ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “አሉኝ” የሚላቸውን መረጃዎች የሚያሰራጭበት ሚዲያ በመኖርና በመጥፋት መካከል እንደሆነ ጠቅሶ የተለያዩ አማራጮችን ሲያቀርብ የነበረው ኤሊያስ መሠረት በተቃውሞ ሽፋን ለብልጽግና እየሠራ እንደሆነ መቅመጫቸውን ኬኒያ ያደረጉ ክፍሎች ገልጸዋል። በአገር ቤት ያሉና ይህንኑ ዜና የሚደግፉ ተጨማሪ ማስረጃዎችን በመገጣጠም ዜናውን አጉልተዋል። ኤሊያስ መሠረት በተቃውሞ ሽፋን ለብልጽግና እንደሚሠራ መረጃ የሰጡት ክፍሎች ኤሊያስ መሠረት ናይሮቢ በከተመበት ወቅት በቅርበት የሚያውቁት ናቸው። ትህነግ በሥልጣን በነበረበት ዘመን በሥልት ዜናዎችን ሲያቀዛቅዝና ሲያድበሰብስ ጠንቀቀው የሚያውቁት ወዳጆቹ እንደሚሉት፣ ኤሊያስ መሠረት ወደ ብልጽግና የመሸጋገር ዝንባሌ የታየበት “ትህነግ ዳግም ይመለሳል” የሚለው ምኞቱ ሙሉ በሙሉ መክሰሙን ከተረዳ በኋላ ነው። ለትህነግ … [Read more...] about ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …?
Elias Meseret
የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ?
ቴድሮስ አድሃኖም አዲስ አበባ አልመጣም! መሠረተቢሱ መሠረት ሚዲያ! ራሱን “ዓለምአቀፋዊ ጋዜጠኛ” ብሎ በመሰየም ለፈረንጅ ሚዲያ መሥራት እና አገርን መሸጥ፣ ባንዳ መሆንን ጌጡ ያደረገው ኤሊያስ መሠረት ህወሃት/ትህነግ ከመንበሯ ከተነቀለች ጊዜ ጀምሮ በዋንኛነት የያዘው አጀንዳ መርዘኛ ፕሮፓጋንዳውን በ“መረጃ” ስም መትፋት ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፋኖ ትግል መሪ የሆነውን እስክንድር ነጋን ፊት ለፊት በማድረግ “ከመንግሥት ጋር በውጪ ድርድር እንዲደረግ የፋኖ ክንፍ ጠየቀ” ብሎ የሐሰት ወሬ በትኖ ነበር። ይህ ሆን ብሎ የፋኖ ኃይሎችን ለመበታተን እና አንድነት በመካከላቸው እንዳፈጠር ያስወራው ተራ አሉባልታ እንደሆነ ራሱ እስክንድር ወጥቶ ተናግሯል። መሠረተ ቢሱ ኤሊያስ ይህንን መረጃ ካወጣ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ይህ ሰው ያኔ ለወያኔ እንደሠራ አሁንም ለብልፅግና … [Read more...] about የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ?
ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!
የመሠረት ሚዲያ ባለቤት አቶ ኤሊያስ መሠረትን በስም ጠቅሶ የመንግሥት ተከፋይ እንደሆነ የፋኖ አንድ ክንፍ መሪ እስክንድር ነጋ በይፋ ተናገረ። እስክንድር “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ” ሲል አመልክቷል። እስክንድር ይህን ያለው ከEMS ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲሆን፣ መነሻው አቶ ኤሊያስ መሠረት በአባቱ ስም እንደሰየመው በሚገልጸው የግሉ ሚዲያ ላይ እስክንድርን ጠቅሶ “ከመንግሥት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ” በማለት ሪፖርት ማድረጉን ተከትሎ ነው። አቶ ኤሊያስ “መሠረት ሚዲያ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ በሠሩ እና አሁንም እየሠሩ ባሉ ጋዜጠኞች ሚዛናዊ፣ አዳዲስ እና ፈጣን መረጃዎችን ለአንባቢዎች ያደርሳል” በሚል መሪ እሳቤ እንደሚሠራ በማኅበራዊ ገጹ ላይ አስፍረዋል። እስክንድር ነጋ በቃለ ምልልሱ “ኤሊያስ … [Read more...] about ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው!