የተዛባ እና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨትና ከዚያ በማትረፍ ሕዝብን ማደናገርና ሀገርን መበጥበጥ የገፊና ጎታች ሤራ ዋነኛ አካሄድ ነው። የአርሲው ትንሽ ጋብ ሲል ሰሞኑን ደግሞ የታርጋ ጫጫታ አየሩን ሞልቶታል። በተለይ እንደ ኤሊያስ መሠረት ያሉ ከሙያም፣ ከስብዕና እጅግ በጣም የወረዱ ሰዎች ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው የሚያሰራጩት መረጃ የብልጽግና ካድሬ እና የመንግሥት መዋቅሩ የተረዳው አይመስልም ወይም ሆን ብሎ እያገዛቸው ነው። ለታርጋ ሃምሳ ስድስት ሺህ ብር እንዲከፍል ሕዝቡ ተገደደ፣ የአይ ኤም ኤፍ ስልታዊ የግብር ስብሰባ ሕዝቡን እያደኸየው ነው፤ እንደ ኬኒያ ሀገሪቱ ልትናወጥ ነው፤ ሆ ብሎ መነሳት አሁን ነው፤ የግፍ አገዛዝ ገመዱን እያጠበቀው ነው፤ በየማኅበራዊ ሚዲያ የሚታየው ጭስ ይህ ነው። አይ ኤም ኤፍ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያ ብድር ለመፍቀድ እና በፊት … [Read more...] about የታርጋ ጫጫታ

