• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

February 4, 2021 08:48 am by Editor 1 Comment

የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል የሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ግለሰቡ በተጨማሪም ሎችንም የሀሰት መረጃዎች “የትግራይ ልዩ ሃይል ድል” በሚል ርዕስ ፍሪደም ቲቪ በተባለ የዩቲዩብ አድራሻ በተለያ ጊዜ ያልተጨበጠ መረጃ ያሰራጭ እንደነበረ ተገልጿል።

ይህ ሃጎስ ሰልጠነ ፍስሃዬ የተባለው ግለሰብ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ አገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ ዘረዝጊ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱም 6 መቶ የአሜሪካን ዶላር ይከፍለው እንደነበር ግለሰቡ ተናግሯል፡፡

የሚያሰራጨውን የሃሰት መረጃም እንግሊዝ አገር ሆኖ ዩቲዩቡን ከሚያስተዳድረው ዳዊት አብርሃ እንደሚሰጠውና እሱም በውጭ ካሉ አፍራሽ እንቅስቃሴ ካላቸው ከተለያዩ የቴሌቪዝን ጣቢያዎችና ከግለሰቦች ማህበራዊ ገፅ የሚያገኘውን ያልተጣራ መረጃ አሰሪውን በማስፈቀድ ይጠቀም እንደነበርም በተለይ ለደቡብ ዕዝ ሚዲያ ቡድን ተናግሯል።

ይህንን ስራ ከአመት በፊት እንደ ጀመረ የሚናገረው ግለሰቡ፣ መንግስት በትግራይ የህግ ማስከበር ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ያልተጨበጠ የበሬ ወለደ መረጃ ማሰራጨት እንደጀመረና “እየቆየሁ ስሄድም እየሰራሁት ያለው ወንጀል የደህንነት ስጋት ላይ ስለጣለኝ፣ ከአገር ለመውጣት ስንቀሳቀስ ነው በመከላከያ በቁጥጥር ስር የዋልኩት” ብሏል።

ደቡብ ዕዝ የሃሰት መረጃ አሰራጭውን ሃጎስ ሰልጠነን ጨምሮ ከአገር ሊወጡ የነበሩ 8 ሰዎችን እና 4 በህገ ወጥ ዝውውሩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን ግለሰቦች ለፌዴራል ፖሊስ ማስረከቡን ሌ/ኮ ግርማ አየለ አረጋግጠዋል፡፡

ህገ ወጦችን በመያዙ ሂደት የደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት የነበራቸው ተሳትፎ የሚደነቅ ነበር ሲሉም ተናግረዋል ሲል የመከላከያ ሰራዊት አስታውቋል። (ኢ.ፕ.ድ.)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: fake news, operation dismantle tplf, social media fake info, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    February 5, 2021 04:15 pm at 4:15 pm

    ውድ ጎልጒል፣
    ይህን ማውሳት ምን ይጠቅማል? ይህንኑ ዜና ከነመረጃው በእንግሊዝኛ ቪዲዮ ተቀርጾ እዚያው በውጭ ሚድያ ማሠራጨት ነው! ሃጎስ ያልከው ግለሰብ እንግሊዝ ተቀምጦ ሽብር መፍጠር ትልቅ ወንጀል መሆኑን የዘነጋ ይመስለኛል፤ ወይም አይነቃም ብሎ ይሆናል! ኢትዮጵያውያን ምነው ቀልብ ነሳቸው፤ የቋንቋ ብቃት ያላቸው ስንቱን ጒዳይ በመረጃ አስደግፈው አክብሮትና ከስድብ በጠራ መልኩ ቢዘግቡ ህወሓት ፈረንጆችንና ዲቃሎቻቸውን በገንዘብ አሠማርቶ የሚያወናብደው ይከሽፍ ነበር። ጦር ሃይላችን ይህን ያክል ጀግንነት አሳይቶን እንዴት በእኛ ስንፍና ዋጋ ይጣ? ህወሓት እስካሁን የዓለምን ማህበረሰብ ቀልብ ለመሳብ የተጠቀመባቸው ነጥቦች፦
    ፩/ አስገድዶ ሴቶችን መድፈር (እነ ስዬ አብርሃ፣ ስብሃት፣ ደ/ጽዮን ወዘተ ሲያደርጉት የነበረውን ማለት ነው
    ፪/ መስጊድና አክሱም ጽዮንን ማፈረስ ሰባት መቶ ሃምሳ አማንያንን ማረድ (ከሳምንት በፊት አምስት መቶ ነበር)
    ፫/ ረሃብን እንደ መሳሪያ መጠቀም (ህወሓት ሲያደርገው የነበረውና ደርግ ሲከሥሥበት የነበረው)
    ፬/ ኢንዱስትሪዎችን አውራ መንገዶችን በቦንብ ማፈራረስ (ህወሓት ቀድሞ የፌዴራል ጸጥታ አስከባሪዎችን ለማስቆም ያደረገው ወንጀል ነው)
    ፭/ ደ/ጽዮን ድምጹን በወያኔ ሬዲዮ አስተላለፈ (ቪኦኤ ያስተላለፈው)፤
    ፮/ ጠ/ሚ ዐቢይ ዲክታተር ሆነ፤ ኖቤል ሽልማቱ ይሠረዝ የሚሉ፣ ወዘተ

    ይህ ሁሉ ውንጀላና ቱልቱላ፣ ህወሓት ሰላማዊ ሕዝብ ትግሬ አይደላችሁም ብሎ መፍጀቱን፣ አብሮ የተሰለፈውን፣ የትግራይን ሕዝብ አጨዳና አንበጣ ማጥፋት ሲረዳ የዋለውን በተኛበት የፈጸመበትን አሠቃቂ ጭፍጨፋ ለማረሳሳት ነው!
    መረጃው እንደ ቅጠል የትም ተበትኖ እያለ፣ በአገር ወዳድ ወገኖቻችን ንዝህላልነት ዋጋ እያጣ ነው!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule