በተለያዩ ግንባሮች የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ፣ ለጎልጉል በደረሰው መረጃ መሠረት፣ የትህነግ (TPLF) ጽንፈኛ ቡድን እና አጋሩ የሆነው የአፋር “ኡጉጉሞ” ታጣቂ ቡድን ባካሄዷቸው የውጊያ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ የመስክ እና የኮር አመራሮቻቸውን አጥተዋል።
መስከረም 15 እና 16 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄዱ ከባድ ውጊያዎች የትህነግ በርካታ የክፍለ ጦር እና የኮር አዛዦች የተደመሰሱ ሲሆን፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል።
ለጎልጉል የደረሰው የውጊያ ውሎ ሰነድ እንደሚያመላክተው፣ የተመቱት አመራሮች ስም፣ ኃላፊነት እና የተመቱበት ቦታ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦
- ተስፋአለም (የአርሚ 26 ኮር 261ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ)፦ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ “ወንዳች” የተባለውን ስፍራ ለመያዝ በተደረገ ውጊያ ተደምስሷል።
- አሸናፊ (የአርሚ 26 ኮር 261ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ)፦ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በዚሁ በግዳን ወረዳ ወንዳች አካባቢ በተደረገ ውጊያ ተደምስሷል።
- ሙሴ (የአርሚ 11 ከፍተኛ አመራር)፦ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ሰቆጣን ለመያዝ በተደረገ ውጊያ ተደምስሷል።
- ፍስሃ (የአርሚ 11 ከፍተኛ አመራር)፦ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በሀሙሲት አካባቢ በነበረ ውጊያ በጽኑ ቆስሏል።
- ክብሮም (የአርሚ 11 የ111ኛ ኮር ክፍለ ጦር አዛዥ)፦ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ሰቆጣን ለመያዝ በተደረገው ውጊያ በጽኑ ቆስሏል።
- ስሙ ያልተለየ የኃይል አዛዥ (የአርሚ 24 የ242ኛ ኮር ሁለት የኃይል አዛዥ)፦ መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም በዋጃ ጥሙጋ አካባቢ “ቦታ ማሪያም” በተባለ ስፍራ በደረሰበት ምት ቆስሏል።
- ከደር ከሊፋ (የአፋር ታጣቂ /ኡጉጉሞ/ ሻለቃ አዛዥ)፦ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም በአፋር ክልል “ዓዲ ሓራ ማሊ” አካባቢ በነበረው ውጊያ በጽኑ መቁሰሉ ታውቋል።
በተለያዩ ግንባሮች የደረሰው ይህ ከፍተኛ የአመራር እልቂት እና ጉዳት በትህነግ እና በአጋሮቹ ወታደራዊ መዋቅር ላይ ከፍተኛ መናጋት እና መበታተን መፍጠሩን ለጎልጉል የደረሱ የመስክ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply