በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ- ኃይል አሳሰበ። ግብረ-ኃይሉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች በይዘትም ሆነ በአፈጻጸም ስልታቸው ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ባሻገር በርካታ ግለሰቦች የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ ሀገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ … [Read more...] about እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ
social media
“ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳሰበ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከቀናት በፊት፦ "ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው። በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው። የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። " የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት … [Read more...] about “ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር ነው” – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
ኃላፊነት የጎደላቸው የማኀበራዊ ሚዲያና አንቂዎችን ከእንግዲህ አንታገስም
ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና ማህበራዊ አንቂ ነን የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታውቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት ያቀረበውን ሀገርን የመታደግ ጥሪ ተከትሎ ህዝቡ እና የመንግስት ሰራተኛው በነቂስ ዘመቻውን እየተቀላቀለ መሆኑን ገልጿል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የህብረተሰብን ሰላም እና ደህንነት የሚያውኩ ሆነው እስከተገኙ ድረስ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ አይታገስም ብለዋል። (EBC) ከግለሰብ በማለፍ መንግሥት በሕጋዊ መልኩ የት ህነግን ዓላማ እየፈጸሙ ያሉና በዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋምነት እየሠሩ ያሉትንም በዚሁ መልኩ እንዲመለከታቸው ጥሪ እናሰተላልፋለን። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኃላፊነት የጎደላቸው የማኀበራዊ ሚዲያና አንቂዎችን ከእንግዲህ አንታገስም