
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳሰበ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከቀናት በፊት፦
“ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እና ውጤቶችን በተመለከተ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ፣ በየትኛውም የመገናኛ አውታር መስጠትና ማሰራጨት ክልክል ነው።
በየግንባሩ የሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ከተሰጣቸው ሥምሪትና ተልእኮ ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ የጦር ሜዳ ውሎዎችን እንዲሁም ውጤቶችን የሚመለከቱ መግለጫዎች መስጠት የተከለከለ ነው።
የጸጥታ አካላትም ይሄን ተላልለፈው በሚገኙት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዟል። ” የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የተላለፈውን ክልከላ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በመተላለፍ ላይ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት ያሳስባል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ ሀገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የሀገርን ህግ ከማክበር በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ያወጣውን ክልከላ የሚተላለፉ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። (ቲክቫህ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply