በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ- ኃይል አሳሰበ። ግብረ-ኃይሉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች በይዘትም ሆነ በአፈጻጸም ስልታቸው ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ባሻገር በርካታ ግለሰቦች የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ ሀገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ … [Read more...] about እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ
social media fake info
ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል የሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። ግለሰቡ በተጨማሪም ሎችንም የሀሰት መረጃዎች "የትግራይ ልዩ ሃይል ድል" በሚል ርዕስ ፍሪደም ቲቪ በተባለ የዩቲዩብ አድራሻ በተለያ ጊዜ ያልተጨበጠ መረጃ ያሰራጭ እንደነበረ ተገልጿል። ይህ ሃጎስ ሰልጠነ ፍስሃዬ የተባለው ግለሰብ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ አገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ ዘረዝጊ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱም 6 መቶ የአሜሪካን ዶላር ይከፍለው እንደነበር ግለሰቡ … [Read more...] about ጄኔራሎች “ተገድለዋል” በሚል የሀሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ