ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና ማህበራዊ አንቂ ነን የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታውቋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት ያቀረበውን ሀገርን የመታደግ ጥሪ ተከትሎ ህዝቡ እና የመንግስት ሰራተኛው በነቂስ ዘመቻውን እየተቀላቀለ መሆኑን ገልጿል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የህብረተሰብን ሰላም እና ደህንነት የሚያውኩ ሆነው እስከተገኙ ድረስ መንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ አይታገስም ብለዋል። (EBC)
ከግለሰብ በማለፍ መንግሥት በሕጋዊ መልኩ የት ህነግን ዓላማ እየፈጸሙ ያሉና በዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋምነት እየሠሩ ያሉትንም በዚሁ መልኩ እንዲመለከታቸው ጥሪ እናሰተላልፋለን።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply