ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ውስጥ በጎርፍ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ። የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የተከሰተበት ወረዳው ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስን አካባቢ ነው። የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ከተፈናቃዮች መካከል ወ/ሮ ኛዳክ ፓችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከነቤተሰቦቻቸው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። መንግሥት የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት ባለማድረጉም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ወ/ሮ ኛዳክ ተናግረዋል። በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ሱዳንንና ኢትዮጵያን የሚያዋስነው ጂካዎ ወንዝ ሞልቶ በተፈጠረው ችግር ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ የሚኖሩትም … [Read more...] about በጋምቤላ በ10 ሺህዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለዋል
afar
አፋር የመንግሥትንና የሕዝብን አስቸኳይ ድጋፍና እርዳታ ይሻል!
ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም። አፋር የሃገራችን ዳር ድንበር ለዘመናት እየጠብቁ የቆዩ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው። እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200 ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው። ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል። አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል። በሌላ በኩል ፦ ጣና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩ የተነሳ ውሃው ተመልሶ በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን እያጥለቀለቀ ይገኛል። በዚሁ ምክንያት እስካሁን ድረስ በደንቢያ ወረዳ … [Read more...] about አፋር የመንግሥትንና የሕዝብን አስቸኳይ ድጋፍና እርዳታ ይሻል!