ሃራ ወይም ነጻ ተብሎ በሚጠራው መሬት ላይ ሠፍሮ የሚገኘው "የትግራይ የሰላም ኃይሎች" (TPF) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሙሉ ትግራይን እንደሚቆጣጠር አስታወቀ። "ጸጥተኛ" ብለው ለሚጠሩት አቢዮት ሠራዊቱ እየተዘጋጀ እንደሆነም ተነግሯል። ይህ የተገለጸው በፈረንሳይኛ ቋንቋ በድረገጽ የሚታተመውና አፍሪክ XXI (Afrique XXI) የተባለው ጋዜጣ ከጥቂት ቀናት በፊት በትግራይ ላይ በሠራው ዘገባ ነው። ዘገባው በሃራ ምድር የሰፈሩትን የትግራይ የሰላም ኃይል/ቲፒኤፍ ተብለው ከሚጠሩት ታጣቂዎች ጋር ቃለ ምልልስ ካደረገ በኋላ ነው። የሰላም ኃይሉ አባላት በአብዛኛው ከዚህ በፊት በትህነግ ሥር ከነበረው የትግራይ መከላከያ ኃይል ወይም ቲዲኤፍ (TDF) ከሚባለው ከድተው የወጡ ናቸው። በተለይ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በብዛት ከቲዲኤፍ እየኮበለሉ ወደ አፋር … [Read more...] about “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ
simret
በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ
በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦ 1ኛ. ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 4ኛ. አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 5ኛ. ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና 6ኛ. መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም በሙስና ወንጀል … [Read more...] about በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ


