅትም የቡና ምርታቸውና የቤት ኪራይ ገቢያቸው አቶ አዲሱ አወቀ እና አቶ ታምራት አረጋን በመሰሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አማካኝነት በባንክ ከነበሩበት ድረስ በታማኝነት ይላክላቸውም እንደነበር ይናገራሉ።

“በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ አደራ መጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ የወንድሞቻቸውን ንብረት እንደራሳቸው ጠብቀው አደራቸውን በታማኝነት በመወጣት አስረክበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፣ ይህንን የኢሉአባቦርን ታሪክ በማንሳት፤ ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ትኩሳት ሳይበገሩ በአብሮነት የመኖር ጥልቅ እሴት እንዳላቸውና ይህንንም ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተውበታል። የሁሩሙ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ቸርነት እንዳሉት፣ ዛሬ በወረዳው ሁሉም ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በአንድነት እየኖሩ ነው። (EBC)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column, Social Tagged With: DDR, Illubabor, tigray

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule