የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል የሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። ግለሰቡ በተጨማሪም ሎችንም የሀሰት መረጃዎች "የትግራይ ልዩ ሃይል ድል" በሚል ርዕስ ፍሪደም ቲቪ በተባለ የዩቲዩብ አድራሻ በተለያ ጊዜ ያልተጨበጠ መረጃ ያሰራጭ እንደነበረ ተገልጿል። ይህ ሃጎስ ሰልጠነ ፍስሃዬ የተባለው ግለሰብ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ አገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ ዘረዝጊ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱም 6 መቶ የአሜሪካን ዶላር ይከፍለው እንደነበር ግለሰቡ … [Read more...] about ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
fake news
ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
በኢትዮጵያና በውጪ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ በማሰራጨትና የበርካታ ሰዎችን ትኩረት በመሳብ በርካታ ገቢ የሚያስገኝ ተከታታይ መሰብሰብ ያልተለመደ ተግባር አይደለም። በተለይ ግን ብዙ ተከታይ አለን በሚሉ ዘንድ ይህ በተደጋጋሚ ሲከሰት መስተዋሉ የሞራልም የስብዕናንም መዝቀጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው። ህወሓት በአገራችን ሕዝብ ላይ ካደረሰው የግብረገብነት ዝቅጠት ወደ ተሻለ መንገድ ለመሄድ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት በሃሰት መረጃ የሰዎችን ቀልብ በመሳብ እና ክሊክ በማግኘት ይህም ደግሞ የሚያስገኘውን ተራ ጥቅም ብቻ በማየት ለዚህ ዓይነት ርካሽ ሥራ መሠማራት ውርደት ነው። በኢትዮጵያ የሚወጡትን የሐሰት መረጃዎች እያነፈነፈ የሚያጋልጠው Ethiopia Check “ዘሐበሻ” እና “Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ” የተባሉ “በሚዲያ” ስም የሚጠሩ ማክሰኞ … [Read more...] about ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው። ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል የጅምላ ጥሪ ነበር። መረጃው የነፍስ ጉዳይ በመሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ክፉኛ ናጣቸው። ይህንን አሸባሪ መረጃ ለመከላከል የፓሪስ አካባቢ ኃላፊዎች መግለጫ እንዲሰጡ አስገደዳቸው። በመሆኑም አርብ ሐምሌ 12፤ 2011 (ጁላይ 19) ተመረዘ የተባለው ውሃው እንደተባለው እንዳልተመረዘና ለመጠጥም ቢሆን ምንም የማያሰጋ መሆኑን አስረግጠው ተናገሩ። ይህ የሐሰት መረጃ ፓሪስን … [Read more...] about የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!